የትምህርት ሚኒስቴር በተፈጥሮ ሳይንስና ምህድስና ትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎችን ሸለመ

የትምህርት ሚኒስቴር በተፈጥሮ ሳይንስና ምህድስና ትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎችን ሸለመ

የኢ... ትምህርት ሚኒስቴር ሥርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሥርዓተ ጾታና ባለ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በተፈጥሮ ሳይንስና ምህድስና ትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከአንደኛ እስከ አምስተኛ አመት ያሉ ሴት ተማሪዎች፣ ድጋፍ ላደረጉላቸው መምህራንን እና አመራሮች  የማበረታቻ ሽልማት ሰጠ፡፡ በዩኒቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አደራሽ ሚያዝያ 27/2009 በተዘጋጀው ሥነ-ሥርዓት ላይ አሥር ሴት ተማሪዎች፣ ሦስት መምህራን እና ሁለት መካከለኛ አመራሮች ከትምህርት ሚኒስቴር የተበረከተላቸውን ዴል ላፕቶፕ ኮምፒዩተር በትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ጾታ ዳይሬክተር ከሆኑት ከወ/ ኤልሳቤጥ ገሠሠ እና በዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ከዶክተር ይለማሪያም ብርቄ እጅ ተቀብለዋል።

 

ክተር ይለማሪያም ብርቄ በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ  ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በዚህ የትምህርት መስክ ውስጥ ከመሳተፋቸውም በላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎችና ሴቶቹ ውጤታማ እንዲሆኑ አርኣያነት ያለው ከፍተኛ ሥራ ለሠሩ መምህራንና አመራሮች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ሴት ተማሪዎችም ለሌሎች በቀጣይ ወደ ከፍተኛ ትምህርት የሚቀላቀሉ ሴት አህቶቻቸውና በአሁኑ ወቅት በመማር ላይ ያሉ ጓደኞቻቸው እንደ እነሱ ውጤታማ እንዲሆኑ የአርኣያነት ሚናቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። ሴት ተማሪዎችን፣መምህራንና ሠራተኞችን ደግፈው ውጤታማ እንዲሆኑ ያደረጉ መምህራንና አመራሮችም ከራሳቸው አልፈው ይህንን አርኣያነት ያለውን መልካም ልምዳቸውን ወደ ጓደኞቻቸው፣የትምህርት ክፍላቸውና ኮሌጃቸው በማስፋት ቀጣይነት ባለው መልኩ ከነዚህም በላይ በርካቾች ውጤታማ እንዲሆኑ ኃለፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። / /ማሪያም  የትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት ይህን መሰል ማበረታቻ በማዘጋጀቱ ያለውን አድናቆትና ምስጋና በራሱና በዩኒቨርሲቲው ስም አቅርበዋል።

 

/ ኤልሳቤጥ ገሠሠ በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ መክፈቻ ወቅት አጠቃላይ መርሃ-ግብሩን በተመለከተ ባደረጉት ንግግር ይህ የሽልማት መርሃ ግብር ከየትውልዱ 2008 በጀት አመት በእእቅድ አፈጻጸማቸው አንደኛ በወጡት ሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የሚካሄድ መሆኑንና በዚሁ መሠረት ዩኒቨርሲቲው 2008 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸሙ የራሱ ትውልድ ከሆኑት ከሁለተኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የአንደኝነት ደረጃን ተጎናጽፎ 26ኛው የትምህርትና ሥልጠና ጉባኤ በመሸለሙ እንደሆነ ገልጸዋል። ሽልማቱም በነዚህ ውጤታማ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ መሠረት አድርጎ እንዲካሄድ የተፈለገበት ዋነኛ ምክንያት በሁለንተናዊ የዩኒቨርሲቲዎች ስኬት ውስጥ የሴቶች ድርሻ ምን ያህል እንደ ሆነ ለማየትና የበለጠ እንዲጠናከር ለማድረግ እንደሆነ አስገንዝበዋል። መርሃ ግብሩ ከዚህ ቀደም በሁሉም ትምህርት መስኮች ላይ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ውጤታማ ሴት ተማሪዎችን ላይ በማተኮር ሲካሄድ የነበረ መሆኑን ገልጸው በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክም ቢሆን የሴቶች ትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት የሚፈለገው ደረጃ ላይ ደርሷል ባይባልም የተፈጥሮ ሳይንስና ምህንድስና የትምህርት መስክ ያህል የከፋ እንዳልሆነ አስገንዝበዋል። በወቅታዊ የሀገራችንን የሰው ኃይል ፍላጎት መሠረት 7030 የተማሪዎች ቅበላ አንጻር ከመቶ ተማሪዎች 70ዎቹ ገብተው እየተማሩ ባሉበት በዚህ በርካታ ተማሪዎችን በሚያቅፍ መስክ ላይ ሴቶች አይችሉትም በሚል ኋላ ቀር አስተሳሰብ ምክንያት በመስኩ ላይ የሴቶች ተሳትፎ እጥረት እጅግ በጣም የከፋ ደረጃ ላይ የሚገኝ በመሆኑና እዚህ መስክ ላይ ትኩረት ሰጥቶ አለመሥራት አጣቃላይ ሀገራዊ የከፍተኛ ትምህርት የሴቶች ተሳትፎንና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትንም ስለምጎዳ ጭምር ይህ ተሳትፎ ወደሚፈለገው ደረጃ አስክደርስ ድረስ በዚህ መስክ ላይ ብቻ አትኩረው እንዲሠሩ ነበራዊ ሁኔታው ያስገደዳቸው መሆኑን አብራርተዋል።

 

ይህ የሽልማት መርሃ-ግብር ለአሥር ሴት ተማሪዎች፣ለሦስት መምህራንና ለሁለት አመራር በድምሩ 15 ታታሪና ውጤታማ ሰዎች እውቅና ከመስጠት በተጨማሪ ከያንዳዳቸው በስተጀርባ ያሉትን በርካታ ሰዎች ለማነሳሳት ያለመ እንደሆነ ገለጸው ከዚህ በኋላ ሴት ተማሪዎች በሆነ የትምህርት መስክና ክፍል ተሳትፈው ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መመረቃቸውን ብቻ እንደውጤታማነት እየቆጠርን የሚንዘናጋበት ሁኔታ ተለውጦ የሴቶች ውጤታማነት የሚለከው ሴቶች ከወንዶች እኩል በሁሉም የትምህርት መስክና ክፍል ገብተው ከመመረቃቸውም በተጨማሪ ባስመዘገቡት ውጤት ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

 

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከውጤታማ ሴት ተማሪዎች መካከል አራቱ የአጠናን ሥልታቻውንና ሌሎች ስኬታማ የሆኑባቸውን መልካም ልምዶች ለታዳሚ ተማሪዎች አካፍለዋል። የዩኒቨርሲቲው የሥርዓተ ጾታና ባለዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት 2009 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የሥራ ክፍሉ ዳይሬክተር በሆኑት በወ/ ሃይማኖት ብችል ቀርቧል። የተሸላሚ መምህራንና አመራሮች ዋና ዋና ሥራዎች በአዘጋጁ ክፍል አማካኝነት ቀርበዋል።


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡