በህዝብ አስተያየት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ እና በቀውስ ኮሚዩኒኬሽን ዙሪያ በአዳማ ከተማ ሥልጠና ተሰጠ

በህዝብ አስተያየት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ እና በቀውስ ኮሚዩኒኬሽን ዙሪያ በአዳማ ከተማ ሥልጠና ተሰጠ

በኢ.... የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች /ቤት የአቅም ግንባታ እና የጥናትና ምርምር ጀነራል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሀዱሽ ካሱ ለትምህርቱ ዘርፍ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተዘጋጀው የሥልጠና መድረክ ላይ ተገኝተው የህዝብ አስተያየት ዳሰሳ ጥናት በማካሄድ ላይ ሥልጠነ በሰጡበት ወቅት የህዝብ አስተያየት ዳሰሳ ጥናት ለህዝብ ግኝኑነት ሥራው መነሻውና መድረሻው እንደሆነ ገልጸዋል። በዚህም መሠረት ጥናቱም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ደረጃ ለመለየት፣ የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ፣በሆነ ጉዳይ ላይ የህብረተሰቡን አቋም ለመለየት፣ አዝማሚያዎችን ለማስተዋልና ተጽዕኖ ለማሳደር አንደሚከናወን ጠቁመው የህዝብ ግንኙነት ሥራውን ለማቀድም ሆነ በአፈጻጸም የመጣውን ለውጥ (ውጤት) ለመለካት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በመሆኑም በህዝብ ግንኙነት ሥራ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠርና መልካም ገጽታን ለመገንባት በህዝብና በመንግስት መካከል ያለው ግንኙነት የህዝብ አስተያየት ጥናትን መሰረት ያደረገ ሊሆን እንደሚገባ አቶ ሀዱሽ አስረድተዋል።
በጽ/ቤቱ የግንኙነትና ገጽታ ግንባታ ጀነራል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆኑት አቶ አብዱራህማን ናስር በመድረኩ ተገኝተው የቀውስ ጊዜ ኮሚዩኒኬሽንን አስመልክተው ሥልጠና የሰጡ ሲሆን በገለጻቸው በቀውስ ወቅት የሚተላለፉ የህዝብ ግንኙነት መልዕክቶች ለወቅቱ የሚመጥኑና በጥንቃቄ የተዘጋጁ ሊሆኑ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ቀውስ በሚያጋጥምበት ወቅት ከተለያዩ ምንጮች ስፍር ቁጥር የሌላቸው መረጃዎች የሚፈሱ በመሆናቸው እውነተኛ፣ ወቅታዊና ግልጽ መረጃዎችን ለመለየት አስቸጋሪ ስለሚሆን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች እጅግ ውስን ቢሆንም ጥራት ያለውን መረጃ ብቻ በመለየት መጠቀም እንደሚገባቸው አስታውቀዋል፡፡
የቀውስ ኮሙኒኬሽን ሥራ አስቀድሞ ማቀድን፣ታማኝ ምንጮች መጠቀምን፣ለሚዲያ ፈጣን ምላሽ መስጠትን፣ ከክስተቱ ጋር አግባብነት ያለው የአነጋገር ዘዴ መጠቀምን፣የቀውሱን መጠን በልኩ መግለጽን፣ ቀውሱን በተመለከተ ህብረተሰቡ በሌሎች የመረጀ ምንጮች እንዳይወዛገብ በቀጣይነት ለህብረተሰቡ መረጃ እንደሚሰጡና ተዓማኒነት ያለው የመረጃ ምንጭ ሆነው እንደሚያገለግሉ ተስፋ መስጠትና ይህንኑ እውን ማድረግ እና የመሳሰሉትን ቴክኒክና ዘዴዎችን የሚፈልግ ተግባር መሆኑንም አቶ አብዱራህማን ጨምረው አስረድተዋል፡፡
በስልጠናው ላይ በተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። የሥልጠናው ተሳታፊዎችም ከዘጠኙ ብሄራዊ ክልሎች ትምህርት ቢሮዎች ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ትምህርት ቢሮዎች ፣ከትምህርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊዎች ነበሩ።


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡