የአስቸኳይ ጊዜ የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ተጀምሯል

የአስቸኳይ ጊዜ የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ተጀምሯል

በኤልኒኖ ክስተት ሳቢያ የተፈጠረው ድርቅ በትምህርት ላይ እያስከተለ ያለውን ተፅዕኖ ለመቋቋም ሲባል የአስቸኳይ ጊዜ የትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም በሁለተኛው ሴሚስተር ተጀምሯል፡፡

Ato Yassabu - School Improvement Director

በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ያሳቡ ብርቅነህ እንደተናገሩት በሃገራችን የተከሰተው ድርቅ ወላጆች ለልጆቻቸው የሚያስፈልግ ምግብና ግብዓቶችን አሟልተው ወደ ትምህርት ቤት የመላክ አቅማቸውን የሚፈታተን በመሆኑ ተማሪዎች በሚፈለገው ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳይከታተሉ ተፅእኖ አሳድሯል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የችግሩን መጠን በማጥናት ተመጣጣኝ ምላሽ ለመስጠት ባለሙያዎችን ወደ ትግራይ፣ አፋር፣ አማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ደቡብ //ህ፣ ሀረሪ ክልሎች እንዲሁም ድሬዳዋ አስተዳደር ካውንስል በማሰማራት መረጃዎች የማሰባሰብ ስራ ሲሰራ መቆቱን የገለፁት አቶ ያሳቡ መንግስት ድርቁ በከፍተኛ ሁኔታ በተባባሰባቸው አካባቢዎች ለሚማሩ አንድ ሚሊዮን 187 701 ተማሪዎች የአስቸኳይ ጊዜ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ማስተግበሪያ የሚሆን 230 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ ለክልሎች እንዲሰራጭ  ተደርጓል ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በመስክ በተደረገ የክትትልና ድጋፍ ተግባራት በተገኙ መረጃዎች መሰረት እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች 42 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ 735ሺህ 150 ተማሪዎች ደብተር፣ስክሪብቶና እርሳስ እንዲከፋፈል መደረጉንም ከአቶ ያሳቡ ገለጻ ለማወቅ ተችሏል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡