ዜናዎች ዜናዎች

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የትምህርት ሚኒስቴር ቀዳሚ ሆነ

28 የፌዴራል መንግስት ተቋማት መካከል በተደረገው ምዘና የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የትምህርት ሚኒስቴር ቀዳሚ ሆነ፡፡

ምዘናው በዋናነት የፌዴራል ሴክተር መስርያ ቤቶች ስርዓተ ጾታ ጉዳዮችን በፖለቲካዊ በኢኮኖሚያዊና በማህበራዊ ዘርፎች ማካተትና ሴቶችን ማብቃት እዲሁም ተጠቃሚነታቸውንና በመከካከላኛና በከፍተኛ አመራርነት ተሳትፎ ለማጎልበትና ለማብቃት በሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ሚኒስቴርና በብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን አማካኝነት የተካሂደ ነው፡፡

እነዚሁ ተቋማት ባስቀመጡት የስርዓተ ፆታ ማካተት፤ ተቋማዊነትና የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መከታተያ፤ መመዘኛና ደረጃ ማዕቀፍ መሰረት ከፖሊሲና ህግ፤ተቋማዊ መዋቅር፤ አቅምና ክህሎትን ማጎልበት በቅድመ ሁኔታዎች ሲቀመጡ፤ ስርዓተ ፆታን በማካተት ሂደትም የእቅድ ዝግጅት አፈጻጸምና ክትትልና ግምገማ እንዲሁም ንቅናቄ መፍጠር በትብብርና ቅንጅት ስራ ላይ ያተኮሩ መገምገሚያ ነጥቦች ተካተዋል፡፡

የኢ.... ትምህርት ሚኒስቴር የስርዓተ ፆታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ለምዘናው የተቀመጠውን መገምገሚያ መስፈርት በማሳካት 76.24 ከመቶ በማምጣት 28 የፌዴራል ሴክተር መስሪያ ቤቶች ቀዳሚ እንዲሆን አስችሎታል፡፡የስርዓተ ፆታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ገሰሰ ውጤቱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የከፍተኛና የመካከለኛ አመራር እንዲሁም የአጠቃላይ ሠራተኛውና የሁሉም የትምህርት ባለድረሻ አካላት ቁርጠኝነት ድምር ውጤት ነው ብለዋል፡፡ ይህም 5ኛው የትምህርት ዘርፍ ልማት ዕቅድ በተቀመጠው መሠረት በየደረጃው ያሉት አመራሮች የተቋማዊ መዋቅር ለውጥ የሴቶች ተሳትፎና ለአመራርነት የማብቃት ስራ ተሰርተዋል፤ ክትትልና ድጋፍም ተደርገዋል ብለዋል፡፡

ሆኖም ግን ዳይሬክተሯ እንደገለጹት ሀገራችን 2025 መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ እንዲትሰለፍ የበለጠ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤ የተለያዩ የጎንዮሽና የሌሎች ሀገራትን ልምድ በመቅዳት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችንና የልምድ ልውውጦችን ከማዘጋጀት አንጻር አሁንም ገና ይቀረናል ይላሉ፡፡ በሚቀጥሉ ጊዜያት አነስተኛ ነጥብ ያሰጡን እንደነጥናትና ምርምርያሉት ጉዳዮችን ነጥለን እነዛ ላይ እንሰራለንም ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በምዘናው መሠረት ስለ ስርዓተ ጾታ ገና ያልተገነዘቡ፤ ግንዘቤው ያላቸው ግን ያልሰሩበት፤ተገንዝበው ወደ ስራም ገብቶ ውጤት ያላሳዩ እና ወደ ስራ ገብቶ በቁርጠኝነት በመስራት ውጤት ያስመዘገቡ ተቋማት ተብለው ተለይተዋል ያሉት ወይዘሮ ኤልሳቤጥ ሌሎች ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሀገራችንን ሁለንተናዊ ልማት እውን ለማድረግ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸውና ከትምህርት ሚኒስቴር ልምድ መቅሰም እንዳለባቸው አብራርተዋል፡፡No comments yet. Be the first.
ዜናዎች

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ አስታወቁ፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህብረ-ብሔራዊነትና ኢትዮጵያዊነት የሚገነባባቸው ተቋማት እንጂ ተግባራቸው በጥቂት ችግር ፈጣሪዎች የሚስተጓጎል አለመሆኑንም ገለጹ 141ሺህ አዲስ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመማር ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምረቃ ትምህርት መስኮች የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና (የመውጫ ፈተና) ልተገበር ነው

ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምርቃ ትምህርት መስኮች ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና (የመውጫ ፈተና) ወስደው አጥጋቢና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን በተለይም የምሩቃንን ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ አጠቃላይ ምዘና ወይም የመውጫ ፈተና መስጠት የምሩቃንን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለመመዘን የላቀ ሚና ከመጫወቱም በተጨማሪ የተመራቂ ተማሪዎች በራስ መተማመን ያጎለብታል፡፡

የምርምርና የፈጠራ ስራ ውድድር ኤግዚቪሽን ተካሄደ

የሂሳብና ሣይንስ ትምህርቶች ማሻሻያ ማዕከል ከስቴምስ ሲነርጂ ፣ከዩኔስኮ እና ከኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር "በሣይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ የበለፀገ ህብረተሰብ ለዘላቂ ሠላምና ልማት "በሚል መሪ ቃል አገር አቀፍ የምርምርና ፈጠራ ስራ ውድድር ኤግዚቪሽን በኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ተካሄደ፡፡ የምርምርና የፈጠራ ስራ አውደ- ርዕይ መከፈቱን አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ የኢትዮጵያን ሣይንስ ለማበልፀግ የተቋቋመ መሆኑን አስታውሰው ይህ ማዕከል የህብረተሰቡን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ እንዲሁም ቴክኖሎጂን የመጠቀም አቅሙን ለማጎልበት ለማስተማርና የሣይንስ ፖርሽን ለመፍጠር የተሰራ ሲሆን ቋሚ የሳይንስ ማዕከል ለመፍጠር ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ በመሆኑም በቅርቡም የሳይንስ ማዕከሉ ወደ ስራ ይገባል በዚህም ወጣቱ ወደ ሣይንስ በሄደ ቁጥር የሀገራችን ተስፋ እየለመለመ ይሄዳል ብለዋል፡፡

የሥርዓተ-ፆታ ማካተትና ተቋማዊ ማድረግ መከታተያ፣ መመዘኛና በደረጃ የመለያ ማዕቀፍ ላይ ስልጠና ተሰጠ

የትምህርት ሚኒስቴር ሥርዓተ ፆታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሁሉም የሥራ ክፍሎች እና ከተጠሪ ተቋማት ለተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ባለው ስልጠና የሁለተኛ ቀን ውሎ በሥርዓተ-ፆታ ማካተትና ተቋማዊ ማድረግ መከታተያ፣ መመዘኛና በደረጃ የመለያ ማዕቀፍ ላይ ስልጠና ሰጠ ፡፡ ስልጠናውን የሰጡት በዳይሬክቶሬቱ የስርዓተ ፆታ ክትትልና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ብርሃኑ አረጋ ሲሆኑ የዚህ ስልጠና ዋና አላማ በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ያሉ የስራ ክፍሎች የሥርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ማብቃት ተቋማዊ ለማድረግ የሚያከናውኑትን ተግባራት በመመዘንና ተከታታይ ድጋፍ በመስጠት የሥርዓተ ፆታ እኩልነት በሁሉም ዘርፍ ለማረጋገጥ ብሎም የሀገራችንን የልማት ራዕይ ለማሳካት ነው ብለዋል፡፡

የመንግስታዊና ግብረሰናይ ድርጅቶች የጋራ ፎረም ውይይት ተካሄደ፡፡

ዛሬ ጥቅምት 20/2010 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አዳራሽ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በትምህርት ስልጠና ዘርፍ የ2010 ዓ.ም ዋና ዋና ዕቅዶች ላይ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ተገኝተው የመድረኩን አላማ የገለጹት በትምህርት ሚኒስቴር የእቅድ ዝግጅትና ሃብት ማፈላለግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ግርማ የመድረኩ ዋና አላማ የትምህርት ሴክተሩ እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ማድረግ ነው ብለዋል፡፡