በተፈጥሮ ሳይንስና በምህንድስና ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች መምህራንና እና መካከለኛ አመራሮች ተሸለሙ

በተፈጥሮ ሳይንስና በምህንድስና ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች መምህራንና እና መካከለኛ አመራሮች ተሸለሙ

 

2 - Hawwasa University News - Pic-4

በተፈጥሮ ሳይንስና በምህንድስና ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 10 ሴት ተማሪዎች እንዲሁም ሶስት ሴት መምህራንና ሁለት መካከለኛ አመራሮች በኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀላቸውን የሞባይል ስልክና ሌሎች ሽልማቶች ከዶክተር ዴላሚኒ ዙማ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ተቀበሉ፡፡

‹‹ኢትዮጵያን እወዳታለሁ፡፡ይህን የምለው ላለፉት አራት ዓመታት ስለኖርኩባት አይደለም፡፡ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የመጣሁት በተማሪነት ዘመኔ እንደ ኤውሮፓ አቆጣጠር 1976 አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ልዩ ስብሰባ ላይ የደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስን ወክዬ ንግግር ለማድረግ ነበር ፡፡እናም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያን አውቃታለሁ፡፡በኢትዮጵያ ለመጣው ሁለንተናዊ ለውጥ ህያው ምስክር መሆኔን ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡›› የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር / ዴላሚኒ ዙማ፡፡

/ ዴላሚኒ አፍሪካ ህብረት ተብሎ በተሰየመው የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዳራሽ በመገኘት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የአፍሪካን አህጉራዊ ራዕይ /አጀንዳ 2063/ አስመልክተው ንግግር ባደረጉበት ወቅት ሴቶች የሚጨቆኑበትና ወደ ኋላ የሚቀሩበት ጊዜ አልፎ ተደማጭነታቸውና ተቀባይነታቸው አያደገ መጥቷል በመሆኑም በተፈጥሮ ሳይንስና በምህንድስና ዘርፎች ከወንዶች ተማሪዎች ተመጣጣኝ የሆነ የሴት ተማሪዎች ተሳትፎ ሊኖር ይገባል ብለዋል፡፡ በስነስርዓቱ ላይ ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች በኤሌክትሪካል ኢንጅነሪንግ፣ በወተር ሰፕላይ ኤንድ ኢንቫሮመንት ኢንጅነሪንግ፣ በኮምፒዩተር ሳይንስ፣ በኤሌክትሮ ሜካኒካል፣ በባዮሎጂና በስታቲስቲክስ ትምህርቶች 3.59 እስከ 3.85 ውጤት ያመጡ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

አጀንዳ 2063 አንድነቷ የጠነከረ፣ የበለፀገችና ሰላም የሰፈነባት አፍሪካን የመፍጠር ጉዳይ መሆኑን የገለፁት / ዴላሚኒ ዛሬ ላይ ጠንክረን ከሰራን ከረሃብ፣ ከድንቁርና፣ ከበሽታና ከጦርነት ነፃ የሆነች አፍሪካን መፍጠር እንችላለን ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለማችን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች ያለች ሀገር መሆኗን የተናገሩት / ዴላሚኒ ይህንን ዕድገት ለማስቀጠል በግብርና፣በትምህርትና በቴክኖሎጂ ላይ የተጠናከረ ስራ መስራት እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡

በመቀጠልም ጥያቄና አስተያየት ከተሳታፊ ተማሪዎች የቀረበ ሲሆን በዶ/ ዴላሚኒ ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ዮሴፍ ማሞ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች እንደመሆናችሁ መጠን አጀንዳ 2063 የማሳካት ሃላፊነት የተጣለባችሁ መሆኑን መረዳት ይገባቸኋል ብለዋል፡፡ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ በመሆን 2025 . ከተማሪዎቹ 5 በመቶ የሚሆኑትን የውጪ ሀገራት ተማሪዎች የማድረግ ራዕይ ሰንቆ እየተጓዘ መሆኑን የገለፁት ፕሬዚዳንቱ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለሚውጣጡ 10 ተማሪዎች የነፃ ትምህርት ዕድል ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡

ከተሸላሚዎቹ መካከል አንዳንዶቹ በሰጡት አስተያየት በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ሴት ተማሪዎች ሽልማት መስጠቱ ለሌሎች ማበረታቻ እንደሚሆን ጠቁመው ሴት ተማሪዎች ያለብንን ውስጣዊና ውጫዊ ጫና ተቋቁመን ያስመዘገብነው ውጤት በመሆኑ ዕውቅናና ሽልማት መሰጠቱ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡