በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራሮች ምልመላና ምደባ ረቂቅ መመሪያ ላይ የሚመክር አውደ-ጥናት ተካሄደ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራሮች ምልመላና ምደባ ረቂቅ መመሪያ ላይ የሚመክር አውደ-ጥናት ተካሄደ

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የአመራር ምልመላና ምደባን በሚመለከት በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ላይ የሚመክር አውደ-ጥናት በኢ... ትምህርት ሚኒስቴርና በከGIZ ኢትዮጵያ ትብብር ተዘጋጅቶ ታህሳስ 6/2009. በአዲስ አበባ ከተማ በካፒታል ሆቴል ተካሄደ። የትምህርት ሚኒስቴር  ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር / ሳሙኤል ክፍሌ በወቅቱ ከጋዜጠኞች ጋር በካሄዱት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት ታክስ ፎርሱ ረቂቅ  መመሪያውን  በትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው ኃላፊነት መሠረት  ከትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ እና ከከፍተኛ ትምህርት አዋጅ በተጨማሪ  እስከ አሁን ከነበረን አሠራርና ከሌሎች ሀገራት ጠቃሚ ልምዶችን በመውሰድ ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ያዘጋጀ  መሆኑን ጠቅሰው የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያም በትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲው እና በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ውስጥ  በተበታተነ መልኩ የተጠቀሱ መመሪያ -ነክ ይዘቶችን በተቀነጃና ወጥነት ባለው መልኩ በአንድ ሰነድ አሰባስቦ ተግባራዊ ለማድረግ በሚያመች መልኩ የማዘጋጀት ያህል ከነባር አሠራራችንና ሰነዶቻችን ጋር የማይፈለስ ይዘት ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

 

ረቂቅ መመሪያውን  የዘጋጀው ተክስ ፎርስ አስተባባሪ የሆኑት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት / ጀይሉ ኡመር በቀጣይ ጊዜያት ይህ መመሪያ በተለያዩ ባለድርሻ አካላት ግብዓት ዳብሮ ከጸደቀ በኋላ ከድፓርትሜንት ኃላፊዎች እስከ  ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች ያሉትን አመራሮች ለመምረጥና ለመመደብ ለየኃላፊነት ደረጃ የተቀመጠ  የትምህርት ዝግጅት፣ የሥራ ልምድና እንደየሙያቸው ያስመዘገቡት ውጤት በመስፈርትነት ተወስዶ የሚሠራበት መሆኑን  ጠቅሰው  መመሪያውም  ወጥነት ባለው መልኩ በሁሉም  ዩኒቨርሲቲዎች  በፍትሃዊነት ተግባራዊ  የሚሆን ስለሆነ ብቃት ያላቸውን አመራር ወደ ኃላፊነት በማምጣት ከዚህ ረገድ ሊስተዋሉ የሚችሉ ክፍተቶችን በማጥበብ በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ለተያያዘችው መልካም አስተዳደር የማስፈን ሥራና የትምህርት ጥራትን የማሻሻል  ሥራ ስኬታማ እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ገልጸዋል። / ጀይሉ አክለውም  አሠራሩ በመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት  ያሉ አመራሮች ሁለንተናዊ ብቃታቸውን  በማሳደግ የተቋማቸውን አፈጻጸም  ውጤታማ እንዲያደርጉ የሚያግዝ ተገቢ አሠራር መሆኑንም ተናግረዋል።

 

 አንዳንድ የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አሰተያት እስከ አሁን በነበረው አሠራር በዩኒቨርሲቲዎች ስካሄድ የነበረው የአመራር ምልመላና ምደባ መሥፈርት  መሠረታዊ ሊባል በሚችል ደራጃም ባይሆን ለግለሰቦች አረዳድና ግንዛቤ የተጋለጠ በመሆኑ ምክንያት ከዩኒቨርሲቲ- ዩኒቨርሲቲ ልዩነት እንደነበረው በማስታወስ  መመሪያው ወጥነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ሲሆን እነዚህንና መሰል ችግሮችን እንደሚቀርፍ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡