የእንግሊኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከላት ዓመታዊ ጉባኤ ተካሄደ

የእንግሊኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከላት ዓመታዊ ጉባኤ ተካሄደ

28 - 5ኢንስፔክሽን

በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሥር ያለው የአፍ መፍቻና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ዳይሬክቶሬት 2008 በጀት ዓመት ሊያከናውናቸው ከያዛቸው ዕቅዶች አንዱ ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከላት ጋር ዓመታዊ ጉባኤ በማካሄድ የጋራ ግምገማ ማድረግና አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው። 

በመሆኑም የአፍ መፍቻና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ዳይሬክቶሬት ጉባኤውን ከመምህራን ስልጠና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ካላቸው ከሃያዎቹ ዩኒቨርስቲዎችና 36 የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች፣ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከላት( ELICs) አስተባባሪዎችና GEQIP ተወካዮች እንዲሁም ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው የክልል ትምህርት ቢሮ ተወካዮች በድምሩ 113 ተሳታፊዎች በተገኙበት ጉባኤውን ለሶስት ተከታታይ ቀናት በአዳማ ከተማ ኮምፎርት ሆቴል አካሂዷል።

የአፍ መፍቻና የእንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታያቸው አያሌው እንደተናገሩት የጉባኤው ዓላማ የዓመቱን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከላት ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችና ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት የትኩረት አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ነው። 

ከእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ማዕከላት እና ከአፍ መፍቻና እንግሊዝኛ ቋንቋ ትምህርት ልማት ዳይሬክቶሬት ከቀረበው የመስክ ምልከታ ሪፖርት በመነሳት ባጋጠሙ ተግዳሮቶችና የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ ሰፊ ውይይት የተካሄደ መካሄዱን አቶ ታያቸው ጠቁመዋል፡፡

የማዕከላቱ ዕቅዶችና አፈጻጸም ወጥ አለመሆንና ማዕከላቱ ከተቋቋሙበት ዓላማ አንጻር የተጠበቀውን ውጤታማ ተግባራት አለማከናወን፣ የአፈጻጸም ስታንዳርድ አለመኖር፣ በማዕከላቱ ስልጠና ድጋፍ የሚሰጣቸው አካላት ተለይቶ ያለመቀመጥ እንዲሁም የአፈጻጸም ሪፖርቶች በአብዛኛው መረጃንና ውጤትን እንዲሁም የበጀት አጠቃቀም ሁኔታን ያለማሳየት በዋናነት የሚጠቀሱ ችግሮች መሆናቸውንም ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡