የጅማ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እና የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ስልጠናና ውይይት በማካሄድ ላይ ናቸው

የጅማ ከተማ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እና የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ስልጠናና ውይይት በማካሄድ ላይ ናቸው

አንዳንድ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ስልጠናውና ውይይቱን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ለስልጠና በተዘጋጁት ሰነዶች ላይ ሰፊ ውይዩት በማድረግ ግልጽነት እንዲፈጠር መደረጉ የመማር ማስተማር ሂደቱን ሰላማዊ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

በተለይም ውይይቱ ሀገሪቱ ያቀደችውን የልማት ግብ ዳር ለማድረስ ወሳኝ ነው ያሉት ተሳታፊዎቹ በስልጠናውና በውይይቱ በተነሱት ለልማት ማነቆ በሆኑት ጥያቄዎች መንግስት ፈጣንና ተግባራዊ ምላሽ መስጠት ይገባዋል ብለዋል፡፡

ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር የ2009 ዓ.ም የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ በተሻለ ደረጃ ውጤታማ ለማድረግ አቅም Jimmaእንደሚፈጥርላቸውም ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል፡፡

የጅማ ከተማ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገዛሊ ከድር ስልጠናው ከተጀመረበት እለት ጀምሮ አሰልጣኞቹና የአስተዳደር ሰራተኞቹ ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ስኬታማነት ጥያቄዎችና ሀሳቦችን በማንሳት የነቃ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ስልጠናውና ውይይቱ በቴክኒክና ሙያ በትምህርትና ስልጠና ስትራቴጂ የተቀመጠውን ዓላማና ራእይ ለማሳካት ግብዓት እንደሚሆን አቶ ገዛሊ ተናግረዋል፡፡

የጂማ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሻፊ ሁሴን በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት እየተሰጠ ያለው ስልጠና በትምህርት ተቋሟት ያለውን ግንዛቤ በማስፋት ጠንካራ የትምህርት ልማት ሰራዊት በመገንባት የ2009 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጤናማና ሰላማዊ እንዲሆን ማስቻል ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናውና ውይይቱ መምህራኑም ሆኑ የትምህርት አመራር አካላት በየደረጃው የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እንዴት መፍታት እንደሚችሉና እራሳቸውንም እንዴት ማስተካከል እንደሚገባቸው የሚጠቁም ነው ያሉት አቶ ሻፊ ይህም የተማሪዎችን ውጤታማነት በማሻሻል በሀገር ደረጃ በትምህርት ሴክተር የሚፈለገውን የሰው ኃብት ልማት ለማፋጠን ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ ያነቃቃል ብለዋል፡፡

 


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡