የሠላምና የብቃት ተምሳሌት፣ የአዳባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

የሠላምና የብቃት ተምሳሌት፣ የአዳባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

ለመልካም አስtዳደር ማስፈን አላማ ወደ ዛሬው የምዕራብ አርሲ ዞን ከተጠቀለሉት ባሌ ዞን ስር ከነበሩት አንዱ የሆነው የአሁኑ ምዕራብ አርሲ የአዳባ ወረዳ አዳባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኘው የአዳባ 2 ደረጃ ትምህርት ቤት ከርዕሠ መድናችን አዲስ አበባ በስተ ደቡብ ምስራቅ 345 ኪሎሜትር አከባቢ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ትምህርት ቤቱ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ከሚገኙት ሁሉ 2 ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተወዳድሮ 2009 የትምህርት ዘመን 1 ደረጃ ያገኛ ሲሆን ትምህርት ቤቱን ለዚህ ደረጃ ያበቃ ሚስጥር ጠንካራ የትምህርት ልማት ሰራዊት መፈጠሩን፣ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለተማሪዎች መዳረሱ ፣የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት መኖር፣ ከምንም በላይ ስለ ትምህርት ጥቅምና ምንነት ለሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት በየጊዜው መገለጽ ትምህርት ቤቱ ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ መሠረት መሆኑን የሚገልጹት የትምህርት ቤቱ ርዕሠ መምህር አቶ ሁሌ ሳዶ ናቸው፡፡
በማንኛውም ጊዜ ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት አርማው የሆነው ትምህርት ቤቱ የአከባቢውን ማህበረሰብ ቢሎም ወላጆችን በተደጋጋሚ በማሳተፍ እንዲሁም መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመጣመር የተለያዩ ፋሲሊቲዎችና የትምህርት ቁሳቁሶችን እንዲሟሉ፣ ትምህርት ቤቱ የራሴ ነው የሚል መንፈስ በሁሉም ዘንድ እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚከናወኑ የትምህርት ስራዎች በሁሉም ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ የተያዘበት መሆኑን የሚያሳየው ከተማሪዎች እስከ አመራሮች አንድ ዓይነት ግንዛቤ መኖሩን እንዲሁም በዕቅድ ብቻ የቀረ ሳይሆን መሬት ላይ የወረደ ስራ መሰራቱን የሚያሳይ መሆኑን በተለያዩ ዶኩሜንቶችና ናፋይሎች በገላጭነት ሰፍሯል፡፡
1938. በአንደኛ ደረጃ 1-4 ብቻ ትምህርት መስጠት የጀመረው ትምህርት ቤቱ 1979 . ወደ 2 ደረጃነት በማደግ በአሁኑ ሰዓት 67 መምህራን፣ 10 የድጋፍ ሠጭ ሠራተኞች 9 እስከ 10 ክፍል ላሉት 1788 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡