በለውጥ ሥራዎች ላይ ያተኮረ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄደ

በለውጥ ሥራዎች ላይ ያተኮረ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄደ

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የልውጥ /ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉበት የልምድ  ልውውጥ መድረክ ተካሄደ። መድረኩ የተዘጋጀው በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ዘርፍ ሪፎርም ዳይሬክቶሬት ከከፍተኛ ትምህርት አስተዳደራዊ ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበበር ሲሆን የተካሄደው ከታህሳስ 17-19/2009 . በአዳማ ከተማ ነበር። የከፍተኛ ትምህርት አስተዳደራዊ ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት / ከተማ መስቀላ በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የመድረኩን ዓለማ በሚመለከት መድረኩ ተመሳሳይ ሥራን የሚሠሩ አካላት የታደሙበት መድረክ እንደመሆኑ መጠን ከሁሉም የኒቨርሲቲዎች የመጡ የለውጥ /ቤት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እርስ በርሳቸው እንድተዋወቁ፣እንዲማማሩና እንዲደጋገፉ በማድረግ  የተሻለ አፈጻጸምና ልምዶች ያላቸው  ተቋማት ከስኬቶቻቸው በስተጀርባ ያሉትን ምስጥሮች ለሌሎች የሚያካፉሉበት መድረክ መሆኑን ጠቅሰው ይህ አይነቱ መድረክ እንደ ትምህርት ሚኒስቴርና እንደ ዩኒቨርሲቲዎች ያሉብንን ክፍተቶች  በመለየት እንዲንሞላ የሚያግዘን ከመሆኑም በላይ የለውጥ ፕሮግራሞች ቀጣይነትና ወጥነት ባለው መልኩ ተፈጻሚ እንዲሆኑ በማድረግ የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የፈጻጸም ደረጃ ተቀራራቢ እንዲሆን እጅግ በጣም ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ  ከየጀነሬሽኑ ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች ቀደም ብሎ ከትምህርት ሚኒስቴር በተላከላቸው የሪፖርት ማቅረቢያ ነጥቦች መሠረት ያዘጋጁትን ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን እነሱም፦ ከመጀመሪያ ጀነሬሽን  ጎንደርና ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ ከሁለተኛ ጀነሬሽን ደብረብረሃንና ወለጋ እና ከሦስተኛ ጀነሬሽን ደብታቦርና አድግራት ዪኒቨርሲቲ ናቸው። በሪፖርቶቹ ከተገለጹት ስኬታማ አፈጻጸሞች መካከል ለአብነትያህል የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የለውጥ /ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ይልማ አስማማው ሪፖርታቸውን ባቀረቡበት ወቅት ተማሪዎች 15 አደረጃጀትን ተጠቅመው እርስ በርስ መረዳዳት ከጀመሩ ወዲህ ያለውን መሻሻል ለመገምገም 2008 በጀት አመት በተደረገ ዳሰሳ ጥናት ከአጠቃላይ ተማሪዎች አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ውጤት መሻሻል ያሳየ መሆኑን ጠቅሰው  በሠራተኞችና በመምህራን ዘንድም  እርስ በርስ የመረዳዳት ባህል እየዳበረ መምጣቱንና አወንታዊ የሆነ የውድድር መንፈስ የተፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ይልማ በማከል በዩኒቨርሲቲው ሁለተናዊ ውጤት እንዲመዘገብ በሚያስችል መልኩ በሙከራ ደረጃ ካለው አውቶሜሽን በስተቀር ሁሉም የለውጥ መሣሪያዎች በተግባር ላይ እያዋሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው የራሱ የሆኑ የዕቅድ አዘገጃጀት፣ የሪፖርት አዘገጃጀት፣ የተቋማዊ ጥራት ማሻሸያና ማረጋገጫ፣በየደረጃው ያሉ የዩኒቨርሲቲው የአመራር አካላትና ፈጻሚዎች ከአፈጻጸማቸው አንጻር የሚመዝኑበትና የግለ-ሰቦች በቡድን የመሥራት ብቃት የሚለካበት፣የማህበረሰብ አገልግሎት አፈጻጸም የሚለከበት፣የደንበኞች የእርካታ ደረጃ የሚመዘንበት እና የመሳሰሉ ሥራዎች የሚሠሩበትን ስታንዳርዶችና ቼክሊስቶችን አግባብነት ካላቸው አዋጅ፣ደንቦችና መመሪያዎች ጋር በማይፋለሱበት መልኩ በመዘጋጀት እየሠረበት የሚገኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የአድግራት ዩኒቨርሲቲ የእቅድና የለውጥ /ቤት ኃላፊ የሆኑት / ሰላማዊት ተክሉ ሪፖርታቸውን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት ተማሪዎች በሠራዊት አግባብ ተንቀሳቅሰው ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ 1 5 አደረጃጀታቸው አማካኝነት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የጥናት እቅድ (Schedule) እንዲሁም ተደራሽ የውጤት ግብ (Anticipated Grade) በስሚስቴሩ መጀመርያ አስቀድመው እንዲሞሉ እንደሚደረግ፤ ለእያንዳንዱ የልማት ቡድን (Section) አንድ-አንድ አስተባባሪ መምህር (አጋዥ መምህር) እንደተመደበላቸው፣ መምህሩ በተገኘበት በሳምንት ሁለት ቀናት እንደሚገናኙ (ለምሳሌ፡ ማክሰኞና ሐሙስ)፣በየሳምንቱ ለመምህራኖቻቸው በየሁለት ሳምንቱ ደግሞ ለዲፓርትመንታቸው ሪፖርት የሚያደርጉበትና ለዚሁ ውጤታማነት እንዲያግዝ ተብሎ በእያንዳንዱ ቤተ-መጽሓፍት ውስጥ የቡድን ሥራ የሚካሄድበት አንድ ሰፊ ክፍል ተዘጋጅቶ በጥቅም ላይ እንዲውል የተደረገ መሆኑን ጠቅሰው በዚህ አግባብ በመሠራቱም ተማሪዎችና መምህራን ከጊዜ ወደ ጊዜ ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን በተለያዩ ወቅቶች በተደረጉ ደሰሳዊ ጥናቶችና በተማሪዎች ውጤት መሻሻል መረጋገጣቸውን ገልጸዋል።

የዩኒቨርሲቲዎች 2008 . የሥራ አፈፀፀ ምዘና አጠቃላይ ሪፖርት የከፍተኛ ትምህርት የእንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ደሳለኝ ሳሙኤል እና 26ኛው የትምህርትና ሥልጠና ጉባኤ ወቅት ከከፍተኛ ትምህርት አንጻር በተናጥል የዘርፎች ጉባኤና ሦስቱም የትምህርት ዘርፎች በተሳተፉበት በዋናው ጉባኤ 2009 በጀት ዓመት በትኩረት አቅጣጫነት ተለይተው እንዲፈጸሙ የተቀመጡ ነጥቦች ሪፖርት የከፍተኛ ትምህርት አስተዳደራዊ ጉዳዮች ጀነራል ዳይሬክቶሬት ባለሙያ በሆኑት በአቶ ሳሙኤል አስመላሽ ቀርበዋል።

በመጨረሻም የኮሪያ እድገት ተሞክሮና ከእድገታቸው ጋር ተያይዞ ስለተከሰተባቸው ማህበራዊ ችግሮችና ችግሮቹን ለመፍታት እየተወሰዱ ስላሉ መፍትሔ እርምጃዎችን የሚመለከት ገለጻ ከኮሪያ በመጡ ልዑካን ቡድን ቀርበዋል። የተሞክሮው የመጀመሪያ ክፍል ኮሪያ ከነበረችበት ድህነት ተላቃ አሁን ያለችበት ደረጃ ላይ ለመድረስ ያለፈችበት ውጣ-ወረዶች የቀረቡበት ሲሆን ሁለተኛው ክፍል ከማደጓ ጋር ተያይዞ ስለተከሰተባት ማህበራዊ ችግሮችና እሱን ለመፍታት በመውሰድ ላይ ያለችው የመፍትሄ እርምጃዎች የቀረቡባቻው ናቸው።

ገለጸውን የተከታተሉ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ሀገራችን በአሁኑ ወቅት ተከታታይነት ያለው ፈጣን እድገት ማስመዝገብ የጀመረች ሀገር ብትሆንም ከነበረችበት የድህነትና ኃላ ቀርነት ደረጃ የተነሳ ከድህነት ጋር ሙሉ ለሙሉ ለመላቀቅ ረጅም ርቀት መጓዝ የሚጠበቅብን እንደመሆኑ መጠን በክፍል አንድ ገለጻ የቀረበው የእድገት ተሞክሮ ለሚቀረን ረዥም የሆነ ቀሪ የእድገት ጉዞኣችን ይጠቅመን ዘንድ ከራሳችን ተጨነባጭ ሁኔታ ጋር አስማምተን ብንጠቀም ጥሩ መሆኑን ጠቅሰው  ሀገሪቷን ከእድገት በኋላ ያጋጠማትም ማህበራዊ ቀውስ ችግሮችን ለምፍታት እየወሰደች ያለውን እርምጃዎችን (ለህጻናትና ለወጣቶች ”Mind seting Education” መስጠት ወይም ራስን የመግዛት) ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር አስማምተን ብንጠቀም ችግሮች ሳይከሰቱ ወይም ሳይገዝፉ በፊት አስቀድመን ለማከላከል ዕድል ስለሚሰጠን ተሞክሮው ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ተደራሽ ከመሆኑም በላይ በመደኛ የትምህርት ሥርዓታችን በሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት ውስጥ ተካቶ የሚሰጥበት ሁኔታ ብፈጠር መልካም መሆኑን ገልጸዋል።

በቀረቡ የዩኒቨርሲቲዎች ሪፖርት  ላይ ተሳታፊዎች እንዲወያዩ በተሠጠው እድል መሠረት ሪፖርት አቅራቢዎች የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዙ በግብዓትነት የሚወሰዱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ዘርፍ ሪፎም ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር የሆኑት አቶ ኤሊያስ ግርማ በበኩላቸው ከተሳታፊዎች ለተጠየቁ ጥያቄዎች መልስ የሰጡ ሲሆን ለአብነት ያክል ለለውጥ /ቤት መዋቅሩ መሰጠት ስላለበት የአቅም ግንባታ ሥልጠናን እና የኮሪያ ልዑካን ቡድን ያቀረበውን ተሞክሮ ተደራሽነት በሚመለከት ተጠይቀው እንዲህ በማለት መልሰዋል። በመዋቅሩ ውስጥ የነበሩ አካላትን ለማጠናከርም ሆነ አዳዲስ ወደ መዋቅሩ የመጡትን አካላት አቅም ለመገንባት አግባብነት ባላቸው ርዕሶች ላይ ከዩኒቨርሲዎችም ሆነ ከትምህርት ሚኒስቴር አሠልጣኞችን በማዘጋጃት ሥልጠናዎች የሚሰጡ መሆኑንና ሚኒስቴር /ቤቱ የኮሪያ ልዑካን ቡድን የሚያቀርቡት ተሞክሮ በሁሉም የዩኒቨርሲቲዎች በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንዲዳረስ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ወደቴግባር ለመግባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ጠቅሰው ሥራውን  በፕሮግራሙ መሠረት በሚፈለገው መልኩ ለማሳከት  እንዲቻል የዩኒቨርሲቲዎች ትብብርም ወሳኝነት እንዳለው አሳስበዋል። 

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት ክቡር / ሳሙኤል ክፍል በመድረኩ ተገኝተው ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ምላሽና ማብራሪያ  ከተሰጣቸው ነጥቦች ማካከል የሚከተሉትን ለአብነት ማንሳት ይቻላል። የዩኒቨርሲቲዎች የለውጥ /ቤት አደረጃጀትን መልሶ ማየት የሚያስፈልገው ስለመሆኑ፣ለጽ/ቤቱ ኃላፊዎች አግባብነት ባላቸው የሥልጠና ርዕሶች ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና የሚያስፈልግ ስለመሆኑ፣ጽ/ቤቱ በሚፈለገው የሰው ኃይልና ቁስቁስ መሟላት ያለበት ስለመሆኑ፣ የለውጥ ሥራው የዩኒቨርሲቲ የበላይ አመራሮችና በየደረጃው ያሉ አመራሮች በፕሮጀክትነት ልይዙት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አውስተው በሚገባ ተግባራዊ ሆኖ ውጤት እንዲያመጣ የአመራር አካላት ሥራውን በባለቤትነት መያዝ የሚገባቸው መሆኑንና በተቋም ደረጃ ይህንን ሥራ ለሚከታተልና ለመደገፍ ለተቋቋው /ቤትም የሚገባውን አውቅናና ክብር በመስጠት ማበርከት ስለሚጠበቅባቸው ድጋፍና ትብብር፣የመምህራን ዝውውር በጥንቃቄ መካሄድ ያለበት ጉዳይ መሆኑን፣ ከአንድ በላይ ተቋማት ላይ ተቀጥረው የሚሠሩ መምህራን የተስተዋሉ መሆኑንና ይህም ወንጀል ስለመሆኑ፣የሴቶች ተማሪዎችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የተዘረጉ ሁሉንም የድጋፍ ማዕቀፎችን ተግባራዊ ማድረግ የሚገባ ስለመሆኑ፣ሴቶችን ወደ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ ማምጣጥ ትኩረት ተሰጥቶት ተጠናክሮ መሠራት ያለበት ጉዳይ ስለመሆኑ እና የመሳሰሉት  ከለውጥ ሥራ ጋር ተያያዥነት ያላቸውና የሌላቸው ሁለንተናዊ ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸው መድረኩ ፍጸሜውን ሊያገኝ ችሏል።


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡