የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በውይይቱ ወቅት እንደገለፁት ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በሃገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት መመዝገቡን ጠቁመው በአሁኑ ሰዓት የሃገሪቱን የህዳሴ ጎዞ ወደ ኋላ ለመቀልበስ ፀረ ሰላም ኃይሎች እያካሄዱ ያለውን ህገ ወጥ ድርጊት ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች ማውገዝ እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡ 

ሃገሪቱን ለመበተን የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቅመው የሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ኃይሎችን የተቋሙ ሰራተኞች ከመንግስት ጋር እጅና ጓንት ሆነው በመከላከል ሀገሪቷ የጀመረችውን የህዳሴ ጉዞ ማፋጠን እንዳለባቸውም አቶ ሽፈራው አስገንዝበዋል፡፡

እንደሚኒስትሩ ገለፃ በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰቱት ችግሮች ዋነኛ መንስኤአቸው የመልካም አስተዳደርና ኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮች መሆናቸውን ጠቁመው የተቋሙ ሰራተኞች በንቃት መታገል እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት የገነባነውን የዴሞክራሲ ባህል፣ እሴት፣ ልማትና እድገት ለማስጠበቅ በየጊዜው የሚፈጠሩ ልዩነቶችን በሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ መፍታት ይገባል ያሉት ሚኒስትሩ የተቋሙ ሰራተኞች በህገ ወጥ መልኩ በሚካሄዱ ማናቸውም ድርጊቶች ከመሳተፍ መቆጠብ እንደሚገባቸውና ስራቸውን በአግባቡ ማከናወን እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊዎች ህገ ወጥ ድርጊቶችን በማውገዝ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ የገለፁ ሲሆን በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተው በክቡር ሚኒስትሩ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

32 - 2በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡