የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ውይይት በመግባባት ተጠናቀቀ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የመምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ውይይት በመግባባት ተጠናቀቀ

ውይይቱ በመምህራንና በአስተዳደር ሰራተኛው የነበረውን ብዥታ በማስወገድ የ2009 እቅድን በተሻለ ለመፈፀም የስራ መነሳሳትንና መነቃቃትን የፈጠረ እንደሆነ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ግርማ ጎሮ ተናግረዋል ከ2008 የትምህርት ዘመን አፈፃፀም ከነበረው ጥንካሬና ጉድለት በመማር በዩኒቨርሲቲው የነበረውን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል የሚረዳ ውይይት እንደሆነም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም የያዝነው የትምህርት ዘመን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራው መጠናቀቁን ፕሬዚዳንቱ አክለው ተናግረዋል የፌደራልና አርብቶአደር ልማት ጉዳዮች ሚንስትር ዴኤታ እና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሙሉጌታ ውለታው በበኩላቸው የአገራችን እድገት ፍጥነቱ ሳይቀንስ እንዲቀጥል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ግንዛቤ የፈጠረና መግባባት ላይ ያደረሰ ውይይት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ news

ዩኒቨርሲቲዎች ዘመናዊ አስተሳሰቦች የሚመነጩበት ፣መከባበር የሰፈነባቸው፣ እኩልነት የሚታይባቸው እንዲሁም የዲሞክራሲ ባህል የሚዳብርባቸው ተቋማት እንዲሆኑ የማድረግን አስፈላጊነት ላይ በመወያት መግባባት የፈጠረ መሆኑንም አቶ ሙሉጌታ አብራርተዋል
በአለም ላይ ያለውን ከፍተኛ የገበያ ውድድር ለመቋቋም ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡት ጥራት ያለው ትምህርት ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ሙሉጌታ ለዚህም የመንግስት ፣የመምህራን፣የማህበረሰቡና የራሳቸው የተማሪዎች ሚና ምን መሆን እንዳለበት በውይይቱ መግባባት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡

በውይይቱ የተሳተፉት አንዳንድ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በበኩላቸው የተሻለ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል፡፡ 

በተለያዩ ሰልጣኞች የሚነሱ አዳዲስ ሃሳቦች ግንዛቤያቸውን በማሳደግ በቀጣይ በዩኒቨርሲቲው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እንዳነሳሳቸውም ተሳታፊዎቹ ተናግረዋልnews


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡