የስልጤ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በስኬት ጎዳና

የስልጤ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በስኬት ጎዳና

በሀገራችን ታሪክ በንግድና ቢዝነስ ስራ ታታሪነት የሚታወቀው የስልጤ ማህበረሰብ በትምህርት ዘርፍ ብዙም አይታወቅም ነበር፡፡ ታሪክ ተቀየረና ዛሬ ላይ የዞኑ ህዝብ ለትምህርት ዘርፍ ልማት ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ልጆቹን እያስተማረ ይገኛል፡፡በዚሁ መሠረት በቅርብ ዓመታት በዞኑ ስር የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች የስልጤ 2 ደረጃ ትምህርት ቤትን ጨምሮ በትምህርት ስራ አፈጻጸም የተሸለ ውጤት በማስመዝገብ እንደ ክልል ተሸልመዋል፡፡
የስልጤ 2 ደረጃ ትምህርት ቤት በደቡብ ክልል ስልጤ ዞን ከአዲስ አበባ በስተደቡብ አቅጣጫ 135 / ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ 1945. 1-6 ክፍል ትምህርት ለመስጠት የተመሠረተው ትምህርት ቤቱ 2000 . ወደ 2 ደረጃና መሠናዶነት አድጓል፡፡ ትምህርት ቤቱ በክልሉ ካሉት ሁሉ 2 ደረጃ ትምህርት ቤቶች 2009. የተሻለ የትምህርት ስራ አፈጻጸም በማሳየቱ እንደ ደቡብ ክልል ተሸልሟል፡፡
የትምህርት ቤቱ ርዕሠ መምህር አቶ አብዱልመናን ሡልጣን የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡትን የሌሎች ትምህርት ቤቶች ተሞክሮና ልምድ በመጎብኘት የስልጤ ወረዳና የዞኑን ሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር ስለ ትምህርት ጥቅም ምንም ግንዛቤ ያልነበረው ሕዝብ 2008. ብቻ 420000 ብር ገቢ በማሰባሰብ፣ ክልሉን ጨምሮ ቃል ከተገባው ጋር 5 ሚሊዮን ብር ገቢ እየተሰበሰበ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡ በገንዘቡም ብዙ ግብዓቶች እየተሟለ ይገኛል፡፡
ቀደም ብሎ የመልካም አስተዳደር፣ የዲሲፕሊን፣ የመረጃ አደረጃጀት፣ የመጠነ መድገምና ማቋረጥ፣ አሳታፊ የማስተማር ስነ ዘዴ፣ የግብዓት አቅርቦት፣ ሳምንታዊ የትምህርት ዕቅድ አዘገጃጀት፣ የተከታታይ ምዘና አተገባበር፣ የስፖርት ሜዳ እና የትምህርት ቤት አደረጃጀቶች ችግሮች የነበሩበት ሲሆን ትምህርት ቤቱ እንቅፋቶቹን 2008. ጀምሮ በመቅረፉ ውጤታማ እንደ ሆነ ርዕሠ መምህሩን ጨምሮ የዞኑ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ነስረዲን ከማል አብራርተዋል፡፡
ስነምግባርን አስመልክቶ በማርፈድ፣ በማቋረጥ፣ አጥር ሾልከው መሄድ፣ ፈተና ኩረጃ፣ ከትምህርት ቤት መቅረት ዙሪያ ተደጋጋሚ ውይይት በማድረግ ተማሪዎቹ ፊታቸውን ወደ ትምህርት በማዞር ሙሉ ጊዜያቸውን ለትምህርትና ፈጠራ ስራ እንዲያውሉ ተደርጓል፡፡ የተማሪዎች ፓርላማ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ዲስፒሊን ላይ ይሰራል፣ ተማሪዎቹ እስከ ማታ 6 ሰዓት በትህርት ቤቱ ቤተ-መጽሃፍት እንዲያነቡ መምህራን በፈረቃ እየረዱ መሆኑን፣ ለዚህም ከትምህርት ቅጥር ውጪ ላይ የአካባቢው ህብረተሰብ ተራ በተራ ከከተማው ፓሊስ ጋር በመሆን ጥበቃ እንደሚያደርግላቸው ምክትል ርዕሰ መምህራን አቶ ኑሪ ሽኩር እና አቶ ታሪኩ ዳዊት ይገልጻሉ፡፡
የስርዓተ ጾታ እኩልነት በትክክል እየተሰራበት መሆኑን ከተማሪዎች ተሳትፎ ጨምሮ በአመራርም ሴት መምህራን 2 ትምህርት ክፍል ሃላፊዎች፣ የክበባት ሃላፊዎች ሲሆኑ፣ ከየክፍሉ ተጠሪ ተማሪዎች ሃላፊ ወይም ምክትል ሃላፊ ሴት ተማሪ መሆኑን ርዕሰ መምህሩ ገልጸዋል፡፡
ትምህርት ቤቱ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት፣ ከህብረተሰቡ፣ ከውስጥ ገቢ የሚገኝ የገቢ ምንጭ ያለው፣ የምድረ ግቢው ማራኪና በቂ የትምህርት ግብዓቶች መኖሩ፣ ትምህርት ቤቱ አሁንም ወደ ፊት ለመጓዝ ሰፊ ሃይልና ዕድል እንዳለው ተገንዝበናል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡