የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ መሥሪያ ቤቶች የጠቅላላው ሠራተኞች የጥልቅ ተሃድሶ ማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ

የትምህርት ሚኒስቴርና የተጠሪ መሥሪያ ቤቶች የጠቅላላው ሠራተኞች የጥልቅ ተሃድሶ ማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ

የትምህርት ሚኒስቴር እና የተጠሪ መሥሪያ ቤቶች ሰራተኞች የጥልቅ ተሃድሶ ማጠቀለያ መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ በኦሮሚያ የባህል  አደራሽካቲት 8 እና 9/2009 .   ተካሄደ፡፡

 

በመድረኩ መላው ሠራተኞችና በየደረጃው ያሉ አመራሮች የተገኙ ሲሆን መድረኩን የመሩት የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር / ሽፈራው /ማሪያም ናቸው። መድረኩ የተጀመረው ከደቡብ ኮሪያ የመጡ ልዑካን ቡድን ሀገራቸው 50 ዓመታት በፊት ከዓለም ከህንድ ሀገር ቀጥላ 2 ደረጃ ከነበረችበት እጅግ በጣም አስከፊና ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ተነስታ በአሁኑ ወቅት የደረሰችበትን የኢኮኖሚ እድገት ደረጃንና እድገቱን ተከትሎ ከቅርብ አመታት ወዲህ የተከሰተባትን (በርካታ ዜጎች የደካማ አእምሮ ባለቤት መሆንና ራስን ወይም ፎላጎትን ከነባራዊ ሁኔታ አንጻር መቆጣጠር ያለመቻል) ማህበራዊ ችግር ለመግታት በተግባርና በንድፈ ሀሳብ ለህጻናት፣ለወጣቶችና ለወላጆች እየተሰጠ ያለውን ጠንካራ እእምሮ የመፍጠርና ራስን የመቆጣጠር ትምህርትን ውጤታማነት በተመለከተ ገለጻ ቀርቧል። በገለጻው ላይ አስተያየትና ያቄ እንዲቀርብ በተሰጠው ዕድል መሠረት የተወሰኑ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተሳታፎች ቀርበው መልስና ማብራሪያ ተሰጥቶኣቸዋል። አስተያየት ሰጪዎችም በገለጻው  በርካታ አስተማሪና የይቻላል መንፈስ የሚያላብሱ መልዕክቶች እንደተላለፉ ገልጸዋል። ክቡር ሚኒስትሩም ትምህርቱን በሥርዓተ-ትምህርታች አከተን ለመስጠት ከደቡብ ኮሪያኖች ጋር የተጀመሩ እንቅስቃሴዎች  እንዳሉ ገልጸዋል።

 

በመቀጠል የመድረኩ ትኩረት የጥልቅ ተሃድሶ ማጠቃሊያ ሲሆን  ለውይይት መነሻ ይሆን ዘንድ የጥልቅ ተሃድሶው ግቦች፣የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች ፣የትግበራ ሄደት፣የተገኙ ውጤቶች እና ለማሳያነት ያህል በመልካም አስተዳደር ችግርነት ተለይተው የድርጊት መርሃ ግብር የወጣላቸው 80 ነጥቦችን የያዘ ሰነድ በትምህርት ዘርፍ የለውጥ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት በሆኑት በአቶ እሊያስ ግርማ ቀርቧል። የታለፈበት የጥልቅ ተሃድሶ ሂደት ላይም ሆነ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለውይይት መነሻ እንዲሆንና እግረመንገዱንም እንዲዳብር በቀረበው ሰነድ ላይ ተሳታፊዎች አስተያየት እንዲሰጡና ጥያቄ እንዲጠይቁ በተሰጠው እድል መሠረት በርካታ አሰተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው መልስና ማብራሪያ አግኝተዋል።

 

የጋራ መግባባት የተደረሰባቸው የሚከተሉት ነጥቦች ነጥረው ወጥተዋል። እነሱም፦ የማታ ትምህርት፣የርቀትና የክረምት ትምህርት አሰጣጥ ከጥራት አንጻር ያለበትን ደረጃ የሚለካ ደሰሳዊ ጥናቶች በቅርቡ መካሄድ እንዳለባቸው፣ ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠናም ሆነ ከከፍተኛ ትምህርት የሚወጡ ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ሥራ ፈጣሪ ወይም ተቀጣሪ እንዲሆኑ መሥራት ጉዳዮች ጥቃቅን ሳይባሉ በአፋጣኝ ውሳኔ እንዲያገኙ መሥራት፣ሀገራችን የምንፈለገውን ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ሊታመጣ ከሆነ ሁላችንም መለወጥ እንዳለብንና ለውጥ ደግሞ የምጀምራው ከራስ እንደሆነ፣ የሀገራችንን ህዳሴ ወደ ፊት ልንወስድ ከሆነ ልማታዊ ዴሞክራሲያዊነትን፣ ውጤታማነትንና የህዝብ አገልጋይነትን እሴት አድርገን ተላብሰን የዕለት-ተዕለት መርሆዎቻችን አድርገን መንቀሳቀስ ያለብን መሆኑ፣ በጥልቅ ተሃድሶው የተለዩ ጠንካራ ጎኖችን የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠልም ሆነ የተለዩ ደካማ ጎንችን በቀጣይነት ለማረምም ሆነ ለማስወገድ የሚያስቸለን ዋነኛ አማራጭ ከአድር ባይነት የጸዳና መገነባበትን ማዕከል ያደረገ ትግል ስለመሆኑ፣በየጊዜው የሚንወስናቸው የጋራ ውሳኔዎች ወደ ተጨባጭ ውጤት መቀየር እንዳለባቸው፣ ህዝብን በሚገባ ለማገልገል ጥሩ የሆነ የማስፈጸም አቅም መገንባት እንዳለብን፤ለዚህ ደግሞ መቀናጀት፣መደራጀትና የህዝብ ክንፎቻችን በሚገባ በሁለንተናዊ ሥራዎቻችን ላይ ማሳተፍ እንዳለብን እና የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብም ሆነ ተግባር የሀገሪቷ ሁለንተናዊ እደገት እንዳይቀጥል ከማድረግ  ባለፋ ሀገሪቷ እንደ ሀገር እንኳን እንዳትቀጥል የሚያደርግ በመሆኑ ሁላችንም በመጀመርሪያ ራሳችንን ከዚህ አስተሳሰብና ተግባር ማጽዳት እንዳለብንና በመቀጠል ሌሎችንም መታገል እንደሚገባን፣ በመጨረሻም የአከፋፈል ሁኔታው ለግለ ሰቦች የተተዋ ውሳኔ ሆኖ መላው ሠራተኞች በአንድ ወር ደመወዛቸው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ቦንድ ይገዙ እንደሆነ ከመድረኩ ሀሳብ የቀረበ ሲሆን በአብዝሃኛው ሠራተኞች ሀሳቡ ተቀባይነትን አግኝቷል።


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡