በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የታቦር 2ኛ ደረጃና መሰናደ ትምህርት ቤት መምህራንና የአስተዳዳር ሰራተኞች ውይይት አካሄዱ

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የታቦር 2ኛ ደረጃና መሰናደ ትምህርት ቤት መምህራንና የአስተዳዳር ሰራተኞች ውይይት አካሄዱ

አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊዎች ለሰላማዊ መማር ማስተማር እንቅፋት ከሆኑት የሰላምና የጸጥታ እንዲሁም ከኢኮኖሚ ጋር ተያይዞ በመንግስት በኩል ሊታረሙና ሊሻሻሉ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ መንግስት ፈጣንና ተግባራዊ ምላሽ ሊሰጥ እንደሚገባው የጠቆመ ስልጠናና ውይይት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ውይይትና ስልጠና መካሄዱ በመምህራኑ ላይ ያለውን ብዥታ ግልጽ በማድረግ በተማሪዎች ዘንድ ለሚነሱ ብዥታዎች መምህሩ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በሚያስችል መልኩ ግንዛቤ የፈጠረ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡news

የታቦር 2ኛ ደረጃና መሰናደ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህር አቶ ተሻለ ደስታ በበኩላቸው ባለፉት 25 ዓመታት በትምህርቱ ዘርፍ ላስመዘገብናቸው ስኬቶች ላጋጠሙንን ጉድለቶችን ለመሙላት ከፌዴራል እስከ ትምህር ቤት ድረስ ያሉ ባለድርሻ አካላት እንዴት ተወጡና ከዚህም ምን ተማርን የሚለውን ውይይቱ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ ሀገሪቱ የምትፈልገውን በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት በተለይም በስነምግባርና በስነዜጋ የታነጸ ትውልድ በማፍራት ረገድ የት ደረጃ እንዳለና ክፍተቶቹን በመለየት ምን ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው ግልጽነትን የፈጠረ ውይይትና ስልጠና መሆኑን አቶ ተሻለ አብራተዋል፡፡

የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ስልጠናና ውይይቱ በባለፉት ጊዜያት በትምህርት ልማት ስራችን ላይ ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በማረም በቀጣይ በተለይም ከተሳትፎና ከትምህርት ጥራት አንጻር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡ 

newsውይይቱ መምህሩ የለውጥ ማእከል ሆኖ እንዲቀጥልና የትምህርት አመራሩም ተገቢውን አመራር እየሰጠ የሚቀጥልበት መግባባት ላይ ያደረሰ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሚሊዬን ይህም ትምህርት ቤቶች የሰላም ምንጭ በመሆን ተማሪዎች ተገቢውን እወቀት እንዲቀስሙ በማድረግ የትምህርት ጥራት እንዲጠበቅ ድርሻው የጎላ ነው ብለዋል፡፡


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡