የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ፕሮግራም ትግበራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ

የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ፕሮግራም ትግበራ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ

ይህ የተገለጸው የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ ለህፃን  ዕድገት አጋር ድርጅት (The Partnership for Child Development, PCD) ጋር በመተባባር ባዘጋጀው መድረክ ነው፡፡

 

ሚኒስቴር /ቤቱ ፕሮግራሙን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ  መጋቢት 04/07/2009 .ጤናማ መሆን ለመማር ለመማር ጤናማ መሆን የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ማሳደግበሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የአንድ ቀን ምክክር አውደ ጥናት አካሂዷል፡፡

 

ፕሮግራሙ በመጀመሪያ ደረጃ የሚማሩ ህፃናት በምግብ እጥረትና በተለያዩ በሽታዎች ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩና እንዳያቋሪጡ  ብሎም ትምህርታቸውንም በትኩረት እንዲከታተኩ የጎላ ሚና አለው፡፡

 

በየሚኒስቴር /ቤቱ  የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ያሳቡ ብርቅነህ የአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታን በመወከል የመድረኩ መክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደተናገሩት ተማሪዎች በአካላልና በአዕምሮ ዕድገት የተሸለ ሆኖ እንዲወጡ  የትምህርት ቤት ጤናና ስነ ምግብ ፕሮግራም ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

በመረጃ የተደገፈ የትምርት ቤት ጤናና ምግብ ድጋፍ ማጠናከር፥   በመላው ሀገሪቱ የትምህርት ዘርፍ ልማት እቅዶችና ፖሊሲ  ለማሳካት የተረጋጋ፣ ወጪ ቆጣቢ እንዲሁም  ለረጅም ጊዜ የሚያገለግል  መርሃ ግብር መቅረፅ ነው ብለዋል አቶ ያሳቡ፡፡

 

እንደ ዳይሬክተሩ ንግግር  የተማሪዎች ትምህርት ውጤትና የመማር ፍላጎት ይበልጥ ለማሳደግ  ሚኒስቴር /ቤቱ ከፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከግብርናና የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር እንዲሁም ከውኃና ኤልክትሪክ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተማሪዎች የመማር ሂደት የሚያሳኩ ጤናና  የምግብ ድጋፍ ለማድረግ በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ጨምሮ ጠቁመዋል፡፡  

 

በሚስቴር /በቱ የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት አከለ የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ፕሮግራም በተመለከተ የባንኮክ ተሞክሮ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት የተቀናጀ የትምህርት ቤት ጤናና የምግብ ፕሮግራም የተማሪዎችን የትምህርት ውጤት ከመደገፍ በተጨማሪ  ትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ጋር የተያያዘ የትምህርት ማህበረሰብ ግንዛቤ ማደግ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

 

በቀጣይነትም ለፕሮግራሙ ተግባራዊነት የቅንጅት ስራዎች በተለይም ሚነስቴር /ቤቱና የፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በየደረጃው ያሉ የመንግስት መዋቅሮች እንዲሁም ከልማት አጋ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በመድረኩ የተነሱ ክፍተቶች ለመሙላት ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

 

የዓለም አቀፍ ለህፃን  ዕድገት አጋር ድርጅት ፕሮግራም (PCD) ስራ አስካጅ ወሮ ለውራ አፕለባይ በአግባቡ የተቀረፀ የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ፕሮግራም ወጪ ቆጣቢና ውጤታማ መሆኑን በመናገር የሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ የተማሪዎች ውጤትን ከማሻሻል ባሻገር የግብርና ምርት ገበያ ለማሳደግ እንደሚረዳም ገልጸዋል፡፡

 

የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ፕሮግራም አተገባበሩ ላይ ያጋጠሙ መልካም ግኝቶች ችግሮችና የትኩረት አቅጣጫዎች የሚያሳዩ  ጥናቶች እንዲሁም የውጭ ሀገር ተሞክሮዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

 

በመድረኩ ከሚኒስቴር /በቱ፣ ከፌዴራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ከክልል ትምህርት ቢሮ  እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች የተውጣጡ ኃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና የትምህርት ቤት ጤናና ምግብ ፕሮግራም ተጠሪዎች ተሳትፈዋል፡፡


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡