ኤች አይ ቪ/ ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረው እንቅስቃሴ ሁሉም ርብርብ ሊያደርግ ይገባል

ኤች አይ ቪ/ ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረው እንቅስቃሴ ሁሉም ርብርብ ሊያደርግ ይገባል

ኤች አይ ቪ/ ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረው እንቅስቃሴ ሁሉም ርብርብ ሊያደርግ ይገባል

በትምህርት ዘርፍ  የኤች ኤ ቪ/ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማስተባበሪያ ከመስሪያ ቤቱ የተለያዩ የስራ ሂደቶች ለተውጣጡ ሴት ሰራተኞች በኤች አይ ቪ/ኤድስ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡ 
የማስተባበሪያው ኃላፊ አቶ ሙሴ ተስፋው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቋሙ ሰራተኞች ለኤች አይ ቪ/ኤድስ እንዳይጋለጡ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲጠብቁ ማድረግ እንዲሁም በትምህርትና ስልጠና ተቋማት ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎችና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሚገኙ ተማሪዎች ለኤች አይ ቪ/ኤድስ እንዳይጋለጡ በማስተማር ጤናማና ብቁ ዜጋ ለማፍራት የበኩሉን እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

ስልጠናው ትኩረት ያደረገው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለተውጣጡ ሴት ሰራተኞች መሆኑን የጠቆሙት አሰተባባሪው ሴቶችን ማስተማር ህብረተሰቡን ማስተማር እንደሆነ በመገንዘብ፣ ሴቶች ለልጆቻቸውና ለቤተሰቦቻቸው ቅርብ በመሆናቸው ያገኙትን እውቀት ማካፈል እንደሚችሉ ታሳቢ ተደርጎ ነው ብለዋል፡፡

ሰልጣኞች ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫወት ይገባቸዋል ያሉት አቶ ሙሴ ከመድረኩ ያገኙትን እውቀት በስራ ቦታ እንዲሁም በአካባቢያቸው ለሚገኙ ህብረተሰቦች ግንዛቤ በማስጨበጥ እንዲሁም  ኤች አይ ቪ/ኤድስን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ በሚደረገው እንቅስቃሴ ርብርብ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አንዳንድ ተሳታፊዎች ስልጠናው ስለ ኤች አይ ቪ/ኤድስና የአባለዘር በሽታዎች በግልፅ እንድንወያይ ያደረገና ግንዛቤ ያገኘንበት ነው በማለት በቀጣይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደዚህ አይነት መድረኮችን በተከታታይነት ማዘጋጀት እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው በሥራ ቦታ የፀረ ኤች አይ ቪ/ኤድስ ስራዎች ማካተት(HIV/AIDS MAINSTREAMING)፣ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መሠረታዊ እውነታዎች ላይ ያተኮሩ ፅሁፎች እንዲሁም  የኤች አይ ቪ/ኤድስ የሥራ ቦታ ፖሊሲ ሰነድ ቀርቦ በማስተባበሪያው ባለሙያዎች ትምህርት ተሰጥቷል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡