በ28 የፌዴራል መንግስት ተቋማት መካከል በተደረገው ምዘና የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የትምህርት ሚኒስቴር ቀዳሚ ሆነ፡፡

በ28 የፌዴራል መንግስት ተቋማት መካከል በተደረገው ምዘና የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የትምህርት ሚኒስቴር ቀዳሚ ሆነ፡፡


እነዚሁ ተቋማት ባስቀመጡት የስርዓተ ፆታ ማካተት፤ ተቋማዊነትና የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መከታተያ፤ መመዘኛና ደረጃ ማዕቀፍ መሰረት ከፖሊሲና ህግ፤ተቋማዊ መዋቅር፤ አቅምና ክህሎትን ማጎልበት በቅድመ ሁኔታዎች ሲቀመጡ፤ ስርዓተ ፆታን በማካተት ሂደትም የእቅድ ዝግጅት አፈጻጸምና ክትትልና ግምገማ እንዲሁም ንቅናቄ መፍጠር በትብብርና ቅንጅት ስራ ላይ ያተኮሩ መገምገሚያ ነጥቦች ተካተዋል፡፡
የኢ.... ትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ፆታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለምዘናው የተቀመጠውን መገምገሚያ መስፈርት በማሳካት 76.24 ከመቶ በማምጣት 28 የፌዴራል ሴክተር መስሪያ ቤቶች ቀዳሚ እንዲሆን አስችሎታል፡፡የስርዓተ ፆታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ገሰሰ ውጤቱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የከፍተኛና የመካከለኛ አመራር እንዲሁም የአጠቃላይ ሠራተኛውና የሁሉም የትምህርት ባለድረሻ አካላት ቁርጠኝነት ድምር ውጤት ነው ብለዋል፡፡ ይህም 5ኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት ዕቅድ በተቀመጠው መሠረት በየደረጃው ያሉት አመራሮች የተቋማዊ መዋቅር ለውጥ የሴቶች ተሳትፎና ለአመራርነት የማብቃት ስራ ተሰርተዋል፤ ክትትልና ድጋፍም ተደርገዋል ብለዋል፡፡
ሆኖም ግን ዳይሬክተሯ እንደገለጹት ሀገራችን 2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ እንዲትሰለፍ የበለጠ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤ የተለያዩ የጎንዮሽና የሌሎች ሀገራትን ልምድ በመቅዳት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችንና የልምድ ልውውጦችን ከማዘጋጀት አንጻር አሁንም ገና ይቀረናል ይላሉ፡፡ በሚቀጥሉ ጊዜያት አነስተኛ ነጥብ ያሰጡን እንደነጥናትና ምርምርያሉት ጉዳዮችን ነጥለን እነዛ ላይ እንሰራለንም ብለዋል፡፡
በመጨረሻም በምዘናው መሠረት ስለ ስርዓተ ጾታ ገና ያልተገነዘቡ፤ ግንዘቤው ያላቸው ግን ያልሰሩበት፤ተገንዝበው ወደ ስራም ገብቶ ውጤት ያላሳዩ እና ወደ ስራ ገብቶ በቁርጠኝነት በመስራት ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማት ተብለው ተለይተዋል ያሉት ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሀገራችንን ሁለንተናዊ ልማት እውን ለማድረግ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸውና ከትምህርት ሚኒስቴር ልምድ መቅሰም እንዳለባቸው አብራርተዋል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡