በትግራይ ክልል የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን ስልጠና በመካሄድ ላይ ነው

በትግራይ ክልል የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን ስልጠና በመካሄድ ላይ ነው

የትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ጎበዛይ ወልደአረጋይ እንደተናገሩት በስልጠናው ላይ የመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ባለፉት 25 ኣመታት በሀገራችን ያመጡትን ለውጥ፣የሥነ ዜጋና ሥነምግባር ትምህርት አፈፃፀም፣ የመምህራን ጥቅማ ጥቅምን የተመለከቱ ሠነዶች እንዲሁም በህዝብ ኮንፈረንሶች ላይ ከህብረተሰቡ የተነሱ ጥያቄዎችን መሠረት ያደረገ ሰነድ ተዘጋጅቶ ለውይይት መቅረቡን አስታውቀዋል፡፡

ከክልል ጀምሮ በጎጥ ደረጃ እስከሚገኙ የልማት ቡድን ድረስ ህብረተሰቡ የ2008 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃጸም የሚገመግምበት 1ሺ ያህል መድረኮች መዘጋጀታቸውን አቶ ጎበዛይ ተናግረዋል፡፡news

የዳስ ትምህርት ቤቶችን ለመቀየር የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ጎበዛይ የክልሉ ህዝብ በጉልበት፣በገንዘብና ቁሳቁስ በማቅረብ እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በክልሉ በሁሉም የትምህርት መዋቅሮች የልማት ሠራዊት መገንባቱን የተናገሩት ሃላፊው ይሁንና አፈፃፀም ላይ ወጥነት ያለው አተገባበር አለመኖሩን እና ተጨማሪ ስራዎች መስራት እንደሚገባም አስታውቀዋል፡፡

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ተሳትፎ ንጥር ቅበላ 97 በመቶ እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጥቅል ተሳትፎ 68 በመቶ መድረሱን ነው አቶ ጎበዛይ ያስታወቁት፡፡

ተግባር ተኮር የተቀናጀ የጎልማሶች ትምህርትን በተመለከተም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ያለመስራት ችግሮች ቢኖሩም ካለፉት ዓመታት የተሻለ ስራ መሰራቱንና ሽፋኑም ወደ 80 በመቶ መድረሱንም አስታውቀዋል፡፡

የልዩ ፍላጎት ትምህርት የሚፈለገው ደረጃ ባይደርስም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎች በመሰራታቸው ባሁኑ ወቅት የልዩ ፍላጎት ትምህርት ተጠቃሚዎች ሽፋን እያደገ መምጣቱን አቶ ጎበዛይተናግረዋል፡፡


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡