የአጠቃላይ ትምህርት አመራር አደረጃጀት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎ ና ፋይናንስ መመሪያ ለትምህርት ጥራት ወሳኝ ነው

የአጠቃላይ ትምህርት አመራር አደረጃጀት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎ ና ፋይናንስ መመሪያ ለትምህርት ጥራት ወሳኝ ነው

የአጠቃላይ ትምህርት አመራር አደረጃጀት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎ ፋይናንስ   መመሪያ ለትምህርት ጥራት ወሳኝ ነው

የትምህርት ስራ  ውጤታማ የሚሆኖው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ ሲያደርጉ የህብረተሰቡ አካላት የሚጠበቁባቸውን  ድርሻ በጋራ ለመወጣት የሚያስችላቸው ወቅቱና ቴክኖሎጂው የሚፈልገው  ምቹ ሁኔታ ሲፈጠር ነው፡፡

ይህንኑ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የሀገራችን የትምህርት አመራር አደረጃጀት እንዲሁም አሰራሩም ፌዴራላዊ ስርዓቱን ተከትሎ ያልተማከለ ሙያዊ፣ በቅንጅት የሚሰራ ዴሞክራሲያዊ ግልጽና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል አሳታፊ እንዲሆን ተደርጓል፡፡

መንግስት 1994. የሀገሪቱን ትምህርት ዘርፍ ልማት እንቅስቃሴዎችን በመፈተሽ ተሀድሶ ፕሮግራም ከተካሄደ በኃላ ከተለዩ የትኩረት ነጥቦች  መካከል አንዱ  የአጠቃላይ ትምህርት አመራር  አደረጃጀት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎ የፋይንናንስ መመሪያ እንዲሁም የአጠቃላይ ትምህርት ቤቶች ስታንዳርድ ነው፡፡

በዚሁም መሰረት ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎችን ውጤትና ስነ ምግባር ማዕከል ያደረገ የአጠቃላይ ትምህርት አመራር አደረጃጀት፣የህብረተሰብ ተሳትፎና   ፋይናንስ አሰራር ረቂቅ መመሪያ የመጨረሻ ቅርጽ ለማስያዝ በአዳማ ከተማ ከጥር 03-06/2009. በየደረጃው ያሉ የትምህርት አማራሮችና ባለሙያዎችን ያሳተፈ አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡

አውደ ጥናቱን በንግግር የከፈቱት በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሳቡ ብርቅነህ እንደገለፁት የአውደ ጥናቱ ዋና አላማ በትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም አተገባበር ዙሪያ ሁለት መሰረታዊ ከሆኑት አንዱ የትምህርት አመራር አደረጃጀት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና የፋይንናንስ አሰራር  ረቂቅ መመሪያ ለማሻሻል እንዲሁም  የአጠቃላይ ትምህርት ቤቶች ስታንዳርዶች በተመለከተ ከባለድርሻ ጋር በመሆን አስተያየቶችና ግብዓቶች በማሰባሰብ የመጨረሻ ቅርጽ እንዲይዙ ለማድርግ ታስቦ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የትምህርት አመራርና አደረጃት ረቂቅ መመሪያ  እና የቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መለኪያ በትምህርት ቤቶች የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች፣  በትምህርት ስራ ውስጥ  የህብረተሰቡ  ተሳትፎ  የላቀ እንዲሆን የተማሪዎች ውጤትና ስነ ምግበር በተከታታይነት ለማሳደግ እንዲሁም  የትምህርት ጥራት በሚፈለገው ደረጃ ለማሻሻል የጎላ አስታዋጽኦ እንደሚያበረክትም አቶ ያሰቡ ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም  አሁን በመሻሻል ላይ ያለው  ረቂቅ መመሪያ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ፓኬጅ ለመተግበር የወጡ መርሃ ግብሮችን  ወቅቱ የደረሰበትን የህብረተሰብ ፍላጎትና የቴክኖሎጂ ዕድገት  ከዚህ በፊት በመዋቅሩ ላይ ያልነበረ ቅድመ-መደበኛ ትምህርት እና የመምህራንና ትምህርት አመራርና ሙያ ፍቃድ አሰጣጥና እድሳት ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል፡፡

ስታንዳርዶቹና መመሪያዎቹ መሻሻል ለትምህርት ጥራት የሚኖረው አስታዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ የአውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች የመጨረሻ ቅርጽ ለማስያዝ በቀረቡት ሰነዶች ላይ በቡድንና በጥልቀት ሊወያዩ እንደሚገባም ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

እንደ አቶ ያሳቡ ንግግር መመሪያዎችና ስታንዳርዶች የማይነጣጠሉና ተመጋጋቢ  ከመሆናቸው የተነሳ   አንዱ ከሌላው ቀድሞ ተሻሽሎ ስለማይተገበር  በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ህግ ክፍልና በከፍተኛ አመራሮች  ከታየ በኃላ ፅድቆ  በተያዘው በጀት አመት መጨረሻ  ተግባራዊ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም አማካሪ አቶ ኃይለ ጊዮርጊስ ፈለቀ የትምህርት አመራር  አደረጃጀት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና የፋይንናንስ ረቂቅ መመሪያ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት የመመሪያው ይዘት አራት ክፍሎች የያዘ ሲሆን አራቱም በትምህርት አመራር  አደረጃጀት አስፈጻሚ አካላት ኃላፊነትና ተግባራት፣ በትምህርት ባለሙያዎች ኃላፊነቶችና ተግባራት ለምሳሌ ሙያ ፊቃድና እድሳት አተገባባር በተመለከተ፣ በትምህርት ስራ ውሰጥ ህብረተሰብ በባለቤትነት  ለማሳተፍ የሚያግዝ  እና ትምህርት ፋይናንስ አሰራር ስርዓት መሆናቸውን  አስገንዝበዋል፡፡

የአውደ ጥናቱ ተሳታፊ የሆኑት በሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የእንስፔሽን ስራ ሂደት ኃለፊ አቶ ዘሪሁን ተፈራ አስተያየት በሰጡት ወቅት 1994 . የተዘጋጀ መመሪያ 15 አመታት የአገልግሎት ዘመን ውስጥ በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የሀገራችን ማህበራዊና ኢኪኖሚያዊ ዕድገት ፍላጎትን መሰረት በማድረግ፣ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ወጥና ፍትሃዊ አሰራር እንዲሰፍን እንዲሁም የአጠቃላይ ትምህርት ስታንዳርዱ የትምህርት ቋንቋ ምን መምሰል እንዳለበት ግብዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል፡፡

የአውደ ጥናቱ  ተሳታፊዎች ባቀረቡት አስተያየት  የትምህርት አመራር አደረጃጀት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና የፋይናንስ ረቂቅ መመሪያው  ትምህርት ጥራት በሚፈለገው ደረጃ ለማሻሻል፣ የማህበረሰቡ ትምህርት ተሳትፎን ይበልጥ ለማሳደግ እንዲሁም  ግልጽና ፍትሀዊ የፋይናንስ አሰራር ለመከተል ይረዳል ብለዋል።

 


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡