"የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተጣለበትን ብቁ የሰው ሃይል የማፍራት ተልእኮ እያሳካ ነው"

"የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተጣለበትን ብቁ የሰው ሃይል የማፍራት ተልእኮ እያሳካ ነው"

"የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተጣለበትን ብቁ የሰው ሃይል የማፍራት ተልእኮ እያሳካ ነው"

የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ሃገራችን የጀመረችውን የህዳሴ ጉዞ ለማሳካት የተጣለበትን ብቁ የሰው ሃይል የማፍራት ተልእኮ ማሳካት እንደቻለ የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትር አስታወቁ፡፡

የትምህርት  ሚኒስትሩ ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም "የትምህርትና ቴክኖሎጂ ልማት ሰራዊት ግንባታ ለትምህርትና ስልጠና ጥራት፣ ለሰላምና ለልማታችን"  በሚል መሪ ቃል በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ የተካሄደውን 26 ኛውን ሃገር አቀፍ የትምህርትና ስልጠና ጉባኤ በንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት የትምህርት ስርአታችን የሃገሪቱን የልማት ፕሮግራሞች የሚያሳካ መሆኑን አስመስክሯል ብለዋል፡፡

ባለፈው የእቅድ ዘመን የቅድመ መደበኛ ትምህርትን ለማስፋፋት በመደኛ ትምህርት ቤቶች የ "" ክፍል በመክፈት እንዲሁም ህጻን ለህጻን የትምህርት ቤት ዝግጅት መርሃ ግብር በማዘጋጀት ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በመሰራቱ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ዶ/ር ሽፈራው ተናግረዋል።

"እድሜው ለትምህርት የደረሰ አንድም ህጻን ከትምህርት ገበታ ውጭ አይሆንም" በሚል በተቀጣጠለው ህዝባዊ የንቅናቄ ስራ በ2008 በጀት ዓመት ከአራት ሚሊዮን በላይ ህጻናት ወደ ት/ቤት ማምጣት መቻሉን ዶ/ር ሽፈራው ጠቅሰው ከፍትሀዊነት አንፃርም በሴቶችና በወንዶች፣ በከተማና በገጠር እንዲሁም በክልሎችና በብሄረሰቦች መካከል ይታይ የነበረው የትምህርት ተሳትፎ ልዩነት እየጠበበ መጥቷል ብለዋል፡፡

ሀገራችንን ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለማሸጋገር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ በመለስተኛና በመካከለኛ ደረጃ በልዩ ልዩ የምርትና አገልግሎት ሙያዎች የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ውጤታማ ስራ መሰራቱንም ዶ/ር ሽፈራው ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነትን ለማሳደግ በተደረገው ጥረትም ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት መግባት መቻላቸውን  የጠቆሙት ሚኒስትሩ በጥናትና ምርምር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ዘርፍ አበረታች ፈጠራዎች  ተገኝተዋል ብለዋል።

በዘርፉ በርካታ ለውጦች የመጡ ቢሆንም የትምህርት ተቋማትን ያልረገጡ ዜጎች በተለይም የልዩ ፍላጎት ያላቸውና በታዳጊ ክልሎች ያሉ ህጻናት እንዲሁም የመማር ዕድል ያላገኙ ጎልማሶችን ሙሉ በሙሉ ተጠቃሚ ማድረግ የሁሉንም ርብርብ እንደሚሻ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

የአፋር ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የሲቪል ሰርቪስና አቅም ግንባታ ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አወል አርባ በበኩላቸው ክልሉ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናትን ትምህርት እንዲያገኙ ባደረገው ርብርብ የአንደኛ የትምህርት ሽፋን ጥቅል ተሳትፎ 70 በመቶ ማድረስ መቻላቸውን ተናግረዋል ።

በጉባኤው የ2008 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ2009 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በአፈጻም የታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት በሚያስችሉ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የጋራ መግባባት ተደርሷል።  

በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን፣ ባህላዊ መገልገያ ቁሳቁሶችን የሚገልጹ ፎቶግራፎች እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆችና ግለሰቦች የተሰሩና ለአካባቢው ህብረተሰብ የሚያገለግሉ ፈጠራ ስራዎችን የሚያሳይ አውደ ርእይ ተዘጋጅቶ ጉባኤተኛው እንዲበኝ ተደርጓል፡፡

ሚኒስቴር መ/ቤቱ በአጠቃላይ ትምህርት፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች የላቀ አፈጻጸም ላመጡ ተቋማት የገንዘብ፣ ሰርትፍኬትና የዋንጫ  ሽልማቶች አበርክቷል፡፡

በመጨረሻም የትምህርትና ስልጠና ዘርፉ የተሻለ ለውጥ እንዲመጣ በሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት ዘንድ መነቃቃትን የሚፈጥር ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ጉባኤው ተጠናቋል፡፡   


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡