የሂሳብና ሳይንስ ትምህርቶችን ጥራት ለማሻሻል የሚረደ ስልጠና ተሰጠ

የሂሳብና ሳይንስ ትምህርቶችን ጥራት ለማሻሻል የሚረደ ስልጠና ተሰጠ

በትምህርት ሚኒስቴር የሂሳብና ሳይንስ ትምህርቶች ማሻሸያ ማዕከል ከሁሉም ክልሎች ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ከሥራቸው ጋር አግባብነት ባላቸው ሪዕሶች ላይ ሥልጠና ሰጠ፡፡

ሥልጠናው የተሰጠው ከታህሳስ 17-19/2009. በአደማ ከተማ ሲሆን የዚህ የሂሳብና ሳይንስ ትምህርቶች ማሻሸያ የሥራ ላይ ሥልጠና ዋነኛ ዓለማው ርዐሰነ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ለመምህራን በእውቀት ላይ የተመሠረተ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ከማስተማር ጋር የተያያዙ ችግሮችን ለመፍታት እንደሆነ የማዕከሉ ኃላፊ የሆኑት አቶ በላይነህ ተፈራ ገልጸዋል።

የሥልጠናው ርዕሶች፦ የትምህርት እቅድ ይዘት፣የትምህርት ጥናት (Lesson Study) ምንነትና አስፈላጊነት እንዲሁም አተገባበር፣የክፍል ምልከታ ቼክሊስት ይዘትና አጠቃቀም እና የሂሳብና ሳይንስ ትምህርቶች የሥራ ላይ ሥልጠና መመሪያ ይዘት፣ አጠቃቀምና ትግበራ ናቸው።

 የሥልጠናውን ፋይዳዎች በሚመለከት ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በእውቀት ላይ የተመሠረተ ክትትል፣ ድጋፍ፣ግምገማና ግብረ-መልስ ለመምህራን በመስጠት በመማር ማስተማር ሂደት የሚከሰቱ ችግሮች በወቅቱ ተለይተው የሚፈቱበትን ምቹ የትምህርት አከባቢን ለመፍጠር የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡