ሀገራችን ያስቀመጠችው ራዕይ ለማሳካት በተግባር ልምምድ የተደገፈ የጎልማሶች ትምህርት መሰጠት ያስፈልጋል

ሀገራችን ያስቀመጠችው ራዕይ ለማሳካት በተግባር ልምምድ የተደገፈ የጎልማሶች ትምህርት መሰጠት ያስፈልጋል

በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ማስተባበሪያ ከዲቪቪ ኢንተርናሽናል ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ከተማ ከታህሳስ 11-12/2009 . በጎልማሶች ትምህርት ላይ ባዘጋጀው ሲምፖዚየም ሀገራችን ያስቀመጠችውን ራዕይ ለማሳካት በተግባር ልምምድ የተደገፈ የጎልማሶች ትምህርት ሊሰጥ እንድሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡

የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ሆሄያትን የማስቆጠር ብቻ ሳይሆን ማንበብና መፃፍ የማይችል ዜጎች በችግሮቻቸው ዙሪያ በመወያየት የህይወት ክህሎት   ለማሻሻል፣ የግልና የጋራ ፍላጎትን ያካተተ ቃላት፣ ሀረግ ዐረፍተ ነገር እንዲሁም ቁጥሮችን በማንበብና በማስላት ላይ የተመሰረተ ተግባር ነው፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ አዳነ ማሞ ሲምፖዚየሙን በንግግር ሲከፍቱ እንደተናገሩት የሲምፖዚየሙ ዋና ዓላማ  በአራተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መረሃ ግብር እቅድ መሰረት ያልተከናወኑ ተግባራት በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ታስቦ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ አዳነ ገለፃ ባለፉት አመታት የተመዘገቡ ውጤቶች አበረታች ቢሆንም በየደረጃው የሚገኙ የጎልማሶች ትምህርት አደረጃጀት በተቀመጠው የትምህርት ልማት መርሃ ግብር መሰረት ስራዎችን በሚፈለገው ደረጃ  ለማከናወን  ክፍተቶች   መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡

ጎልማሶች ለጋራ ችግሮቻቸው የጋራ መፍትሄ የሚሹበት የግል እውቀታቸውንና ልምዶቻቸውን እንዲሁም  ክህሎታቸውን ለጋራ ልማት  ወደተሻለ ህይወት እንዲሸጋገሩ ለማድረግ የትምህርት መርሃ ግብሩ ይዘት በአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታን መሰረት ያደረግ እንዲሆንም አቶ አዳነ አስገንዝበዋል፡፡

አቶ አዳነ አክለው በመደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ሂደት ውስጥ መምህራን ለትምህርት ጥራት ማሻሻል ቁልፍ ሚና እነደሚጫወቱ ሁሉ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥም የተቀናጀ የህይወት  ክህሎት ጋር አዋህዶ    ለማቅረብ አመቻቾች የማይተካ ሚና እንዳለቸው ጠቅሰዋል፡፡

ኃላፊው እንደ ገለጹት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን የዕድገት አቅጣጫ ለማሳካት የበኩሉን አስተዋጽኦ ልያበረክት የሚችል ከተግባር ልምምድ ጋር የተገናኘ የትምህርት አቀራረብ መከተል እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡ የጎልማሶች ትምህርት ለፕሮግራሙ  ወጥነት ባለው መልኩ ለማሳለጥ መማማሪያ ማዕከላት  እንዲቋቋሙ የህብረተቡ የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዘለዓለም አላጋው የጎልማሶች ትምህርት ያለበትን ደረጃ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ፕሮግራም በመንግስት ትልቅ ትኩረት በሁሉም ክልሎች መተግበር የጀመረው በአራተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር አፈጻጸም ውሰጥ ሲሆን ለወደፊት በስራ አፈጻጸም ሂደት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ በቀሪው  የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር ውስጥ  የተሻለ  ውጤት ለማምጣት ትምህርት ቤቶችን መሰረት ያደረገ የገጠር ትራንስፎርሜሽን ፓኬጅ  መከተል እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

በዲቪቪ ኢንተርናሽናል  የምስራቅ አፍሪካ ቀንድ /ቤት ዳይሬክተር / ሱንያ በለቴ እንዳሉት ዲቪቪ ኢንተርናሽናል በሀገር አቀፍ የተያዘውን የትምህርት  ልማት መርሃ ግብር ስኬት ለመደገፍ ከፌዴራል እስከ ክልል በጎልማሶች ትምህርት ላይ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ይህ  ሲምፖዚየም በጎልማሶች ትምህርት ያለበት ሁኔታ ተለይቶ ለችግሮች መፍትሔ  በተለያየ ጊዜ የልምድ ልውውጥ፣ አውደ ጥናቶች መካሄዳቸውን በመጠቆም  የዕለቱ  ሲምፖዚየም ለቀጣይ ስራዎች የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ  የጎላ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች ባቀረቡት አስተያየት መሰረት ክልሎች የጎልማሶች ትምህርት ተሳትፎን ለማሳደግ  በርካታ የአመለካከት ችግሮች ያጋጠማቸው መሆኑን ጠቅሰው እንነዚህን ተግዳሮቶች ለማቃለል  በጎልማሶች ትምህርት ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ መማማሪያ ማዕከላትን እንዲሁም የትምህርት ይዘቱም   ላይ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በባለድርሻ አካላትና በጎልማሶች ትምህርት አመቻቾች አማካይነት መሰጠት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡  

በሲምፖዚየሙ ከዘጠኙም ክልሎችና  ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም   ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡