ትምህርት ሚኒስቴር የትራፊክ አደጋን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

ትምህርት ሚኒስቴር የትራፊክ አደጋን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከመንገድ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር  “ከትራፊክ አደጋ የጸዳ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሀገራዊ ህዳሴበሚል ሀገራዊ መሪ ቃል በሀገር ደረጃ የትራፊክ አደጋን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ያካሄደው በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አደራሽ ሚያዝያ 20/2009 ነበር።

 

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚስትር ዴኤታ የሆኑት የተከበሩ / ጥላዬ ጌቴ መድረኩን በእንኳን ዳህና መጣችሁ ንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት የትራፊክ አደጋን ከምንጩ በመቀነስ የህዝባችንን ህይወት፣አካልና ንብረት፤እንዲሁም የሀገሪቱን ሀብት ከጥፋት ለመታደግ መላው ህብረተሰብ በትራፊክ ደህንነት ዙሪያ በባለቤትነት ስሜት እንድንቀሳቀስ ማድረግና ከዚህ አንጻር ዜጎችን በመልካም ሥነ-ምግባር መቅረፅ  በአሁኑ ወቅት እጅግ በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁን ወቅት በትምህርት ዘርፉ ውስጥ በተለያዩ የትምህርት እርከኖች ላይ 30 ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች፣ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ መምህራን፣ከተማሪዎች በስተጀርባ ያሉ በርካታ ወላጆችና መደበኛ ባልሆነ የተቀናጀ የጎልማሶች ትምህርት ላይ እየተሳተፉ ያሉ በርካታ ሠልጣኞች እንዳሉ ጠቅሰው ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በሚገባ በመቀናጀት ከዚህ በፊት ሲሠራ ከነበረው ይበልጥ ሥራውን በማስፋትና በማጠናከር ከተሠራ በሀገር ደረጃ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አስገንዝበዋል።

 

የተከበሩ ሚኒስትር ዴኤታው በማከል የትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ ማህበረሰቡን የእግረኛ መንገድ አጠቃቀም ከትራፊክ አደጋ የጸዳ እንዲሆን ግንዛቤ መፍጠርና እንዲተገብሩት በተለያዩ መንገዶች ድጋፍና ክትትል ከማድረግ ጎን ለጎን በረጅም ጊዜ ሂደት በተሟላ ሥነ-ምግባር የታነጹና ለራሳቸውና ለሌሎች ህይወትና አካል እንዲሁም ንብረት ዋጋ የሚሰጡ በኃላፊነት የሚያሽከረክሩ ዜጎችንም ከማፍራት ረገድ የትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ ሚናና ድርሻ እጅግ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ዘርፋም ይህንን ኃላፊነት በአግባቡ ይወጣ ዘንድ ከዚህ የምክክር መድረክ የሚገኙ ግብዓቶችና ወደፊት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሠራው ሥራ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። ስለሆነም የባለድርሻ አካላት ግብዓት በመስጠትም ሆነ ከዘርፉ ጋር ተቀናጅተው በመሥራት የድርሻቸው እንደሚወጡ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

 

በትራንስፖርት ሚኒስቴር በመንገድ ደህንነት ካውንስል /ቤት የመንገድ ደህንነት ፕሮግራም ክትትል ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ዮናስ በቀለ በምክክር መድረኩ ባቀረቡት ጽሑፍ የመንገድ ደህንነት ቁልፍ ችግሮች የሰዎች የሥነ-ባህሪ ችግሮች፣የመንገድ ዲዛይንና አካባቢ  እና የተሽከርካሪ ቴክኒክ ችግር መሆናቸውን ጠቅሰው እነዚህን  ሦስት ቁልፍ ችግሮችን ከመሠረቱ ለመፍታት የባለድርሻ አካላት ሚና የህብረተሰቡ የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ እንዲዳብርና ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣የትራፊክ ህጎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ድጋፍ ማድረግ፣የመንገድ ዲዛይን ችግሮችን ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ፣የትራፊክ አደጋ ሲደርስ ተጎጂዎች አፋጣኝ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ድጋፍ ማድረግ እና ሥራዎችን ተቀናጅቶ መሥራት እንደሆነ ገልጸዋል። በሀገራችን 90% በላይ የወጪና ገቢ ምርት እንዲሁም 95% በላይ የሰዎች እንቅስቃሴ በመንገድ ትራንስፖርት አማካኝነት የሚከናወን መሆኑንም ጠቁመዋል።

 

በፌዴራል ትራንስፖርት ባለሥልጣን የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ትምህርትና ግንዛቤ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዮሓንስ ለማ በምክክር መድረኩ ባቀረቡት ጽሑፍ በአሁኑ ወቅት በሀገር ደረጃ ያለን የተሸከርካሪ ብዛት 700መቶ አከባቢ መሆኑንና የተሸርካሪና የሰው ጥምርታም 100 ሰው 8 ተሸከርካሪ እንደሆነ ጠቁመው ነገር ግን ይህንን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዝቅተኛ የሆነ የተሸከርካሪ ብዛት ይዘን በሀገራችን እየተከሰተ ያለው የትራፊክ አደጋ ሀገራቷ በትራፊክ አደጋ ክስተት ከዓለም ቀዳሚውን ስፍራ ይዘው ከሚገኙ ሀገራት ተርታ የተሰለፈች መሆኑን አስገንዝበዋል። በአሁኑ ወቅት በዓለም በመንገድ ትራፊክ አደጋ በዓመት 1.24 ሚሊዮን ሰዎች እንደሚሞቱና ይህ አደጋ ሰዎች በስፋት ከሚሞቱባቸው ከአሥሩ ዋና ዋና የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ ምክኒያቶች መካከል 9 ደረጃ ላይ የሚገኝ መሆኑ እና በሚገባ ካልተገተና በዚሁ ከቀጠለ 2030 . ወደ 3 ደረጃ ሊመጣ ይችላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

 

በሀገራችን ባለፉት 5 ዓመታት በደረሰው የትራፊክ አደጋ 16 በላይ ዜጎች ህይወታቸውን እንዳጡና 50 በላይ ደግሞ ለቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደተዳረጉ ጠቅሰው 2008. 4,351 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ፣ 12 በላይ ሰዎች ለቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደተዳረጉ፣ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ንብረት እንደወደመ እና አደጋው አሳሳቢ ደረጃ ላይ ከመሆኑ የተነሳ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሀገራችንንም መልካም ገጽታ በማጉደፍ አለሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ መሆኑን አስገንዝበዋል። አቶ የሓንስ በመካል በሀገራችን እየደረሱ ካሉ የትራፊክ አደጋዎች መካከል 90% የሚሆኑት ምክንያቶቹ ከሥነ-ባህሪ (የአሽከርካሪ፣የተሳፋሪና የእግረኛ ሊሆን ይችላል) ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ጠቅሰው እነዚህን ችግሮች ከመሠረቱ ለመቅረፍ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው በዘላቂነት ከትምህርትና ሥልጠና ዘርፉ ጋር መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

 

በትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ታምራት ፊጤ በምክክር መድረኩ ባቀረቡት ጽሑፍ የትራፊክ ደህንነት ትምህርት ከቅድመ መደበኛ እስከ 5 ክፍል ባሉ በአብዝሃኛው የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርቶች ውስጥ በተለያዩ አግባቦች ተካቶ እየተሰጠ እንደሆነ ጠቀሰው ለማሳያ ያህል ይዘቶቹንም በአጭሩ ለማስቃኘት ሞክረዋል። አቶ ታምራት በማከል ትምህርቱ እየተሰጠ ቢሆንም በሚፈለገው መልኩ የባህሪ ለውጥ ማምጣት እንዳልተቻለ ጠቅሰው ተማሪዎች የባህሪ ለውጥ አምጥተው በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት ከክህሎታቸው ጋር አዋህደው እንዲተገብሩት ለማድረግ የሌሎች ባለድርሻ አካላት ርብርብ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። እስከ አሁን ከነበረው አፈጻጸም፣ከውይይት መድረኩና በቀጣይ ከሚካሄዱ ጥናቶች የሚገኙ ግብዓቶችን በመጠቀም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሥርዓተ ትምህርቱን ለመከለስ ዳይሬክቶሬቱ በዝግጅት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል። መጨረሻም በቀረቡ ሦስቱ ጽሑፎች ላይ ውይይት እንዲካሄድባቸው ለተሳታፊዎች በተሰጠው እድል መሠረት በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ተነስተው በመድረኩ አወያይ በአቶ ያሳቡ ብርቅነህ እና በጽሑፍ አቅራቢዎች ማብራሪያና መልስ ተሰጥቶባቸዋል። 


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡