ለሀገራችን ፈጣን እድገት የሰው ኃይል በማልማት ረገድ የትምህርት ፖሊሲው፣ የህዝብና የልማት አጋሮችን ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው!

ለሀገራችን ፈጣን እድገት የሰው ኃይል በማልማት ረገድ የትምህርት ፖሊሲው፣ የህዝብና የልማት አጋሮችን ተሳትፎ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው!

ለፉት 25 ዓመታት ወዲህ ለሀገራችን ልማትና እድገት ወሳኝ ሚና የተጫወተውን የሰው ኃይል ልማት ማፍራት የተቻለው መንግስት ከነደፈው የትምህርት ፖሊሲ በተጨማሪ ህዝቡንና የልማት አጋሮችን ማሳተፍ በመቻሉ እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አስታወቁ፡፡

article

25ኛውን የግንቦት 20 የድል በዓልን አስመልክቶ ለተለያዩ የሚዲያ አካላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ትምህርት የአንድ ሃገር የልማት፣ የሰላምና የዴሞክራሲ ኃይል የሚሆን የሰው ሃይል የሚያለማ የስራ ዘርፍ መሆኑን ገልፀው ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በየደረጃው በሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ዘርፎች በትምህርት ተሳትፎና ፍትሐዊነት ውጤታማ ስራ በመሰራቱ ለሀገራችን ልማትና እድገት ወሳኝ ሚና የተጫወተውን የሰው ኃይል ልማት ማፍራት ተችሏል ብለዋል፡፡

ትምህርት በየአካባቢው ባልተማከለ አስተዳደር እንዲተዳደር በማድረግ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በራሳቸው ባህልና ቋንቋ እንዲማሩ ከማድረግ ባለፈ ትምህርት ቤቶች በስፋት እንዲደርሱ መደረጉን የጠቆሙት ሚኒስትሩ በአንድ ቀበሌ አንድና ቢበዛ አራት የሚደርሱ ትምህርት ቤቶችን እንዲሁም የቅድመ መደበኛና የመደበኛ ትምህርት ቤቶችን በሁሉም አካባቢዎች በፍትሐዊነት ማዳረስ በመቻሉ የሀገራችን ዜጎች የመማር ዕድል አግኝተዋል ብለዋል፡፡

በሂደትም የትምህርት አሰጣጡ በትምህርት ፖሊሲ እንዲታገዝ በማድረግ ካለፉት 20 ዓመታት ወዲህ የትምህርት ፖሊሲ ተነድፎ ወደ ስራ መገባቱን ክቡር አቶ ሽፈራው ገልጸው የፖሊሲው መነደፍም የተደራሽነትን፣ የፍትሐዊነትን፣ የተገቢነትንና የጥራትን ጥያቄ የመለሰ ከመሆኑም ባለፈ በገጠርና በከተማ፣ በአርብቶ አደርና በአርሶ አደር አካባቢዎች፣ በሴቶችና በወንዶች መካከል የነበረውን ልዩነት ማጥበብ ተችሏል ብለዋል፡፡  ከሃያ አምስት አመታት በፊት በመላ ሃገሪቱ አራት በሚጠጉ ትምህርት ቤቶች 1.9 ሚሊዬን ተማሪዎች የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በመንግስትና በግል 39 በላይ ትምህርት ቤቶች እንደደረሱና በዚህም 27 ሚሊዬን በላይ ተማሪዎችን ማስተማር የተቻለ መሆኑን ክቡር አቶ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡

273 የማይበልጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችንም ቁጥር ለማሳደግ በተደረገው ጥረት በአሁኑ ወቅት ከሶስት 300 በላይ የሚበልጡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በሁሉም ወረዳዎች ማስፋፋት መቻሉን አቶ ሽፈራው ገልጸው በአንዳንድ ወረዳዎች እንደአስፈላጊነቱ ሶስትና አራት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያሉበት ሁኔታም አለ ብለዋል፡፡

ፖሊሲው ጸድቆ ወደ ስራ ሲገባ በመላ ሀገሪቱ በከተማም በገጠርም ተሰማርተው ዜጎችን ሲያስተምሩ የነበሩ የመምህራን ቁጥር 68 ይደርሱ የነበሩ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ 1ኛና 2 ደረጃ በማስተማሩ ስራ ላይ 497 200 መምህራንን በማሰልጠንና በማሰማራት የትምህርት ስራውን ተደራሽ ማድረግ መቻሉንም ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

1 - Ginbot 20 - Minister Pic 2

እጅግ ዝቅተኛ የነበረውን የቅድመ መደበኛ ትምህርት ተሳትፎ ለማሳደግ በተወሰደው እርምጃ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ያገኙ የነበሩትን ሰባት ሚሊዬን ህጻናት በአሁኑ ወቅት 45 ሚሊዬን በላይ ህፃናትን የቅድመ መደበኛ ትምህርት እንዲያገኙ በማድረግ ሽፋኑንም 60 በመቶ ማድረስ መቻሉም ተጠቅሷል፡፡

ራሳቸውን ብሎም ለሀገራቸው ሁነኛ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ ክህሎት ያላቸው ተወዳዳሪ የሆኑ ዜጎችን በማፍራት በተለይም ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ መር የኢኮኖሚ ሽግግር ለሚደረገው እንቅስቃሴ የበኩሉን አስተዋፅኦ የሚያበረክት ዜጋ በማፍራት ረገድ ስኬታማ ስራ መሰራቱን ሚኒስትሩ ጠቅሰው ለዚህ ስኬትም ከግንቦት 20 ድል በፊት በሀገሪቱ የነበሩ 16 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ማሰልጠኛ ተቋማትን ወደ አንድ 350 ተቋማት በማድረስና 20 በላይ ብቁ አሰልጣኞችን ማፍራት በመቻሉ ነው ብለዋል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዘርፍም ከግንቦት 20 ድል በፊት ከነበሩት ሁለት ዩኒቨርሲቲዎች በመነሳት በአሁኑ ወቅት ግማሽ ሚሊዬን ተማሪን የሚያስተናግዱ 33 የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተገንብተው የሀገሪቱን ሰብዓዊ የሰው ሀብት ልማት በማፍራት ላይ እንደሚገኙ የተናገሩት አቶ ሽፈራው በቀጣይም በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን አስራ አንድ ተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመገንባት ላይ መሆናቸውንና ይህም ሀገሪቱ በየዘርፉ ለልማት የምትፈልገውን የሰው ሃይል ልማት በማፍራት ረገድ የገዘፈ ሚና እንዳለው አስረድተዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ከማስፋፋት ጎን ለጎንም የሀገሪቱን የቀጣይ እድገት ታሳቢ በማድረግ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቅበላና ስልጠና ስርዓት ሰባ በመቶ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ቀሪው ሰላሳ በመቶ ደግሞ በማህበራዊ ሳይንስ እንዲሆኑና ስርጭታቸውም የሃገራችንን ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦችን አሰፋፈርና አኗኗር ታሳቢ ያደረጉ መሆኑን አቶ ሽፈራው ገልፀዋል፡፡

በዘርፉ የተገኙ ስኬቶች እንዳሉ ሆኖ የግብዓት አቅርቦትና አጠቃቀም ችግሮች መኖራቸው፣ ምሩቃን ወደ ሚፈለገው የሙያና ሥነ ምግባር ብቃት ደረጃ በተሟላ መልኩ አለመድረስ፣ የቴክኖሎጂና የምርምር ውጤቶች በሚፈለገው ደረጃ አለማደግ እንዳሉና በቀጣይ ለክፍተቶቹ መፍትሔ በመስጠት ዘርፉን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሁሉንም ተሳትፎና ርብርብ እንደሚጠይቅ በጋዜጣዊ መግለጫው ተጠቅሷል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡