የኮሙዩኒኬሽን ስትራቴጂው ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የትምህርት ዘርፉን እቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ እገዛው የላቀ ነው

የኮሙዩኒኬሽን ስትራቴጂው ለሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የትምህርት ዘርፉን እቅዶች ተግባራዊ ለማድረግ እገዛው የላቀ ነው

አስራ አንደኛው የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የኮሙኒኬተሮች ፎረም የአምስት አመት ረቂቅ የኮሚኒኬሽን እስትራቴጂ፣ 2008 . የመልካም አስተዳደር ንቅናቄ ማቀጣጠያ ረቂቅ እቅድ እና በፈተና ሥነ-ምግባር ጥሰትን በማሰወገድ ረገድ የኮሚኒኬተሮች ሚና ላይ በዝርዝር በመወያት አቅጣጫዎችን አስቀመጠ፡፡

በአዳማ ከተማ የተካሄደው ፎረም ኮሚኒኬሽን 5ኛው የትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ልማት ፕሮግራም እና 2ኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የትኩረት ጉዳዮች ላይ ውጤታማ የሆነ አስተዋጽኦ ሊያደርግ የሚችልበት መንገዶች ላይ ለመወያት አድል ፈጥሯል፡፡ ፎረሙ በዋናነት ያተኮረው ለዘርፉ የተዘጋጀውን ረቂቅ የአምስት አመት ኮሚኒኬሽን እስትራቴጂ በመገምገም እና በማበልጸግ ኮሚኒኬተሮች በባለቤትነት እንዲተገብሩት ማስቻል ላይ ነው፡፡ በተጨማሪም ፎረሙ የትምህርት ዘርፍ ኮሚኒኬተሮች የእስትራቴጂ አነዳደፍ ላይ ያላቸውን አቅም በማጎልበት በአዲስ መልክ የተነደፉትን የኮሚኒኬሽን እስትራቴጂክ ግቦች ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ሊተገብሩት በሚችሉት መልኩ እንዲያስቀምጡ አስችሏቸዋል፡፡ በተሰጣቸው ስልጠና መሰረትም ኮሚኒኬተሮች የእስትራቴጂውን ረቂቅ የተግባር እቅድ በመከለስ የተቋማዊ ፍላጎት እና አላማዎችን ባገናዘበ መልኩ 2009 .. እቅዳቸው ውስጥ እንደሚያካትቱት አረጋግጠዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ አህመድ ሰይድ ስትራቴጂው በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት አቅም የሚፈጥር እንደሆነና በመልካም አስተዳደር ስራዎች ላይም የኮሙዩኒኬሽን ሚና የላቀ እንዲሆን እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡

በመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት የሚኒስትሩ ልዩ አማካሪ አቶ ሞቱማ ተመስገን በበኩላቸው የኮሙዩኒኬሽን ስራ የሀገራችንን ገጽታ በመገንባትና ብሄራዊ መግባባትን በመፍጠር የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተናግረው መንግስት ትምህርትን በየደረጃው በፍትሀዊነት ለማዳረስ ጥራቱንም ለማረጋገጥ የሚያደርገው ጥረት የመላውን ህብረተሰብና የትምህርት ማህብረሰብ ተሳትፎና ድጋፍ የሚጠይቅ በመሆኑ በትምህርት መስክ የተመዘገበውን እድገት ለማሳወቅ ብሎም ዕድገቱ ቀጣይነት እንዲኖረው በዘርፉ ከሚገኙ ኮሙዩኒኬተሮች የሚጠበቅ አብይ ተግባር እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡

መንግስት በትምህርት ዘርፍ የያዛቸው እቅዶች እንዲሳኩ የተጠናከረ የኮሙዩኒኬሽን ስራ መስራት ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር ቢሆንም የዘርፉን የኮሙዩኒኬሽን መዋቅር በሚፈለገው መጠን በማደራጀትና በመጠቀም ረገድ አሁንም ክፍተቶች የሚስተዋሉ በመሆኑና ክፍተቶችንም ቀርፎ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት ሚኒስቴር /ቤቱ ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር እየሰራ ያለው የአቅም ግንባታ ስራ የሚበረታታና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባ መሆኑን አቶ ሞቱማ ገልፀዋል፡፡         

በትምህርት ሚኒስቴር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በትምህርት ጥራት ስትራቴጂያዊ ድጋፍ ፕሮጀክት /QESSP/ አማካኝነት ከብሪትሽ ካዊንስል የተመደቡት አማካሪዎች አቶ ፍሬው በቀለ እና ሚስተር አርኖ ሄጂንስ ረቂቅ የኮሙኒኬሽን እስትራቴጂውን አስመልክቶ ለፎረሙ አባላት ስልጠና በሰጡበት ወቅት እንደገለፁት እስትራቴጂው የትምህርት ዘርፉን የኮሙኒኬሽን ስራ ወጥነት፣ ተያያዥነት እና ቅንጅት ባለው መልኩ በማካሄድ ስኬታማነቱን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

ረቂቅ ስትራቴጂው ሰባት ጥቅል ዓላማዎችን የያዘ ነው፡፡ እነዚህም በዘርፉ ውስጥ /ኢንተርናል/ ኮሚዩኒኬሽን እንቅስቃሴን በማጠናከር የዘርፉን እውቀት መረጃ እና መልእክት ከምችት እና ስርጭት ውጤታማ ማድረግ፤ ኮሚኒኬተሮች ግልፅ የሆነ የስራ ሃላፊነት፣ ድርሻ፣ መዋቅር፣ እና የተግባራት ዝርዝር እንዲኖራቸው ማስቻል፤ የተቋማዊ የማንነት የምንነት እንዲሁም የባህሪያት እና የእሴቶች መገለጫ (ብራንዲንግ) መመሪያዎችን በአግባቡ ስራ ላይ ማዋል፤ ቁሶች በጀትና መዋቅርና እና ምቹ ከባቢያዊ ሁኔታዎች ማመቻቸት፤ የተጠናከረ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ወይም የገጽታ ግንባታ ስራ ማከናወን፤ የዘርፉን መርሃግብራዊ የስራ እንቅስቃሴዎች በተጠናከረ እና ውጤታማ በሆነ የኮሚኒኬሽን ስራ ማገዝ፤ እና የመጨረሻውም በትምህርትና የስልጠና ዘርፍ ውስጥ ያሉትን የፖሊሲ የህግጋት እና የመመሪያ ማእቀፎች ላይ እንደአስፈላጊነቱ የአድቮኬሲ ስራዎችን በኮሚኒኬሽን ማገዝ ናቸው፡፡

15 - Communicators Forum - Strategy - Pic 1

 

ረቂቅ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂው 2009 . ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ፣ የክልል ትምህርት ቢሮዎችና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲዎች እንደየስራቸው ተጨባጭ ሁኔታ የራሳቸውን የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ በማዘጋጀትና በማደራጀት የዘርፉን የኮሙኒኬሽን ሥራ ለትምህርት ልማት አስተዋፅኦ እንዲያበረክት የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አማካሪዎቹ ገልፀዋል፡፡

በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አህመድሲራጅ ሚስባህ የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የኮሙዩኒኬሽን አካላት የመልካም አስተዳደር ማስፈፀሚያ ረቂቅ ዕቅድ በፎረሙ ላይ ባቀረቡበት ወቅት የመልካም አስተዳደር ችግሮች በአብዛኛው የሚታዩት በመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ መሆናቸውና አገልግሎቶችን ለማግኘት ግዴታውን አውቆ የሚንቀሳቀስ፣ ተገቢውን አገልግሎት ተቋማቱ ባስቀመጡት ስታንዳርድ መሠረት የማግኘት መብቱን ማስከበር የሚችልና ብልሹ አሠራሮችን የሚያጋልጥ ህብረተሰብ በመገንባት ሂደት የኮሙኒኬሽን አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የረቂቅ ዕቅዱ ዓላማ በትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ መልካም አስተዳደርን በሚፈለገው ደረጃ በማስፈን በየደረጃው የታቀዱ የልማት እቅዶች የጋራ መግባባት ተፈጥሮባቸው ተግባራዊ እንዲሆኑ የሚያስችል የኮሙዩኒኬሽን ሥራ መሥራት መሆኑን የጠቆሙት ባለሙያው በቀጣይም በየደረጃው የሚገኙ የትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ የኮሙዩኒኬሽን አካላት የየራሳቸውን የተዘረዘረ የመልካም አስተዳደር ማቀጣጠያ ዕቅድ እንዲያዘጋጁና በዕቅዱ ላይ ከህዝብና መንግስት ክንፎቻቸው፣ ከተገልጋዮችና ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተውበት የጋራ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ ክትትል ይደረጋል ብለዋል፡፡

አንዳንድ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከመድረኩ ስለኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ቀረፃና አስፈላጊነት እንዲሁም የኮሙኒኬሽን እቅድ አዘገጃጀት ላይ እውቀት እንዳገኙ ገልፀው በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለመፈፀም የተያዙ የኮሙኒኬሽን ተግባራትን በስትራቴጂው መሰረት በውጤታማነት ለመተግበር ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ የኮሙኒኬተሮች ፎረም በአመት ሁለት ግዜ የሚካሄድ ሲሆን አላማውም በዘርፉ ያለውን የኮሚኒኬሽን ስራ እስትራቴጂክ በሆነና በተቀናጀ መልኩ በመተግበር ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡

የፎረሙ ተሳታፊዎች ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ፣ የፌደራል እና የክልሎች ቴክኒካል ቮኬሽናል ትምህርትና እና ስልጠና ኤጀንሲዎች፣ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ኤጀንሲ፣ ከዘጠኙ ክልሎችና ከሁለቱ የከተማ መስተዳድሮች የትምህርት ቢሮና የቴክኒካል ቮኬሽናል ትምህርትና እና ስልጠና ኤጀንሲ ቢሮዎች እንዲሁም ከሰላሳ ሶስቱ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የኮሚኒኬሽን ሃላፊዎች እና የተወከሉ ባለሙያዎች ናቸው፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡