ለወረዳ ትምህርት አመራሮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሠጠ

ለወረዳ ትምህርት አመራሮች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሠጠ

በቅርቡ በመላ ሀገሪቱ ሊሰጥ ለታቀደው የወረዳ ትምህርት አመራሮች የአመራርነት የአቅም ግንባታ የአሠልጣኞች ሥልጠና ከዘጠኙ ክልሎችና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ከመቶ ስልሳ በላይ ለሚሆኑ በክልልና በዞን መዋቅር ደረጃ ላሉ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ከክልሎችና ከዩኒቨርሲቲዎች በተውጣጡ አሠልጣኞች በአሥራ አንድ የአመራርነትና ከአመራርነት ሚና ጋር በተያያዙ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከሚያዚያ 3-8/2010 . በአዳማ ከተማ ተሰቷል።

በትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሐመድ አህመዲን ሥልጠናውን በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት የትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ ራሱን ጨምሮ ለሁሉም ዘርፎች የሰው ኃይል አቅራቢ እንደመሆኑ መጠን የዘርፉ ሁለንተናዊ ስኬት ሁሉንም ዘርፎች ለስኬት የሚያመቻች፤ የዘርፉ ሁለንተናዊ ውድቀት ሁሉንም ዘርፎች ለውድቀት የሚያመቻች ስለሆነ የተሰጠው ኃላፊነት ድርብርብና እጅግ በጣም ከባድ መሆኑን ጠቅሰው በየደረጃው ያሉ የትምህርት አመራሮች፣ባለሙያዎችና ባላድረሻ አካላት ለትምህርት ጉዳይ የቅድሚያ-ቅድሚያ በመስጠት የድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ክቡር አቶ መሐመድ ለወረዳ ይህ ሥልጠና ለትምህርት ተቋሞቻችንና ለህብረተሰቡ ቅርብ ለሆኑት ለወረዳ አመራሮች ሳይሸራረፍ እንዲደርስና ወደ ተግባርም እንዲቀየር ከአሰልጣኞችና ሰልጣኞች በአንድም ሆነ በሌላው ብዙ እንደሚጠበቅ ገልጸው ሥልጠናው የተሳካ እንዲሆን ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል።
በሚኒስቴር /ቤቱ የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር / አሰፋሽ ቱሉ በሥልጠናው መክፈቻ ወቅት እንደተናገሩት ሥልጠናውና ርዕሶቹ የተለዩት ሚኒስቴር /ቤቱ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ሲያካሂዳቸው የነበሩ የክትትልና ግምገማ ተጨባጭ ግብረ-መልሶች እና ይህንንም መሠረት በማድረግ ባካሄዳቸው ጥናቶች መሠረት መሆኑን ገልጸው ሥልጠናው በሚቀጥሉት ቅርብ ጊዜያት በመላው ሀገሪቱ በወረዳ ደረጃ ለሚገኙ ከአምስት በላይ ለሚሆኑ የትምህርት አመራሮች እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡