የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ፖሊሲው የዜጎችን በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማር መብት ያረጋገጠ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ፖሊሲው የዜጎችን በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማር መብት ያረጋገጠ መሆኑ ተገለፀ፡፡

... ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡሩ / ጥላዬ ጌቴ 27ኛው የግንቦት 20 የድል በዓል አስመልክቶ ትምህርትና ስልጠና ስርዓቱ 27 ዓመት ጉዞ ያስገኛቸው ውጤቶች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ክቡር ሚኒስትሩ ይህ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ከመቀረፁ በፊት ከትምህርት ተደራሽነት ፣ፍትሃዊነትና ተገቢነት ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት መሆኑን አስታውሰው ይህ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ እነዚህን ችግሮች በሚገባ መልሷል ብለዋል፡፡ከምንም በላይ ፖሊሲው የዜጎችን በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማር እድል አረጋግጧል፤ በዚህም በአሁኑ ሰዓት 51 የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት እየተሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡ክቡር ሚኒስትሩ አክለውም ፖሊሲው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ለሁሉም ዜጎች በፍትሃዊነት እንዲዳረስ አድርጓል፣በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት ዜጎች ተጠቃሚ መሆናቸውን እንዲሁም ለአንድ ሀገር እድገት የሰለጠነ የሰው ሃይል መፍለቂያ የሆነውን የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በማስፋፋትና በቂ የሰው ሃይል በማፍራት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገቱ ላይ ዘርፈ ብዙ ቱሩፋቶች እንደተመዘገቡ አብራርተዋል፡፡ ነገር ግን ጥራትና ተገቢነትን ከማረጋገጥ አኳያ የበለጠ መስራትና ማተኮር እንደሚገባ የተገመገመ መሆኑን ገልፀው ይህን ለመፍታት ስርዓተ ትምህርቱን በየጊዜው የማሻሻል፣የመምህራንን አቅም በቀጣይነት የመገንባት ፣የትምህርት አሰጣጡን የበለጠ በቴክኖሎጂ የመደገፍ እና የትምህርት ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀትን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን በመግለጫቸው የጠቀሱ መሆኑን የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዘገባ ያመለክታል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡