የትምህርት አመራር፣ አደረጃጀት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና የፋይናንስ መመሪያ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ያላቸው አስተዋፅኦ ወሳኝ ነው

የትምህርት አመራር፣ አደረጃጀት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና የፋይናንስ መመሪያ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ያላቸው አስተዋፅኦ ወሳኝ ነው

የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተግባራዊ በሆነባቸው 21 ኣመታት ውስጥ አራት የትምህርት ዘርፍ ልማት ዕቅዶች ተግባራዊ ሲሆኑ አምስተኛውም የትምህርት ዘርፍ ልማት ዕቅድ እየተተገበረ ይገኛል፡፡ መንግስት 1994 . የሀገሪቱን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎችን በመፈተሽ የተሃድሶ ፕሮግራም ባካሄደበት ወቅት የትምህርት ስርዓታችንን በመፈተሽ ሶስት መሠረታዊ ነገሮች አከናውኗል፡፡ከነዚህ ሶስት መረታዊ ነገሮች የመጀመሪያው በሀገሪቱ የትምህርት ጥራት ላይ የተደረገው ጥናትና የመምህራን ትምህርት ልማት መርሃ ግብር ነው፡፡ሁለተኛው የሃገሪቱ ዜጎች የሀገራችንን እሴቶች ተላብሰው እንዲቀረፁ ያስችላል በሚል የተዘጋጀውን የስነ ዜጋ እና የስነምግባር ትምህርት ተግባራዊ ማድረግ ሲሆን ሶስተኛው የሀገሪቱ የትምህርት አመራር፣አደረጃጀት፣የህብረተሰብ ተሳትፎና የፋይናንስ መመሪያ ስርዓት በመዘርጋት በክልሎች ተሰራጭቶ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ነበር፡፡

በአዳማ ከተማ ለሶስት ቀናት በተካሄደ ዓውደ ጥናት የሀገራችንን የትምህርት አመራር፣ አደረጃጀት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና የፋይናንስ መመሪያ እንዲሁም የቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስታንዳርዶች ላይ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት ለማሻሻል የሚረዳ ግብዓት ማሰባሰብ ነው፡፡

ዓውደ ጥናቱን በንግግር የከፈቱት በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶር ጥላዬ ጌቴ እንደተናገሩት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ሽፋን ባሁኑ ወቅት በከፍተኛ ሁኔታ በማደጉ ባሁኑ ወቅት ከሀገራችን አጠቃላይ ህዝብ ውስጥ 27 ሚሊዮን ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው ጥሩ ሥርዓተ ትምህርት ቢኖረንም ብቃት ያለው የሙያ ስነምግባር የተላበሰ መምህርና የትምህርት አመራርና አደረጃጀት ከሌለን በሚፈለገው መጠን ውጤታማ መሆን አይቻልም ብለዋል፡፡

መንግስት ከፌዴራል እስከ ወረዳ ድረስ ባሉት እርከኖች ምቹ የትምህርት ቤት አካባቢ በመፍጠር ከፍተኛ የትምህርት ውጤት ለማስመዝገብ ዓላማ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው ያሉት ዶር ጥላዬ የስታንዳርዶቹና መመሪያዎቹ መሻሻል የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የሚኖረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ የኣውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በቀረቡት ሰነዶች ላይ በጥልቀት ሊወያዩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የትምህርት ሥርዓታችን ችግር የጥራት ችግር በመሆኑ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ በማዘጋጀት የተለያዩ መርሃ ግብሮች ተግባራዊ ስናደርግ ቆይተናል ያሉት / ጥላዬ በተለይም ስርዓተ ትምህርቱ የሀገራችንን ራዕይ የሚያሳካ እንዲሆን በየጊዜው ማሻሻያዎች በማድረግ የትምህርት ጥራትን ለማሳካት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የመምህራን ትምህርት ልማታችንን ለመፈተሽ 11 ዩኒቨርሲቲዎችና ከአራት መምህራን ትምህርት ኮሌጆች የተውጣጣ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ከቅድመ መደበኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን አሰለጣጠን እንዲሁም የትምህርት አመራሩን በመፈተሽ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

በገጠርም ሆነ በከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን ስታንዳርዳቸውን መፈተሸና ማስተካከል እንደሚገባ ጠቁመው ይህም የትምህርት ሥርዓቱ የላቀ ለውጥ እንዲያመጣ የሚያደርግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የዓውደ ጥናት ተሳታፊዎች ከተልዕኳቸውና ከስራ ሃላፊነታቸው አኳያ የትምህርት ስርዓታችንን ለማሳለጥ እንዲሁም በትምህርት ገበታ ላይ ያለው ትውልድ የኢትዮጵያን ህዳሴ የሚያስቀጥል እንዲሆን ለማድረግ ወሳኙ ነገር የትምህርት አመራርን፣አደረጃጀት እና አሰራር የህብረተሰብ ተሳትፎ፣ለትምህርት ቤቶች የሚመደብ ሃብትና በጀት እንዲሁም የትምህርት ቤቶች ስታንዳርድ ወሳኝ መሆናቸውን ተረድተው ለውይይት የቀረቡትን ሰነዶች ለማዳበር የሚያስችል ግብዓት ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል፡፡

6 - Educan mangmnt Public Partcpn and Fiance Pic 2

በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤቶች መሻሻል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሳቡ ብርቅነህ በበኩላቸው የትምህርት አመራር፣አደረጃጀት፣የህብረተሰብ ተሳትፎና የፋይናንስ መመሪያ ተቀርፆ ስራ ላይ ከዋለ ወዲህ በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ በርካታ ለውጦች ከመምጣታቸው ባሻገር የተለያዩ ስትራቴጂዎችና ማኑዋሎች ተዘጋጅተው ጠቁመው የትምህርት ሥርዓቱን ፍላጎት በሚመልስ መልኩ መመሪያውን ማሻሻል አስፈልጓል ብለዋል፡፡ የትምህርት ቤቶች ስታንዳርድ ብቃት ያላቸው መምህራን፣ምቹ የመማሪያ ቦታ እንዲሁም ለመማር ማስተማሩ ሂደት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች እንዲሟሉ የሚያስገድድ በመሆኑ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዓውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች በትምህርት አመራር፣አደረጃጀት፣የህብረተሰብ ተሳትፎና የፋይናንስ መመሪያ፣ በቅድመ መደበኛ፣ በመጀመሪያ ደረጃ እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስታንዳርድ ላይ በቡድን ተወያይተዋል፡፡ በዓውደ ጥናቱ ላይ ከፌዴራልና ከክልል የተውጣጡ 300 ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡