ዜናዎች ዜናዎች

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ለሚገኙ ሴት እጩ ርዕሳነ መምህራን የሥራ አመራር ሥልጠና እየተሰጠ ነው

ሥልጠናው እየተካሄደ ያለው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ፣ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣በኢ... ትምህርት ሚኒስቴርና አጋር ድርጅቶቹ ትብብር ነው። ሥልጠናው እየተሰጠ ያለበት ቦታ በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ሲሆን ስልጠናውን እየተሰጠ ያለው ከፍተኛ ልምድ ባላቸው በዩኒቨርሲቲው መምህራን ናቸው። ሰልጣኞች በተለያዩ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች ውስጥ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ርዕሰ መምህር ለመሆን ተወዳድረው የተመለመሉ 41 ሴት መምህራን ናቸው። የሥልጠናው የቆይታ ጊዜ ሦስት ወራት ሲሆን መጋቢት 28/2009. በቦታው በተገኘንበት ወቅት ሥልጠናው ከተጀመረ አንድ ወር ከአንድ ሳምንት በላይ እንደሆነ  ለመረዳት ችለናል።

 

በኢ... ትምህርት ሚኒስቴር በመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት የመምህራንና ትምህርት አመራር የሥራ ላይ ሥልጠና ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት / ሊዲያ ሳንቴ ለሥልጠናው ክትትልና ድጋፍ ለመስጠት በክልሉ በተገኙበት ወቅት እንደተናገሩት ይህ ሥልጠና  የትምህርት ዘርፉን የሴት አመራር ፑል ለመፍጠር በሀገር አቀፍ ደረጃ 3060 ሴት መምህራንን በርዕሰነ መምህርነት መልምሎ ወደ ሥልጠና ለማስገባት እቅድ የተያዘ መሆኑን ጠቅሰው፤ በእቅዱ መሠረት በአሁኑ ወቅት 1020 ሴት መምህራንን በርዕሰነ መምህርነት ተመልምለው 12 ዩኒቨርሲዎች ላይ ተመድበው በመሰልጠን ላይ እንዳሉ ገልጸዋል። ይህም በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ እየተሠጠ ያለው ሥልጠና የዚሁ ሥልጠና አካል መሆኑን ጠቅሰው፤ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች የተጣለባቸው ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑን ተገንዝበው  ለሥልጠናው እጅግ በጣም ከፍተኛ ትክረት በመስጠት የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። የዩኒቨርሲቲው አሠልጠኝ መምህራንና አስተባባሪዎችም ሰልጣኞቹ የስልጠና ሰነዶችን አስቀድመው በማንበብ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዲችሉ አስፈላጊውን ሰነዶች ከያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳዮች በፊት አስቀድመው ለሰልጣኞች እንዲሰጡ ከመደረግ ጀምሮ ለየርዕሰ ጉዳዮቹ የተመደቡ ጊዜያት ለአንድ ደቂቃም ቢሆን ሳይሸራፍ ለሥልጠናው በሚውልበት አግባብ ለዚህ ሀገራዊ ተልዕኮ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ሰልጣኞች በተመደቡበት ትምህርት ቤት በሚያከናውኑት የአመራርነት ሥራ ውጤታማ ሆነው ለሌሎችም ሴቶች አርኣያ የመሆን እጅግ ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለባቸው መሆኑን አውቀው በሥልጠነው መጨበጥ የሚገባቸውን እውቀትና ክህሎት ከውዲሁ ጨብጠው  ለውጤታማ ትግበራ ዝግጁ ሆነው መውጣት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

 

በዩኒቨርሲቲው መምህር፣የሥልጠናው አንዱ አሰልጣኝና ረዳት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጠቅል ዓለማው ሥልጠናው ከተጀመራ ከአንድ ወር ጊዜ በላይ መሆኑን ጠቅሰው በአሰልጣኝነታቸውም ሆነ በአስተባባሪነት እስከ አሁን ባገኙት ግብረ-መልስ ሥልጠናው ጥራት ባለው ሁኔታ በትምህርት ሚኒስቴርና በአጋር ድርጅቶቹ ተዘጋጅተው የቀረቡትን ሰነዶች መሠረት በማድረግ በንድፈ ሀሳብና በተግባራዊ ልምምድ እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰው የሚሰጥ ሰልጠኞችም በከፍተኛ ተነሳሽነትና ጉጉት እየሰለጠኑ መሆኑን ገልጸዋል። በሠልጣኞቹ መካከል ለጥቂት ጊዜያትም ቢሆን የሠሩ ጥቂት ሰልጣኞች መኖራቸውን ጠቅሰው በዚህም እርስ በርሳቸው ስለተጨባጭ የሥራ ዓለም ልምድ የሚለዋወጡበት ተጨማሪ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ገልጸዋል። አሠልጣኞችም እሳቸውን ጨምሮ በአንድ ወይም በሌላ መልኩ በተለያዩ የትምህርት እርከንና  ተቋማት አመራርነት ውስጥ ያለፉና ከፍተኛ ልምድ ያለቸው መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ጠቅል በማከል ሥልጠናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት የተቸረው ቢሆንም ለሥልጠናው አስፈላጊ ናቸው በሚል በተለያዩ የበጀት ርዕሶች ከተመደቡ በጀቶች መካከል እስከ አሁን ያልተለቀቁ የበጀት ርዕሶች እንዳሉና ከጊዜ በኋለ እንደመፍትሄ ስለቀቁ ይተካሉ በሚል እሳቤ ከዩኒቨርሲቲው በጀት እየተጠቀሙ መሆኑን ጠቅሰው እንደዚህ አይነቱ ችግሮች በአፋጣኝ መፈታት እንዳለባቸውና በቀጣይ በሚዘጋጁ መሰል ሥልጠናዎች ላይም እንዳይደገሙ ለማስቻል የትምህርት ቢሮውና የትምህርት ሚኒስቴር የተጠናከራ ክትትልና ድጋፍ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

 

የዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አብዱልሙሁስን ሀሰን  ከትምህርት ሚኒስቴር ለሥልጠናው ክትትልና ድጋፍ ለመስጠት በዩኒቨርሲቲው ከተገኙ ባለሙያዎች ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሴት አመራሮችን ተሳትፎና ብቃት ለማሰደግ እንዲቻል ለርዕሰነ መምህራን እየሰጠ ባለው ሥልጠና ላይ ዩኒቨርሲቲያቸውም የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የተሰጠውን ተልዕኮ በአግባቡ ለማሳከት የሥልጠናው አስተባባሪ ቦርድ አባል በመሆን ለሥልጠናው የቅርብ ክትትል በማድረግ እየሠሩ መሆኑንና በቀጣይም ለሥልጠናው የሚያደርጉትን ክትትልና ድጋፍ የበለጠ አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት አረጋግጠዋል።

 

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ታዬ  ከትምህርት ሚኒስቴር ለሥልጠናው ክትትልና ድጋፍ ለመስጠት በክልሉ ከተገኙ ባለሙያዎች ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅትሴት ዕጩ ርዕሰነ መምህራኖቹ ሥልጠናውን እንዳጠናቀቁ ወዲያውኑ መድቦ ለማሠራት የክልሉ ዝግጁነት በምን ደረጃ ይገለጻል?” በሚል ከባለሙያዎቹ ለተነሳላቸው ጥያቄ መልስ ስሰጡ ሥልጠናውን እየተከታተሉ ካሉ 41 ሴት ዕጩ ርዕሰነ መምህራን መካከል 35 ቀደም ብለው ምድባቸውን አውቀው ወደ ሥልጠና የገቡ መሆናቸውን ጠቅሰው ቀሪዎቹም (ስድስቶቹ) ሴቶች ሥልጠናውን እንዳጠናቀቁ ወዲያውኑ እንዲመደቡ ለማድረግ ከወዲሁ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

 

በኢ... ትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት አመራር  ዳይሬክቶሬት አማካሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን አበራ ለሥልጠናው ክትትልና ድጋፍ ለመሥጠት በዩኒቨርሲቲው ተገኝተው ሰልጣኞችን ባነጋገሩበት ወቅት የሥልጠናው ሞጁሎች ሰባት መሆናቸውንና በሦስት ዋና ዋና መርሃ-ግብሮች (በፖሊሲ፣በአመራርነትና በዘርፈ ብዙ ጉዳዮች) ላይ  ትኩረት አድረገው በከፍተኛ ጥንቃቄ የተዘጋጁና ጥራት ያላቸው መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በዝግጅታቸውም ላይ  የኮሌጆች፣የዩኒቨርሲቲዎች፣የትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎችና አማካሪዎች የተሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል። ከሥልጠናው ርዕሰ ጉዳች መካከል ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን፣ የት/ቤት አመራርን፣መሪነትን፣ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በተለይ ኮምፒውተርን፣ የት/ቤት ፋይናንሲንግን፣ የወላጅና ህብረተሰብ ተሳትፎን ለአብነት ገልጸዋል። በሰነዶቹ ጥራት ልክ  አሠልጣኞች በሚገባ እንዲያሰለጥኑ እና ሰልጣኞችም የነቃ ተሳትፎ በማድረግ በሥልጠናው መጨበጥ ያለባቸውን እውቀትና ክህሎት ጨብጠው በተመደቡበት ትምህርት ቤት ላይ በሚገባ ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል። አቶ ሰለሞን በማከል ይህ በዚህ ዓመት በዚህ አግባብ የተጀመረው የሥልጠና መርሃ ግብር በእቅዱ መሠረት ከተፈጸመ እስከ አምስተኛው የትምህርትና ሥልጠና ልማት ፕሮግራም መጀመሪያ ድረስ 8% የነበረውን የትምህርት ቤቶች የሴት አመራር ሚናንም ሆነ መጠንን በአምስተኛው የትምህርትና ሥልጠና ልማት ፕሮግራም ማጠናቀቂያ ማለትም 2012 . መጨረሻ 20% በማድረስ ከዚህ አንጻር ለተያዘው ግብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን ገልጸዋል።

 

በወቅቱ በዩኒቨርሲቲው ተገኝተን ከናጋገርናቸው ሠልጣኞች መካከል መምህርት ታየች በላይነህ ወደ ሥልጠናው የመጣችው ከማንዱራ ወረዳ ፎቶ መንጃሬ ትምህርት ቤት ሲትሆን ለርዕሰ መምህርነት ተወዳድረ ሲታሸነፍ የጠበቀችሁ ምንም እንኳ ከዚህ በፊት የእንግልዝኛ ቋንቋ መምህርት ሆነ ከማስተማር ውጪ በርዕሰ መምህርነት ምንም አይነት ልምድ ባይኖራትም እንደተለመደው በቀጥታ ወደ ተመደችበት ትምህርት ቤት ሄዳ በርዕሰ መምህርነት ማገልገልን ነበር።ነገር ግን  በቀጥታ በርዕሰ መምህርነት ሥራ ላይ ከመሠማራቷ በፊት ይህን ሥልጠና በማግኘቷ በጣም ደስተኛ እንደሆነች ጠቅሳ እሰከ ተገናኘንባት ወቅት በነበራት የሥልጠና ላይ ቆይተዋ ሥልጠናው ከልምዷ ለመማር የሚትፈጀውን ጊዜና ከስህተት የመማር አጋጣሚን ከመቀነሱም በላይ በበቂ እውቀትና ክህሎት ላይ ተመስርታ በሙሉ የራስ መተማመን ትምህርት ቤቱን በተሻለ ደረጃ እንድትመራ የሚያስችላት አቅም እየፈጠረላት እንደሆነ ገልጻለች።

መምህርት ጸሐይ ወርቄ የመጣችው ከፓዊ ወረዳ ቀጠና 2 መንደር 130 ትምህርት ቤት ሲትሆን የእንግልዝኛ ቋንቋ መምህርት ነበረች። ለርዕሰ መምህርትነት ተወዳድራ ቦታውን አግኝታ የተመደበችው ህዳር/2009. ቢሆንም ልምድ ያልነበራትና መሰል ሥልጠና ባለመውሰዷ የተነሳ ሙሉ በሙሉ ወደ ርዕሰ መምህርትነት ሥራው ገብታ ከመሥራት ይልቅ ልምድ እስክ አገኝ በሚል ምክንያት ቀደም ብሎ ጊዜያዊ ተወካይ ሆኖ ሲሠራ በነበረው ተወካይ ላይ ጥገኘ ሆነ እየመራች ባለችበት ሁኔታ ለይ ሆነ ወደ ሥልጠናው እንደመጣች ገልጻለች። ከአንድ ሰው ሲታገኝ የነበረው ልምድ ከአንድ ሰው መሆኑ ብቻ በራሱ ጉድለት ከመሆኑ በተጨማሪ እሱም በሳይንሳዊ ዕውቀትና ክህሎት ላይ ተመሠርቶ ሳይሆን በልምድ ላይ የተመሠረተ አመራር ስለሆነ በእንደዚህ አይነቱ የልምድ አወሳሰድ ሂደት ደግሞ የሱን ጠንካራ ጎን ብቻ ለቅማ በመውሰድ ፋንታ ደካማ ጎኑንም ጭምር ወስዳ እንዳታስቀጥል ዋስትና የሚሰጥ አንዳልነበረ አብራርታለች። በመሆኑም መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ ሴቶች በስፋት ወደ ርዕሰ መምህርነት እንዲመጡ ለወሰደው እርምጃም ሆነ በአመራራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ እየሰጠ ላለው የአመራርነት ሥልጠና ከፍተኛ አድናቆት ያላት መሆኑን ገልጻ ከዚህ በፊት በነበረው አመላመልና ምደባ ውድድር ቢኖርም አብዝሃኛውን ጊዜ ከፍተኛ ነጥብ አግኝተው ርዕሰ መምህር የሚሆኑት በሆነ አጋጣሚ የዲፓርት ኃላፊና ዩኒት ሊደር ሆነው የሠሩ መምህራን ሲሆኑ ወደ አመራርነት ስመጡም አንደዚህ አይነት የአመራርነት ሥልጠናዎች እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚሰጡበት አግባብ እንዳልነበረ ገልጻለች። ነገር ግን በአሁኑ የምልመላ ሂደት ሴቶች እርስ በራሳቸው ብቻ ተወዳድረው ለርዕሰ መምህርነት ቦታ እንዲበቁ ከመደረጉም በላይ ክፍተታቸውን በመሙላት ውጤታማ በሆነ መልኩ ከተመደቡበት ተቋምም በላይ የሆኑ ተቋማትን ጭምር መምራት በሚያስችላቸው ሁኔታ መሰል ገንቢ የሆነ ሥልጠና እንዲያገኙ መደረጉ ቀጣይነት ሊኖረው የሚገባ ትክክለኛ ታሪካዊ ውሳኔና ድርጊት መሆኑን ገልጻለች።

 

መምህርት ላይላ አልሀሰን ወደ ሥልጠናው የመጣችው ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከቤኒሻንጉል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን ርዕሰ መምህርትነት ተወዳድራና ተመልምላ ወደ ሥልጠናው እስከ ገባችበት ጌዜ ድረስ የሲቪክስ መምህርት ሆነ ሲታገለግል ነበር። እየተሰጣቸው ያለው ሥልጠና ወደ ፊት ተመደበውበት ከሚሠሩበት የርዕሰ መምህርትነት ሥራ ጋር ተያያዥነት ያለው ከመሆኑም በላይ የሥልጠናው ሂደት በንድፈ ሀሳብና በተግበራዊ ልምምድ ላይ የተመሠረተ መሆኑ ከሥልጠናው መጨበጥ የሚገባትን እውቀትና ክህሎት ለመጨበጥ እንዳስቻላት ጠቅሳ ከሥልጠናው በተጨማሪም ከዚህ በፊት ርዕሰ መምህራን ሆነው የሠሩ ጥቂት ሴት መምህራን በመካከላቸው እንደሚገኙና ከነሱም ልምድ እየወሰዱ መሆኑን ገልጻለች።No comments yet. Be the first.
ዜናዎች

የ2009 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ (የ10ኛ ክፍል) ብሔራዊ ፈተና ከግንቦት 23- 25 እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና (የ12ኛ ክፍል) ከግንቦት 28 እስከ ሰኔ 1 2009 ዓ.ም. ይሰጣሉ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2009 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ (የ10ኛ ክፍል) ብሔራዊ ፈተና ከግንቦት 23- 25 እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተናዎች (የ12ኛ ክፍል) ከግንቦት 28 እስከ ሰኔ 1 2009 ዓ.ም. እንደሚሰጡ ገለጸ፡፡ የፈተናው አጠቃላይ ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን በሀገሪቱ ለሚገኙ ተፈታኞች 3,467 የፈተና ጣቢያዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ በዚህ ዓመትም ከ1.2 ሚሊየን በላይ የ10ኛ ክፍል እንዲሁም ከ288ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በተፈጥሮ ሳይንስና ምህድስና ትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎችን ሸለመ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሥርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሥርዓተ ጾታና ባለ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በተፈጥሮ ሳይንስና ምህድስና ትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከአንደኛ እስከ አምስተኛ አመት ያሉ ሴት ተማሪዎች፣ ድጋፍ ላደረጉላቸው መምህራንን እና አመራሮች የማበረታቻ ሽልማት ሰጠ፡፡ በዩኒቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አደራሽ ...

በሙያ ፍቃድ የምዘና ውጤት ትንተናና በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች እውቅና አሰጣጥ ስታንዳርዶች ዙሪያ ምክክር መድረክ ተካሄደ

ሀገራችን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥና እድሳት ስርዓት በመዘርጋት የመምራን፣ የርዕሰ መምህራንና የሱፐርቫይሮች ሙያዊ ብቃት ምዘና ሂደትን በወጥነት ለመተግበርና በሙያ ፍቃድ አሰጣጥ የአደረጃጀቶችን ሚናና የፈጻሚ ባለድርሻ አካለላትን ተግባርና ኃላፊነት ለይቶ ለማሳወቅና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚየስችል የአሰራር ስርዓት ዘርግታ እየሰራች ትገኛለች፡፡ በሙያ ፍቃድ አሰጣጥ ስርዓት ውስጥ ሶስት የሙያ ፍቃድ አይነቶች አሉ፡፡ እነዚህም፦ አንደኛው የመጀመሪያ ሙያ ፍቃድ ለጀማሪ መምህራንና በትምህርት ተቋማት አመራርነት ሰልጥነው ወደሙያው ለሚገቡ እንዲሁም ለደረጃው የብቃት መመዘኛ ላሟሉ የሚሰጥ ፣ ሁለተኛው ሙሉ የሙያ ፍቃድ፥ ለአምስት አመት የሚያገለግል ሆኖ የመጀመሪያ ሙያ ፍቃድ በማግኘት ሲሠሩ ቆይተው ላጠናቀቁ የሚሰጥ ሲሆን የሦሥተኛው ደግሞ ቋሚ የሙያ ፍቃድ ነው፡፡ ይህ ፍቃድ ሙሉ የሙያ ፍቃድ ከያዙ በኋላ ለደረጃው የሚመጥን አገልግሎት አጠናቀው የሙያ ፍቃድ ብቃት መመዘኛ ላሟሉ መምህራን፣ ለርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የሚሰጥና በየአምስት አመት የሚታደስ ቋሚ የሙያ ፍቃድ ነው፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የትራፊክ አደጋን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከመንገድ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “ከትራፊክ አደጋ የጸዳ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሀገራዊ ህዳሴ“ በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል በሀገር ደረጃ የትራፊክ አደጋን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ያካሄደው በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አደራሽ ሚያዝያ 20/2009 ዓ∙ም ነበር። የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚስትር ዴኤታ የሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ መድረኩን በእንኳን ዳህና መጣችሁ ንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት የትራፊክ አደጋን ከምንጩ በመቀነስ የህዝባችንን ህይወት፣አካልና ንብረት፤እንዲሁም የሀገሪቱን ሀብት ከጥፋት ለመታደግ መላው ህብረተሰብ በትራፊክ ደህንነት ዙሪያ በባለቤትነት ስሜት እንድንቀሳቀስ ማድረግና ከዚህ አንጻር ዜጎችን በመልካም ሥነ-ምግባር መቅረፅ በአሁኑ ወቅት እጅግ በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁን ወቅት በትምህርት ዘርፉ ውስጥ በተለያዩ የትምህርት እርከኖች ላይ 30 ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች፣ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ መምህራን፣ከተማሪዎች በስተጀርባ ያሉ በርካታ ወላጆችና መደበኛ ባልሆነ የተቀናጀ የጎልማሶች ትምህርት ላይ እየተሳተፉ ያሉ በርካታ ሠልጣኞች እንዳሉ ጠቅሰው ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በሚገባ በመቀናጀት ከዚህ በፊት ሲሠራ ከነበረው ይበልጥ ሥራውን በማስፋትና በማጠናከር ከተሠራ በሀገር ደረጃ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አስገንዝበዋል።

የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት የትምህርት አቀራረብ ሥነ-ዘዴ እንደ አንድ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ማስፋፊያ አመራጭ ተወስዶ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንድተገበር የምመክር አውደ ጥናት ተካሄደ

የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ከ2007 ዓ.ም ክረምት ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተተገበረ ያለውን የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት የቅድመ መደበኛ ትምህርት አቀራረብ ውጤታማነትን ለማስተዋወቅና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማስፋት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጪ ከሁሉም ክልሎች፤ ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር፣ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ እና ከህጻናት አድን ድርጅት እንዲሁም ከትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና የትምህርት ባለሙያዎች የተሳተፉበት አውደ ጥናት ሚያዚያ 2 እና 3/2009 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አደራሽ ተካሄደ። ይህ ፕሮግራም ከአራቱ የቅድመ መደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ሥነ-ዘዴ መካከል አንዱ ሲሆን በሦስቱም (መዋዕለ ህጻናት፤ ኦ ክፍልና ህጻን ለህጻን) የቅድመ መደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ተጠቅመው ለመደበኛ ትምህርት ቅድመ ዝግጅት ያላደረጉትን እድሜያቸው ስድስት ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ህጻናትን በስምንት ሳምንታት ውስጥ ለመደበኛ ትምህርት ዝግጁ ማድረግ ያሚያስችል ፕሮግራም ነው።

Communication Address:

Tel: +251-11-156-14-94

Fax: