በቤኒሻንጉል ጉምዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለሚገኙ የ”ኦ” ክፍል መምህራንና አመቻቾች በማስተማር ሥነ-ዘዴ ላይ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለሚገኙ የ”ኦ” ክፍል መምህራንና አመቻቾች በማስተማር ሥነ-ዘዴ ላይ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል

የሥራ ላይ ሥልጠናው እየተካሄደ ያለው በቤኒሻንጉል ጉምዝ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ፣ በኢ... ትምህርት ሚኒስቴርና አጋር ድርጅቶች ትብብር ነው፣እየተካሄደ ያለው በክልሉ የሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ውስጥ ሲሆን ቆይታው የአንድ ወር ያክል ከመጋቢት 25/2009 . እስከ ሚያዝያ 24/2009. ድረስ የሚቆይ ነው። ሥልጠናውን እየሰጡ ያሉት ቀደም ሲል በትምህርት ሚኒስቴር፣በዩኒሴፍና በዓለም ባንክ ትብብር በአዳማ ከተማ ላይ 10 ቀናት የአሰልጣኞች ሥልጠና የወሰዱ አግባብነት ያላቸው 44 የክልሉ የትምህርት ዘርፍ ባለሙያዎች ናቸው። በሥልጠናው ላያ እየተሳተፉ ያሉት መምህራን በተለያዩ የክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች ውስጥ ከሚገኙ ክፍል ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 499 (170 ወንዶችና 329 ሴቶች) ክፍል መምህራንና አመቻቾች ናቸው። ሥልጠናው በክልል ደረጃም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ስሰጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን እየተካሄደ ያለውየቅድመ መደበኛ ትምህርት ለመደበኛ ትምህርት ውጤታማነት መሠረት ነውበሚል መሪ ቃል ነው።

 

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ታዬ በክልሉ የሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ተገኝተው ሥልጠናውን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት  ከዚህ በፊት ክልሉ ለቅድመ መደበኛ ትምህርት የሚገባውን ትኩረት ሰጥቶ በሁሉም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተደራሽ ባለማድረጉ በርካታ ህጻናት በሚገባቸው መልኩ የትምህርት ቤት አከባቢን ሳይተዋወቁና መደበኛ ትምህርት ለመማር የሚያስችል መሠረት ሳይጣልባቸው በቀጥታ መደበኛ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ሲደረግ እንደነበረ ገልጸዋል።ይህም በመሆኑ በመደበኛ ትምህርት ቤቶች በርካታ ተማሪዎች ለመጠነ ማቋረጥናከትምህርት ገበታ ላይ ለመቅረት የተዳረጉ መሆኑን ጠቅሰው ከዚሁ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች የማንበብ፣የመጻፍና የማስላት ክህሎታቸውም ሲፈተሽ ከሚጠበቀው በታች መሆኑን ገልጸዋል። እነዚህንና መሰል ችግሮችን ለመፍታትክፍልን ማስፋፋትና ክፍል መምህራንን አቅም መገንባት ወሳኝ ሥራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ሰልጣኞቹም መንግሥት ለፕሮግራሙ የሰጠውን ልዩ ትኩረት ከግምት በማስገባት የሥልጠናው ዓለማ ከግብ እንዲደርስ በንቃት ተሳትፈው በዚህ አንድ ወር ቆይታቸው ማግኘት የሚገባቸውን ዕውቀትና ክህሎት መጨበጥ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። አቶ ሀብታሙ በማከል ክልሉ የሥልጠናውን የመጀመሪያ ዕድል እንዲያገኝም ሆነ በአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም በኩል ለሥልጠናው አስፈላጊው በጀት እንዲመደብ በማድረግ ለተደረገው ድጋፍ ትምህርት ሚኒስቴርና አጋር ድርጅቶችን አመስግነው፤የክልሉ መንግሥትም ሥልጠናውንም ሆነ ቀጣይ ትግበራውን በጥብቅ ዲሲፒሊን የሚከታተለው መሆኑን ገልጸዋል።

በኢ... ትምህርት ሚኒስቴር በመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት የመምህራንና ትምህርት አመራር የሥራ ላይ ሥልጠና ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት / ሊዲያ ሳንቴ ለሥልጠናው ክትትልና ድጋፍ ለመስጠት በክልሉ በተገኙበት ወቅት ለሰልጣኞች እንደተናገሩት ክልሉ የሥልጠናውን የመጀመሪያ ዕድል በማግኘት በሀገር ደረጃ የመጀመሪያ ክልል እንደመሆኑ መጠን ሠልጣኞች በሚገባ ሰልጥነውና ተግብረው ውጤታማ ሆነው እንደ ሀገር የፕሮግራሙ ቀጣይነት እንዲረጋገጥ ማድረግ የሚገባቸው ከመሆኑም ባሻገር ወደ ተቀሩትም የሀገራችን ክልሎች ማስፋፋት የሚያስችል ተሞክሮ የሚወሰድበት ስለሆነ ሥልጠናውን በጥብቅ ዲሲፕሊን ወስደው ትምህርት ቤት ማውረድ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። ሥልጠናው እስከሚጠናቀቅም ሆነ በትግበራው ወቅት ትምህርት ሚኒስቴር ከክልል ትምህርት ቢሮው ጎን በመሆን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ  አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ እንደሚከታተል ገልጸዋል።

 

በኢ... ትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና ትምህርት አመራር  ልማት ዳይሬክቶሬት አማካሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን አበራ ለሥልጠናው ክትትልና ድጋፍ ለመሥጠት በክልሉ ተገኝተው ሰልጣኞችን ባነጋገሩበት ወቅት የቅድመ መደበኛ ትምህርት ህጻናት በአካል፣በአእምሮና በሥነ-ልቦና በፍጥነት የሚያድጉበትና የመማር ፍጥነታቸውም እጅግ በጣም ከፍተኛ በሆነበትና ለቀጣይ መደበኛ ትምህርታቸውም ሆነ ህይወታቸው መሠረት የሚጥሉበት የእድሜ ደረጃ ላይ የሚሰጥ ትምህርት መሆኑን ገልጸዋል። ስለሆነም ትምህርቱ የህጻናት ለወደ ፊት ሀለንተናዊ ዕድገት መሠረት የሚጣልበት እንደመሆኑ መጠን ትዕግስትና ብልሃት በተሞላበት አኳኃን ከመደበኛው ትምህርት በተለየ አቀራረብ ለህጸናት በሚመቻቸው ለምሳሌ በጨዋታ፣በመዝሙር፣በተረት፣በአካል እንቅስቃሴና በመሳሰሉት መልክ የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰው ሰልጣኞች የተጣለባቸው ኃላፊነት ወሳኝ መሆኑን አውቀው በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚያገኙትን ሥልጠና ሳያንጠባጥቡ ወደ ትምህርት ቤታቸው ወስደው በህጻናት ላይ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል። በመጨረሻም በቀጣይ ሥልጠናውን በተመሳሳይ መልኩ ወደ ሌሎች ክልሎች ለማስፋፋት እቅድ የተያዘ መሆኑን ጠቁመዋል።


ዜናዎች

የቀጣይ 5 ዓመት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ይፋ ሆነ

የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር "የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ መርሃ-ግብር ለፍትሃዊነት " በሚል መሪ ቃል ለቀጣዩ 5 ዓመታት የሚተገበር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በተገኙበት ይፋ ሆኗል።

አካል ጉዳተኞች እንደየችሎታቸውና እንደየፍላጎታቸው መማር እንደሚገባችዉ ተገለጸ፤

በትምህርት ሚኒስቴር የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ከሰኔ 04 - 11/2010 ዓ.ም በአካል ጉዳተኞች ትምህርት ስታንዳርድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት አካሄደ፡፡ በውይይቱም ከተለያዩ ክልሎች ለተውጣጡ የአካቶ ትምህርትና የስርዓተ ትምህርት ባለሙያዎች፤ከትምህርት ሚኒስቴር ልዩ ልዩ ክፍሎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ መሀመድ አህመዲን የፈተናውን መጠናቀቅ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት በፈተናው ሂደት ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የተማሪ ወላጅ፣ የሚዲያ አካላትና የፀጥታ ኃይል እንዲሁም መላው ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማበርከታቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ሚኒስትሩ ገለፃ በአንዳንድ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተንቀሳቃሽ ስልክ ይዘው ክፍል መግባትና ለሌላ ተማሪ ለመፈተን የመሞከር አዝማሚያዎች ቢከሰቱም በየደረጃው በተሰማሩ የፈተናው ግብረ ኃይል አማካይነት ችግሮቹ እልባት ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም ተጠናቀቀ

የ2010ዓ.ም የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሠላም መጠናቀቁን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ዘርሁን ዱሬሳ ገለጹ፡፡ 1.2 ሚሊዮን የሚሆኑ ተማሪዎች የተፈተኑት እና ከ70ሺህ በላይ የሚሆኑ ፈታኞችና ተቆጣጣሪዎች የተሳተፉበት ፈተና፣ በአንዳንድ ፈተና ጣቢያዎች ላይ ሞባይል ይዘው ክፍል መግባት፣ ለመኮረጅ መሞከር፣ ለሌላ ተማሪ ለመፈተን መሞከር ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ጉዳዩ ቀላልና በፈተና ደንብ የሚታይ ይሆናል፣ በአጠቃላይ ግን ፈተናው በታቀደለት ጊዜ በሠላም ተጠናቋል ብለዋል ዶ/ር ዘርሁን፡፡

በአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ስልጠና ተሠጠ፤

በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር የጋራ ትብብር በተባበሩት መንግስታት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ስምምነት አተገባበር ዙሪያ ከፌደራል ተቋማት ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት የተዘጋጀ ስልጠና ከግንቦት 23-ግንቦት 27/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ነው ፡፡