የኤች. አይ. ቪ/ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ የ2009 ዓ.ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ

የኤች. አይ. ቪ/ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ የ2009 ዓ.ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚነስቴር ጤና ነክ ጉዳዮች በስርዓተ ትምህርትና መምህራን ትምህርት ስልጠና ውስጥ እንዲካተት ከማድረግ ባሻገር በተገኙ አጋጣሚዎች ሁሉ በመጠቀም ማለትም ከክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከህትመትና ከኤሌክትሮኒክስ ሚዲያና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት እንዲሁም በየደረጃ ያሉ ትምህርትና ስልጠና  ተቋማት ውስጥ የተቋቋሙ ክበባት ለዚሁ ስራ በመጠቀም የትምህርት ማህበረሰቡንና የአካባቢውን ህዝብ የጤናን እውቀት ይበል በማጎልበት የበኩሉን እገዛ በማበርከት ላይ ነው፡፡

 

በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የኤች. አይ. . ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች፣ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲዎችና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመሆን የተማሪዎች የመማር ሂደት ምቹ፣ ለጤንነታቸው የማያሰጋ ተማሪዎች ለትምህርት ያላቸውን ፍላጎትና ተነሳሽነት እንዲጨምር  የትምህርት አቀባበላቸውም እንዲሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

 

በዘርፉ የኤች. አይ. /ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ ሃላፊ አቶ ሙሴ ተስፋው አመታዊ ምክክር ጉባኤውን በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት መድረኩ 2009 . በጀት አመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈጻጸም ለመገምገምና በሚኒስቴር /ቤቱ የተዘጋጀውን የትምህርት ማህበረሰብ ውይይት ሰነድ (School Community Conversation’s Manual) እና በዘርፉ የኤች. አይ. . ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ  የማስተግበሪያ ሰነድ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ አስተያየት በማሰባሰብ ሰነዱን ለማዳበር ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

በዘርፉ ያሉትን ተማሪዎች፣ ሰልጣኞች፣ መምህራን፣ አመቻቾችና የትምህርት ማህበረሰብን በማሳተፍ ከኤችአይቪ/ኤድስ  እና ሥነ-ተዋልዶ ጤና ችግሮችን  ቀጣይነት ባለው መልኩ በመከላከል  አምራችና ጤናማ ዜጋ ማፍራት  እንደሚቻል አቶ ሙሴ ጠቁመዋል፡፡

ሀላፊው  በሚኒስቴር /ቤቱ የኤች. አይ. . ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ  ባለሙያዎች በሁለት ቡድን ተዋቅረው ሰባት የክልልና ከተማ አስተዳደር  ትምህርት ቢሮዎች፣ 24 ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤቶች፣ አምስት የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች እንዲሁም 14 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያገናዘቤ  የአካል ምልከታ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ 

 የወጣቶችን ተጠቃሚነትና ምርታማነት ለማሳደግ  በስነ ተዋልዶ-ጤና የኤች. አይ. /ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባም አቶ ሙሴ አሳስበዋል፡፡

 

በሚኒስቴር /ቤቱ የኤች. አይ. . ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ የሚይንስትርምንግ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ታደለ ጆቴ የክልል ትምህርት ቢሮዎች የአካል ምልከታ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት የኤች. አይ. /ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠሪያ ስራዎችን እቅድ ውስጥ ለማስገባት ጅምር ስራዎች መኖራቸውን በመጥቀስ ሁለት በመቶ ፕሮግራም በጀት ውስጥ በማስገባት ወደ ስራ የገቡ ክልሎች ጥቅት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

 

በሁሉም የትምህርትና ስልጠና  ዘርፍ መዋቅሮች፥ በማስተግበሪያ  ሰነዶች፣ ዕቅዶችና ፕሮገራሞች ውስጥ ኤችአይቪ/ኤድስን የመከላከልና የመቆጣጠር ዋና ዋና ተግባራት ተካተው በማይቋረጥ ሁኔታ  መከናወን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡  በየእርከኑ የሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ተቋማት መምህራን፣ ሠራተኞች፣ ሰልጣኞችና ተማሪዎች ከኤች.አይ /ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች ራሳቸውን እንዲጠበቁ የክልሎችን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ  የአቻ ለአቻና የህይወት ክህሎት ስልጠናዎች ለመስጠት የስልጠና ማኑዋል ለማዳበር ግብዓት የማሰባሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን አቶ ታደለ ጠቁመዋል፡፡

 

በየደረጃው ያሉ የትምሀርትና ስልጠና  gማት ውሰጥ በኤች. አይ. /ኤድስና ተዘማጅ በሽታዎች ተጋላጭ ለሆኑ ተማሪዎች ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል  እንደሚገባ ባለሙያው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ለናሙናነት ከተመረጡ  ሰባት  የክልል ትምህርት ቢሮዎች ውስጥ ወደ 29 የሚጠጉ ትምህርት gማት የአካል ምልከታ የተደረገ ሲሆን በክልል ትምህርት ቢሮዎችና በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲዎች አሁንም የኤች. አይ. /ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች ፕሮግራሙ በአግባቡ ለማሳለጥ በስራ እቅድ ውስጥ ከማካተት የኤድስ ፈንድ ከማggም፣ በመመሪያው መሰረት እስከ ሁለት በመቶ በጀት ከመመደብ፣ ግብረ ሃይል ከማgg አንጻር ክፍተቶች  እንዳሉ ሪፖርቱ ያመላክታል ብለዋል፡፡ 

 

 የደቡብ ክልል፣ የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች እንዲሁም ከፍተኛ ትምህርት gማት የተሻለ እቅድ አፈጻጸም ሲኖራቸው በሌሎች ትምህርት gማትም ጅምር ስራዎች እንዳሉ ሆኖ ብዙ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አቶ ታደለ ተናግረዋል፡፡

 

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት መሰረት የኤች. አይ. . ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ የጤና ጤና ነክ ተጓዳኝ ትምህርት ማስተግበሪያ ሰነድ፣ ከሚኒስቴር /ቤት ጀምሪ እስከ ትምህርት ቤቶች ያሉት ትምህርቶች አደረጃጀት ከማጥናት በተጨማሪ ለትምህርት ማህበረሰብ የሚሰጡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ያሳዩት ተጨባጭ የባህሪ ለውጥ ላይ ዳሰሳዊ ጥናት ማካሄድ እንደሚያስፈል ተናግረዋል፡፡

 

በመድረኩ ከሚኒስቴር /ቤቱ ፣ከዘጤኙም ክልል ከሁለት ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎችና ከፍተኛ ትምህርት gማት የተውጣጡ  ባለሙያዎችና የፕሮግራሙ ተጠሪዎች ተሳትፈዋል፡፡


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡