ሃያ ሶስት ሺ አምስት መቶ ሰባ አንድ መምህራንና የትምህርት አመራር አካላት እየሰለጠኑ ነው

ሃያ ሶስት ሺ አምስት መቶ ሰባ አንድ መምህራንና የትምህርት አመራር አካላት እየሰለጠኑ ነው

 

8 - Training 23000 teachers and leaders Pic 2

በሃገር አቀፍ ደረጃ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና በየትምህርት እርከኑ ብቁ የሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራር አካላትን ለማፍራት በተያዘው ዕቅድ በስራ ላይ ስልጠናና በቅድመ ስራ ስልጠና አቅማቸውን እያጎለበተ ነው፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክተር / አበበች ነጋሽ 2008 በጀት አመት የስድስት ወራት እቅድ ክንውን ግምገማ መድረክ ላይ እንደገለፁት ብቁ የሆኑና ለየትምህርት እርከኑ የሚመጥኑ መምህራንና አመራር አካላትን በማፍራት በትምህርት ቤቶች እንዲመደቡ ለማድረግ በበጀት አመቱ በተደረገው ጥረት ሃያ ሶስት አምስት መቶ ሰባ አንድ መምህራንና የትምህርት አመራር አካላትን ከሰርተፊኬት ወደ ዲፕሎማ ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪና ከዲግሪ ወደ ሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ደረጃቸውን ለማሻሻል 2007 . በክረምት እና 2008 . በበጋ ወራት እየሰለጠኑ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

የመምህራንና የአመራሩን አቅም ለማጎልበት ስርዓተ ትምህርት እንዲሁም ሞጁሎች ተዘጋጅተው እየሰለጡ ቢሆንም አሰለጣጠኑን በመፈተሸ ተግዳሮቶች ካሉ መፍትሄ ለመስጠትና የአሰለጣጠን ስርዓቱን ለመከለስ እንዲቻል በሃገር አቀፍ ደረጃ ሶስት ቡድን ተቋቁሞ ጥናት እየተካሄደ እንደሚገኝ / አበበች ገልጸዋል፡፡

ከሃያ አመታት በፊት ትኩረት ያልተሰጠው የቅድመ መደበኛ ትምህርት በአሁኑ ወቅት ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ዳይሬክተሯ የቅድመ መደበኛ ትምህርት መምህራንን ከሰርተፊኬት ወደ ዲፕሎማ ደረጃቸውን ለማሻሻል የቅድመ መደበኛ የዲፕሎማ ስርዓተ ትምህርት ተዘጋጅቶ ስልጠና የሚሰጡ ኮሌጆች እየተጠቀሙበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር በተያያዘ በሃገር አቀፍ ደረጃ 2 746 ቅሬታዎች ለአብነት የመምህራን ዝውውር፣ የደረጃ እድገት፣ የአመራር ክህሎት፣ በየደረጃው የአፈፃፀም ችግሮች መኖራቸው ቀርበው 2 615 ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ቀሪዎቹ በመመሪያ መሰረት የሚፈቱ መሆኑን / አበበች ገልፀዋል፡፡

የመምህራን የመኖሪያ ቤትና የደመወዝ ጥያቄዎች በተለያዩ ጊዜያት የቀረቡ ሲሆን ምላሽ ለመስጠት ሰፊ ጥናት ተካሂዶ በየደረጃው ባለ አመራር እየታየ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በክልሎች የመልካም አስተዳደር ችግሮች የነበሩ ሲሆን አሁን እየተፈቱ ያሉበት ሁኔታ መኖሩን የገለፁት ዳይሬክተሯ በቀጣይ የትምህርት አመራር አካላት አፈፃፀማቸው ተገምግሞ ብቃት ከሌላቸው ከአመራርነታቸው ተነስተው በሚመጥናቸው ቦታ ተመድበው እንዲሰሩ የሚያስችል ስርዓት ለመፍጠር የአፈፃፀም መመሪያ የተዘጋጀ መሆኑንም / አበበች ገልፀዋል፡፡

ሴቶችን ወደ አመራርነት ለማምጣት 50 በመቶ ለመፈፀም ግብ የተጣለ ቢሆንም አፈፃፀሙ 19 በመቶ ብቻ በመሆኑ በቀጣይ ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ በመግለፅ 2008 በጀት ዓመት 2ኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ 25 በመቶው የሚፈፀምበት በመሆኑ ክልሎች የመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ተግባርን በተያዘለት ጊዜ እንዲያጠናቅቁ ዳይሬክተሯ አስገንዝበዋል፡፡

በቀጣይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ስልጠና መርሃ ግብር በመፈተሸ ማሻሻል፣ ሴቶችን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርነትና በየደረጃ ባሉ እርከኖች የአመራርነት ተሳትፏቸውን ማሳደግ፣ የሥራ ላይ ሙያ ማሻሻያ መርሃ ግብር አተገባበርን ማጠናከር ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራ / አበበች አስታውቀዋል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡