አራተኛው ሃገር አቀፍ የትምህርት ዘርፍ የታዳጊ ሴት ልጆች ቀን በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ተከበረ

አራተኛው ሃገር አቀፍ የትምህርት ዘርፍ የታዳጊ ሴት ልጆች ቀን በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ተከበረ

አራተኛው ሃገር አቀፍ የትምህርት ዘርፍ የታዳጊ ሴት ልጆች ቀን በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ተከበረ

በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት አራተኛውን ሃገር አቀፍ የትምህርት ዘርፍ የታዳጊ ሴት ልጆች ቀን በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም በአማኑኤል ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ባከበረበት ወቅት የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ይሁኔ ጌታቸው ባደረጉት ንግግር የሴቶችን የትምህርት ተሳትፎ ውጤታማነት ለማሳደግ ልዩ ዕገዛ በመደረጉ የሴት ተማሪዎች ቁጥር ከመጨመሩም በላይ ውጤታማነታቸውም ከወንዶች የተሻለ ሊሆን ችሏል ብለዋል፡፡

 

በትምህርት ቤቱ የሴቶች ተሳትፎና ውጤታማነት ሊጨምር የቻለው የተለየ የማጠናከሪያ ትምህርት የስነ ተዋልዶና የጤና ትምህርት በመስጠት፣ የሚደርስባቸውን ፆታዊ ጥቃት ለመቋቋም የሚያስችላቸውን ግንዛቤ በመፍጠር፣ የምክር አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የሴት ተማሪዎችን ክበብ በማጠናከር እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ችግር ላለባቸው ሴቶች የገንዘብና የመማሪያ ቁሳቁሶችን በመስጠታቸው እንደሆነ ርእሰ መምህሩ አብራርተዋል፡፡

 

2007 . ጀምሮ በትምህርት ቤቱ የሴት ተማሪዎች ክበብ ተጠናክሮ ስራ መጀመሩ የሴት ተማሪዎች ንቃተ ህሊና እንዲዳብር ማድረጉንም አቶ ይሁኔ ገልፀዋል፡፡

 

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት የስርጻተ ፆታ ጉዳዮቸ ክትትልና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ እስክንድር ላቀው በዓሉን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት በአለም ለአምስተኛ ጊዜ በሃገራችን ደግሞ ለአራተኛ ጊዜ "ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በማስቆም የታዳጊ ሴቶችን ተሳትፎና ብቃት ለማረጋገጥ የገባነውን ቃል እንጠብቅ!" በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን አለም አቀፍ የታዳጊ ሴት ልጆች ቀን ማክበር ያስፈለገበት ዓላማ በሴቶቸ ላይ የሚደረጉ ጎታች ልምዶችን በመቅረፍ የትምህርት ተሳትፎአቸውን ለማጎልበትና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ህብረተሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ ግንዛቤ ለመፍጠር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

 

በሴት ልጆች ላይ የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶችን በመከላከል ጤንነታቸውና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ለትምህርታቸው የሚያስፈልጋቸው ቁሳቁስ ተሟልቶ እንዲማሩና ውጤታማ እንዲሆኑ ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አቶ እስክንድር አስገንዝበዋል፡፡

 

በስርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት የሥልጠናና አቅም ግንባታ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት / የሻረግ ነጋሽ በበኩላቸው በሴትነታቸው ከሚደርስባቸው ጥቃት እንዲታደጉ የሴቶች የትምህርት ተሳትፎ እንዲያድግ ከተሳትፎም ባለፈ የሴት ተማሪዎች የዕውቀት ማዕድ እንዲጠናከር በማድረግ የሃገሪቱን የህዳሴ ጉዞ ለማስቀጠል ወሳኝ ሚና እንዳላቸው ባቀረቡት ፅሁፍ ተንትነው አሳይተዋል፡፡

 

በአማኑኤል ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት የሴት ተማሪዎች ክበብ ሃላፊ የሆነችው ተማሪ ባህሪ ምንይችል ክበቡ የቅያሬ ዩኒፎርም፣ የተለያዩ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች የተለያዩ አገልግሎቶች በማዘጋጀት ሴት ተማሪዎች ሳይቸገሩና የትምህርት ጊዜያቸው ሳይስተጓጎል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ምቹ ሁኔታ እንደተፈጠረላቸው ገልፃለች፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡