በመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች አሰለጣጠንና የመምህራን ገዥ መመሪያ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማሻሻል በተሰራ ጥናት ላይ ግብአት እየተሰበሰበ ነው

በመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች አሰለጣጠንና የመምህራን ገዥ መመሪያ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማሻሻል በተሰራ ጥናት ላይ ግብአት እየተሰበሰበ ነው

በመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች አሰለጣጠንና የመምህራን ገዥ መመሪያ ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማሻሻል ትኩረት ተደርጎ በተካሄደው ጥናት ላይ ግብአት ለማሰባሰብና የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ 

 

በዚህ መድረክ 250 የሚሆኑ በሃገሪቱ ከሚገኙ 22 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ፕሬዚዳንቶችና ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ 36 የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ዲኖች፣ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ትምህርት ቢሮ የተውጣጡ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ከሚኒስቴር /ቤቱ ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተወከሉ ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች እየመከሩ ይገኛሉ፡፡

 

የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር / ጥላ ጌቴ የምክክር መድረኩን በንግግር ሲከፍቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍን አሰራርና አደረጃጀት በማሻሻል፣ ስትራቴጂን በመቀየስና ምርምሮችን በማካሄድ ሃገሪቱ በምትፈልገው ደረጃ የትምህርት ስርዓቱን ተከትሎ በዘርፉ የተማረ የሰው ሃይል ለማፍራት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

 

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድና በአምስተኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር በተጣተሉ ግቦች መሰረት እየተተገበረ እንደሚገኝ የጠቆሙት / ጥላዬ፤ በሃገራችን የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች አሰለጣጠንና አመላመል እንዲሁም የመምህራን ገዥ መመሪያ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት የመፍትሄ ሃሳቦች ለማሰባሰብ እንዲያስችል ከሚመለከታቸው የትምህርት አመራር አካላትና ባለሙዎች ጋር በተደረው ስምምነት መሰረት 2008 . ጀምሮ ጥናት ተካሂዶ መጠናቀቁንና ጥናቱ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻልና የመምህራንን ብቃት ለማሳደግ ሚናው የጎላ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡  

 

ጥናቱ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ መነሻ በማድረግ እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያት በተካሄዱ ውይይቶች መሰረት በተገኘ ግብአት የተጠናና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው የመድረኩ ተሳታፊዎች የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች አሰለጣጠንና አመላመል እንዲሁም የመምህራን ገዥ መመሪያ ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን በመፈተሸ በጥናቶቹ ላይ ሙያዊ አስተያየት እና ዘላቂ ለውጥ ለማምጣጥ የሚያስችል ግብአት እንደሚሰጡ እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡

 

በመድረኩ ሶስት ጥናቶች የቅድመ መደበኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን አሰለጣጠን ፕሮግራም፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን አሰለጣጠን ፕሮግራም እንዲሁም የትምህርት አመራር አሰለጣጠን ፕሮግራም ቀርበው ውይይት እየተካሄደባቸው ይገኛል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡