ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከለኛ አመራሮች በሥርዓተ ጾታ ማካተት ላይ ያተኮረ ስልጠ ተሰጠ፤

ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከለኛ አመራሮች በሥርዓተ ጾታ ማካተት ላይ ያተኮረ ስልጠ ተሰጠ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ በሥርዓተ ጾታ ማካተት ላይ ያተኮረ 04 - 09/07/2010. ስልጠና ተሰጠ፡፡ ስልጠናው በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር / ኤልሳቤ ገሠሠ የመክፈቻ ንግግር የተከፈተ ሲሆን የስርዓተ ጾታ ስራን በሁሉም ተግባራት አካቶ እንዲሰራ ስምምነት የተደረገ ቢሆንም ተፈላጊው ውጤት ግን አለመገኘቱን አብራርተው ለዚህም ቀጣይ ሁሉም የራሴ ስራ ነው ብሎና ትኩረት ሰጥቶ መስራትና መደገፍ እንደሚገባው ዳይሬክተሯ በንግግራቸው ገልጸዋል፡፡
ዳይሬክተሯ በስልጠናው ላይ ለተገኙት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከለኛ አመራሮች ከዚህ ስልጠና በኋላ የምታገኙትን ግንዛቤ ስንቅ በማድረግ ቀጣይም የስርዓተ ጾታን ተግባራት በእቅዳችሁ ውስጥ ማካተትና አፈጻጸሙንም ውጤታማ ማድረግ ይጠበቅባችኋል በማለት ጨምረው አብራርተዋል፡፡
አቶ ብርሃኑ አረጋ በትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ በስርዓተ ጾታ ጽንሰ ሀሳቦች ላይ ሰፊ ማብራሪያ በመስጠት በዓለም አቀፍና በሀገራችን ደረጃ ለስርዓተ ጾታ ትኩረት በመስጠት በተቀመጡ ህጎችና ስምምነቶች ላይ ሰፊ ገለጻ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም በዓለማችን ድህነትን ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት፣ ለሰብአዊ መብቶች አያያዝ፣ ለዲሞክራሲ ሥርዓት መስፈን እና መልካም አስተዳደርንም ለመገንባት የሴቶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የሥርዓተ ጾታ ጉዳይን በሁሉም ዘርፍ አካቶ መስራት ትኩረት እንደሚሻ ገልጸዋል፡፡
በስልጠናውም የሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የእቅድ፣ የፋይናንስና የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡