የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋማዊ ለውጥ ምክር ቤት ጉባኤ በሠመራ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት በሠመራ ከተማ ተካሄደ

የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋማዊ ለውጥ ምክር ቤት ጉባኤ በሠመራ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት በሠመራ ከተማ ተካሄደ

 33ኛው  የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋማዊ ለውጥ ምክር ቤት ጉባኤ አንደተለመደው የተካሄደው  ከህዳር 2-4/2009 ሲሆን  26ኛው የትምህርትና ሥልጠና ጉባኤ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስተናጋጅነት  በሠመራ ከተማ ከህዳር 5-6/2009 . ከመካሄዱ ቀደም ብሎ  ሦስቱም የትምህርትና ሥልጠና ዘርፎች በተናጥል ባካሄዱት መድረክ ነበር። ጉባኤው የተጀመረው  አስተናጋጅ  የሆነችው የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቶ አደም ቦሪ የእንኳን  ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው ውስጥም የሚከተሉትን መልዕክት አስተላልፈዋል።  የለውጥ ምክር ቤት ጉባኤው ተቋማት በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዙሪያ  ከጊዜ ወደ ጊዜ እያስመዘገቡ የመጡትን  ለውጦችና የወደፊት ውጥናቸውን  የሚጋሩበት የጥሩ ተሞክሮዎች  መቅሰሚያ መድረክ ሆኖ  በማገልገል ላይ ያለ መድረክ መሆኑን ጠቅሰው  በተለይ በመሠረታዊ  አገልግሎት አሠጣጥ ዙሪያ ተቋማት ራሳቸውን እንዲፈትሹ እድል የሰጠና  እና ከሀገራዊ ተልዕኮዎች አልፈው ዓለም አቀፍ ተልዕኮዎች እንዲወጡ የሚያስችላቸውን አቅም እንዲያካብቱ  እያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት መድረኩ እየሰጠ ካለው ፋይዳ አንጻር  ዩኒቨርሲቲዎችን በጋራ ከሚያሰባስቡ መድረኮች መካከል ዋነኛና በላጭ መሆኑንም ገልጸዋል።

 

የሠመራ የኒቨርሲቲ  የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳብ እና የፌዴራልና አርብቶ አደር አከባቢ ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አወል ወግሪስም በተመሳሳይ መልኩ ባደረት  የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው ውስጥ የሚከተሉትን መልዕክት አስተላልፈዋል። መንግሥት የህዝቡን የትምህርት ጥማት ለማርካት ስል ተደራሽነቱን በማስፋት፣ አግባብነቱንና ጥሩትንም ለማሻሻል የሰጠው ትኩረትና በተጨባጭ እያደረገ ያለው ጥረት የሚደነቅና አበረታች መሆኑን ጠቅሰው ዩኒቨርሲቲዎች በየአከባቢውና በየክልሎች መቋቋማቸው በተለይ የአርብቶ አደሩ ህዝባችን ሴት ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ፣የአከባቢው  ማህበረሰብም ሆና ሠራተኛው በተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር የትምህርት ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ አድል የሰጠ መሆኑን ገልጸዋል። በዩኒቨርሲቲዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጠው የተማሪ ቅበላችን በአገልግሎት አሰጣጣችንና ከዚሁ ጋር ጥብቅ ቁርኝት ካለው የመልካም አስተዳደር ጉዳይ  ላይ የሚያሳርፈው ጫና ቀላል ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት ተሠጥቶት ሊሠራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው  በዚህም ሆነ በሌሎች ሁለንተናዊ ሴኬቶችን ማስመዝገብ ይችሉ ዘንድ ዩኒቨርሲቲዎች ከማህበረሰባቸውንም ሆነ ከአከባቢያቸው ማህበረሰብ ጋር ያላቸውን ትስስር የበለጠ ማጠናከርና በቅርበት መሥራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

 

የቀደሞው የኢ... ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ (ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ) የሆኑት  ክቡር / ካባ ኡርጌሳ በመክፈቻ ንግግራቸው የሚከተሉትን መልዕክቶች አስተላልፈዋል። ባለፉት ሁለት  አሥርት ዓመታት መንግሥት ለህዝባችን ትምህርትን ለማዳረስ ከፍተኛ ሥራ ሥሠራ መቆየቱንና በዚህም የተነሳ ከጊዜ ወደ ጊዜ ዩኒቨርሲቲዎቻችንን አመታዊ የተማሪዎች ቅበላችንን እየጨረ መምጣቱን ጠቅሰው ይህም ውጤት ቀድሞ ከነበረን አቅም አንጻር ሲታይ በማንኛውም መስፈርት እጅግ በጣም ከፍተኛ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል። ክቡር / ካባ አክለውም መንግሥት ትምህርትን ከማስፋፋት ጎን ለጎን ጥራቱንም ለማስጠበቅ በሰጠው እጅግ በጣም ከፍተኛ ትኩረት  በመምህራን ልማት፣የትምህርት ጥራትን የሚያስጠብቁ የመማር ማስተማር ሥራዎችን በማከናወን፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ  መሠረተ ልማትን በመገንባትና ሌሎችንም ለትምህርትና ለምርምር ሥራዎች አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት የድርሻውን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተናግረው ነገር ግን የትምህርት ልማት ሥራ የበርካታ በለድርሻ አካላት ተሳትፎን የመፈለጉን ያህል ሁሉም የባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

 

 ባለፉት አመታት የዩኒቨርሲቲዎችን አጠቃላይ ማህበረሰብ በማሳተፍ የተሰጡ የሥልጠና ፕሮግራሞችና በሥልጠናው ወቅት ከማህበረሰቡ የተነሱትን የመልካም አስተዳደር ጉደለቶችንና መንስኤዎችን በመለየትና ለጉድለቶቹ ባለቤት በመስጠት ለማረም በተደረጉ ጥረቶች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ የተቻለ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ውጤት እንዲመዘገብ የየድርሻቸውን ላበረከቱ ዩኒቨርሲቲዎች እና በተለይም 2008 . በኦሮሚያና በአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥታት በተወሰኑ አከባቢዎች ላይ የተከሰተው አለመረጋጋት በአከባቢው ወደሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተስፋፍቶ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዳያስተጓግል ኃላፊነታቸውን የተወጡትን በየደረጃው ያሉ የዩኒቨርሲቲ አመራሮችን፣ የተማሪዎች ህብረትን፣ መላ የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ፣ የአካባቢውን ህብረተሰብ፣የአከባቢውን የአስተዳደር አካላትና የጸጥታ ኃይሎችን አመስግነዋል፡፡

 

ሥራዎችን ሁሉ በለውጥ ሠራዊት አግባብ በመንቀሳቀስ ለመሥራት የሚደርገውን ጥረት በተመለከተ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች አደረጃጀቶች ተፈጥረው ወደ ሥራ በመግባት ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን ጠቅሰው እነዚህ የጀመረናቸው የለውጥ ሥራዎች በሚፈለገው  ደረጃ ላይ እንዲደርሱ አሁንም ብሆን በአስተሳስብ ለውጦች ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ መሠራት የሚገባ መሆኑንና ይህንንም በሚፈለገው ደረጃ ለማሳካት የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝንዳቶችና የአስተዳደር ቦርድ አመራሮች የመሪነት ሚና ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

 

2008 በጀት አመት እቅድ በቁልፍነት ከተያዙት ሥራዎች መካከል የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት፣ኪራይ ሰብሰቢነትትን በአመለካከትና ተግባር ደረጃ ማክሰም እና የትምህርት ጥራትን የሚያስጠብቁ ወሳኝ ሥራዎችን መሥራት ዋና ዋናዎቹ መሆኑን ጠቅሰው እነዚህንም ለማሳካት በተሠሩ ሥራዎች ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበ ቢሆንም የሚፈለገው ደረጃ ላይ መድረስ እንዳልተቻለ ገልጸዋል። ከነዚህ ጉዳዮች አንጻር በሚፈለገው ደረጃ ውጤት ለማስመዝገብ እንዲቻል ዩኒቨርሲቲዎች በውስጣቸው በሚያከናውኗቸው ሥራዎች ለአከባቢው ማህበረሰብ አርኣያ ሆኖ ለመገኘትና በአከባቢያቸው ያሉ ትምህርት ቤቶችም አርኣያ እንድሆኑ ከፍተኛ ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል። ክቡር / ካባ አክለውም በሁሉም ደረጃ የሴቶችንና የአካል ጉዳተኞችን ተሳትፎ ለማሳደግ የተጀመረው ጥረት 2009 በጀት አመት የበለጠ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና በተለይ የሴቶች ተሳትፎ  በመምህርነት፣ በተመራማሪነትና በመሪነት ደረጃ እንዲያድግ ልዩ ትኩረት ተሠጥቶት መሠራት የሚገባው ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።

 

ክብር ሚኒስትር ዴኤታው የሚቀረጹ አዳዲስ ሥርዓተ-ትምህርቶችና በአዲስ መልክ የሚከፈቱ የትምህርት ፕሮግራሞች ከሀገሪቷ  የልማት ፍላጎት አንጻር አግባብነት ያላቸው መሆናቸው በትምህርት ሚኒስቴር እየተረጋገጠ ይሁንተ አግኝቶ ተግባራዊ እንዲሆን አቅጣጫ የተቀምጦለትና መመሪያ ተዘጋጅቶለት 2008 በጀት አመት እቅድ ተይዞ ስሠራ የነበረ መሆኑን ጠቅሰው በአብዛኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች የተተገበረው በተቀመጠው አቅጣጫና እቅድ መሠረት መሆኑንና በዚህም በመጀመሪያ፣በሁለተኛና በሦስተኛ ድግሪ በአጠቃላይ 51 የትምህርት ፕሮግራሞች አግባብነታቸው በትምህርት ሚኒስቴር ተረጋግጦ ወደ ሥራ እንዲገቡ የተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ 2008 በጀት አመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት፣የ2009 በጀት ዓመትና የአንደኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የሱፐርቪዥን የመስክ ምልከታ ሪፖርትና ዩኒቨርሲቲዎች በሦስት ቡድን ተከፍለው በትይዩ መድረክ ያቀረቡት ጭማቂ ሪፖርት ቀርበው ውይይት ተካሄዶባቸዋል።

 

በጉባኤው ማገባደጃ እንደተለመደው 2008 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸምን መሠረት በማድረግ ዩኒቨርሲቲዎችን በሦስት ትውልድ በመክፈል የተሠራ የሥራ አፈጻጸም ደረጃ ይፋ ሆኗል። በዚህም መሠረት ከየትውልዱ 1 እስከ 3 ደረጃ ያገኙ ዩኒቨርሲቲዎች የሚከተሉት ሲሆን 26ኛው አገር አቀፍ የትምህርትና ሥልጠና ጉባኤ ተሸልመዋል።

 

ከመጀመሪያ ትውልድ 1 ደረጃ ያገኛው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ጅማና ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በቅደም ተከተላቸው 2ኛና 3 ደረጃን አግኝተዋል። ከሁለተኛው ትውልድ 1 ደረጃ ያገኛው ደብረብረሃን ዩኒቨርሲቲ ሲሆን ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 2 ያገኘ ሲሆን ወላይታ ሶዶና ወሎ ዩኒቨርሲቲ እኩል ነጥብ በማምጣት 3 ደረጃን አግኝተዋል። ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች በቅደም ተከተላቸው 2ኛና 3 ደረጃን አግኝተዋል። ከሦስተኛው ትውልድ 1 ደረጃ ያገኛው ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ሲሆን አዲግራትና ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች በቅደም ተከተላቸው 2ኛና 3 ደረጃን አግኝተዋል።

 

በመጨረሻም ጉባኤው ከዘጠኙ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ስትራቴጂክ ዓለማዎች ጋር ቁርኝት ያላቸውን ባለዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ፍጻሜውን አግኝቷል።  


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡