ፐብሊክ ሰርቫንቱ የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ መላበስ ለሀገር ዕድገት ቁልፍ ሚና እንዳለው ተገለፀ፡፡

ፐብሊክ ሰርቫንቱ የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ መላበስ ለሀገር ዕድገት ቁልፍ ሚና እንዳለው ተገለፀ፡፡

ይህ የተገለጸው የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ለዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞና ተጠሪ ተቋማት ከጥር 04-10/2009. የፐብሊክ ሰርቫንቱ ጥልቅ ታሀድሶን አስመልክቶ ባዘጋጀው  መድረክ ነው፡፡

የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች፣ በመንግስትና ህዝብ ስልጣን ያለአግባብ የመጠቀም፣ ኪራይ ሰብሳቢነት እንዲሁም ሌሎች ብልሹ አሰራሮች ከስር መሰረታቸው ለማረምና ለማስተካከል ሕዝባዊ እርካታና አመኔታ ያለው መንግስታዊ አሰራርና አመራር ለመፍጠር እንዲቻል ፐብሊክ ሰርቫንቱ የበለጠ  የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ እንዲላበስ የሚረዳ በሀገር አቀፍ ደረጃ ጥልቅ ተሀድሶ ፕሮግራም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ / ሽፈራው ተክለማርያም "በፐብሊክ ሰርቪሱ የነቃና የተደራጀ ተሳትፎ የህዳሴ ግቦቻችን እውን ይሆናሉ " በሚል መሪ ቃል በትምህርት ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤትና በለሎች ተጠሪ ተቋማት የተካሄደውን ጥልቅ ታሀድሶ መድረክ  በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት  በሀገራችን ባለፉት አመታት በተለይም ባለፉት 13 አመታት ባለ ሁለት አሀዝ ዕድገት የተመዘገበ ሲሆን በዚህ ውጤት  የፐብሊክ ሰርቫንቱና የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ክቡር ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

እንደ ክቡር ሚኒስትሩ ንግግር የመድረኩ ዋና አላማ ባለፉት 15 አመታት ጉዞ መነሻ በመድረግ ጥልቅ ግምገማ ለማድረግ፣ ስርዓቱን የሚፈታተኑ በየወቅቱ ብቅ ጥልቅ የሚሉ የተሳሳተ አመለካከቶችና አስተሳሰቦች እንዲሁም ተግባሮች ምንጮቻቸውን በመለየት ለማስወገድ  ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሃገራችን የጀመረችውን የህዳሴ ጉዞ ለማሳካት የፐብሊክ ሰርቫንቱ የነቃና የተደራጀ ተሳተፎ የማይተካ ሚና እንዳለው ክቡር ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን በየጊዜው ራሱን በመፈተሽ ለህዝብ ጥያቄ ምልሽ የሚሰጥ ነውያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ባለፉት 25 አመታት በሀገር አቀፍ ደረጃ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባት እየጎለበተ መምጣቱ፣ ለዴሞክራሲ መሰረት የሚሆኑ ህግ መንግስትና ህጋዊ ማዕቀፎች የተዘረጉበት አስተማማኝ ሰላም የሰፈነበትና ባለ ሁለት አሀዝ የኢኮኖሚ ዕድገት የተመዘገበበት እንዲሁም ማህበራዊ ተቋማት የተስፋፉበትና ሰፋፊ የሆኑ መሰረተ ልማቶች የተዘረጉት በፐብሊክ ሰርቫንቱና የህዝብ የነቃ ተሳትፎ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በየደረጃው ያለው የመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚሰሩ  ፐብሊክ ሰርቫንት በህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ከውጤታማነት፣ ከስነ ምግባር ፣ከኪራይ ሰብሳቢነት ጋር ተያይዞ እንዲሁም ከመልካም አስተዳደር  አኳያ ያገጠሙ ተግዳሮቶች በጥልቅ ታሀድሶ ወደ ራሱ በመውሰድና ራሱን ፈትሾ በማረም  በቀሪው ጊዝያት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት መረባረብ እንደሚገባም ክቡር ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል፡፡

ዶክተር ሽፈራው አክለውም ህብረተሰቡ ከመንግስት የሚፈልገውን ቀልጣፋ የገልግሎት አሰጣጥ፣ ፐብሊክ ሰርቫንቱ ለህዝብና ለሀገር ያለውን ወገንተኝነት ለማረጋገጥ በተሰማራበት የሙያ መስክ ስራውን በቅንነት፣ በውጤታማነት፣ በታማኝነት፣ እንዲሁም የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ  በመላበስ  የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ብልሹ አሰራሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ በትጋት መስራት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ / ጥላዬ ጌቴ 15 አመት ጉዞ የልማታዊ ዴሞክራሳያዊ መንግስት ልዩ ባህሪ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት ዴሞክራሲና ልማት የመንግስት ብቻ ሳይሆን የህዝብ ትኩረት አጃንዳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የግብርና ምርታማነት ገበያው ከፈጠረው ዕድል ጋር ተያይዞ የሀገራችን አርሶና አርብቶ አደሮች ከዕደገቱ ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱ፣ በከተሞች አነስተኛና  ጥቃቅን ተቋማት እንዲሁም በባለሀብቱ የሚገነቡ የምርትና አገልግሎት ተቋማት መስፋፋታቸው የብዙ ዜጎች ተጠቃሚነት መረጋገጥ መቻሉ በልማታዊ ዴሞክራሳያዊ ስርዓት ውጤት የተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩም አመራሩና ፐብሊክ ሰርቫንቱ  በአስተሳሰብ፣ በአመለካከትና በተግባር የሚታዩ ስልጣንን እንዲሁም የመንግስትና የህዝብ አገልግሎትን  ለግል ጥቅም አደርጎ መጠቀም፣ የስነ ምግባር ጉድለት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች፣ ኪራይ ሰብሳቢነት ማለትም የትምክህት፣ የጠባብነት፣ የሃይማኖት አክራሪነት እና የመሳሰሉ አፍራሽ አስተሳሰቦችንና ተግባሮችን የፐብሊክ ሰርቫንቱ አጠብቆ ሊዋጋቸው እንደሚገባም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡