የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀሙን ገመገመ

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት 2008 . የስድስት ወራት የቁልፍና የአብይ ተግባር አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ከክልሎችና  ህዝብ ክንፎች ጋር ከጥር 16-19/2008 አካሂዷል፡፡Inspection Director_Ato Asfaw

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ዳይሬክተር አቶ አስፋው መኮንን የእቅድ አፈፃጸሙን አስመልክተው እንደተናገሩት በመላው ሃገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 40 በመቶ በሚሆኑት ላይ የኢንስፔክሽን ስራ ለማከናወን መታቀዱን ጠቁመው  የክልሎች የአፈጻጸም ደረጃ የተለያየ ቢሆንም በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ዕቅዱን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የባለሙያ እጥረት፣ በክልሎች በኩል ለስራው በቂ በጀት አለመመደብ እንዲሁም የባለሙያ ፍልሰትና የመሳሰሉት ችግሮች በኢንስፔክሽን ስራው ላይ ጫና መፍጠራቸውን የጠቆሙት አቶ አስፋው በቀጣይ ችግሮቹን ለመቅረፍ ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በጋራ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡

ባለፉት ስድስት ወራት የትምህርትና ስልጠና ስርዓት ውጤታማነትን ለማሻሻል የሚያግዙ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን የገለፁት ዳይሬክተሩ ከአራቱ ታዳጊ ክልሎች ለተውጣጡ 70 ወንድና ሴት እንዲሁም ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ 95 ሰልጣኞች እና 20 የኢንስፔክሽን፣ የመረጃና የትንተና ባለሙያዎች በአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን መመሪያ፣ ማዕቀፍና የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግለ ግምገማ ማዕቀፍ ዙሪያ ያተኮረ  ስልጠና መሰጠቱንም አቶ አስፋው ገልጸዋል፡፡

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን የትምህርት ቤት አካባቢ፣ የትምህርት ቤት አመራርና አስተዳደር፣ መማር ማስተማር፣ ከወላጆችና ከህብረተሰቡ ጋር ያለ ግንኙነት እና የተማሪዎች ውጤትን መሠረት ያደረገ ሲሆን ባሁኑ ወቅት 26 ስታንዳርዶች መሰረት በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች በሚገኙ የተመረጡ ትምህርት ቤቶች ላይ የኢንስፔክሽን ስራ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝም ከአቶ አስፋው ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የአጠቃላይ ትምህርት የኢንስፔክሽን ዳይሬክቶሬት በሀገሪቱ የሚሰጠውን የቅድመ መደበኛ፣ አማራጭ መሰረታዊ ትምህርት፣ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በተጨማሪም የተግባር ተኮር ጎልማሶች ትምህርት እና የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማትን ጥራት የማስጠበቅ ኃላፊነት ከተሰጣቸው የስራ ክፍሎች መካከል አንዱ ነው፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡