የታዳጊ ክልሎች የሴቶች ትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት የንቅናቄና የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሄደ

የታዳጊ ክልሎች የሴቶች ትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት የንቅናቄና የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሄደ

ሀገር አቀፍ የታዳጊ ክልሎች የሴቶች ትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት የንቅናቄና የምክክር መድረክ ከየካቲት 26-30/2009 . በአዳማ ከተማ የተካሄደው በትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓታ ፆታ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ነበር።

 

በትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓታ ፆታ ዳይሬክቶሬት / ኤልሳቤጥ ገሠሳ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው  መንግሥት ዘላቂና ፍትሃዊ ልማትን የሚገድብ የሰርዓተ ፆታ እኩልነት መፋለስን ለመቅረፍ የህግ፣የፖሊሲና የስትራቴጂ ማዕቀፎችን በመዘርጋት እነዚህኑ መሠረት ያደረጉ የረጅም፣የመካከለኛና የአጭር ጊዜ እቅድ  አዘጋጅቶ በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው  ከነዚህም ማዕቀፎች መካከል ለአብነት ያህል የሚከተሉትን ጠቅሰዋል። ከህግ ማዕቀፎች አንጻር፦ የኢ... ህገ-መንግሥት አንቀጽ 35፣የአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996፣የፌዴራል መንግሥት  አስፈጻሚ አካላት ሥስልጣንና ኃላፊነት ለመወሰን የወጣ አዋጅ ቁጥር 691/2003፣የገጠር መሬት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 455/1996  እና የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ አዋጅ ቁጥር 515/1997 መሆናቸውን፤ከፖሊሲ ማዕቀፎች አንጻር፦ ብሔራዊ የሴቶች ጉዳይ ፖሊሲ፣የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ፣የባህል ፖሊሲ፣ የተፈጥሮ ሀብትና አከባቢ ጥበቃ ፖሊሲ፣የማህበራዊ ድህነትና ልማት ፖሊሲ፣ግብርና መር ኢኮኖሚክ ፖሊሲ፣የጤና ፖሊሲ እና ሌሎችም መሆናቸውን፤ ከስትራቴጂዎችና  እቅዶች አንጻር፦የኢትዮጵያ ሴቶች የልማትና የለውጥ ፓኬጅ እና በአንደኛውና በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ ከተያዙት  ከሰባቱ  መሠረታዊ አቅጣጫዎች መካከል የሥርዓተ ፆታ እኩልነትና የሴቶችን ሁለንተናዊ ብቃት ማሳደግ እንደ አንድ አቅጣጫ ተወስዶ እየተተገበረ እንደሆነ ገልጸዋል። / ኤልሳቤጥ በማከል  ከላይ የተጠቀሱትን ማዕቀፎች መሠረት በማድረግ በትምህርትና ሥልጠና ሴክተሩ በየደረጃው የሴቶች ትምህርት ተሳትፎ፣ውጤታማነትና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በተሰጠው ልዩ ትኩረትና እንቅስቃሴ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።

 

በኢ... ትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ እስክንድር ላቀው መድረኩን ከመምራት በተጨማሪ የትምህርት ሚኒስቴር አመታዊ ስታትክስንና የማዕከላዊ ስታትክስ ኤጀንሲን ዳታን ማዕከል ያደረገ ከእቅድ ጋር በንጽጽርና በተለያዩ መለኪያዎች የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ 2008 በጀት አመት የሴቶች ትምህርትና ሥልጠና ተሳትፎና ውጤታማነት ሪፖርትን አቅርበዋል። አቶ እስክንድር ሪፖርቱን በአቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት የሴት ተማሪዎች ተሳትፎና ውጤታማነት በጥቅሉ  ሲታይ ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል ያሳየ መሆኑን ጠቅሰው  ይሁንጂ ከቅድመ-መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ወደ ላይ በሄድን ቁጥር አፈጻጸሙ እየወረደ ከመሄዱም በላይ በተለይ ከነባር ብሔረሰቦች ሴቶች ተሳትፎና ውጤታማነት አንጻር እየተመዘገበ ያለው ውጤት ከሚጠበቀው አንጻር ሲታይ ዝቅተኛ ስለሆነ ለሥራው የሚመጥን አደረጃጀት በመዘርጋት፣በቂና ብቃት ያለው የሰው ኃይል በመመደብ ጉዳዩ ከሚመለካታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በሚገባ ተቀራርቦና ተቀናጅቶ መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

 

በመድረኩ የአራቱም ታዳጊ ክልሎች 2009 በጀት አመት 6 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርበው  ከተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየት ተነስተው ምላሽና ማብራሪያ ተሰቶባቸው የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶባቸዋል። በሪፖርቶቹ ከተዳሰሱት እና በጥያቄም ሆነ በአስተያየት መልክ ተነስተው ማብራሪያ ከተሰጣቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል ለአብነት ያክል የሚከተሉትን መጥቀስ የሚቻል ሲሆን እነሱም፦ ሴቶች በየትምህርት እርከን በሁሉም የአመራር ደረጀ ተመድበው እንዲሠሩ የማብቃት፣የማበረታታትና የመደገፍ ሥራ መሠራት እንዳለበት፤ሴቶች በሁሉም የትምህርት መስኮችና የልማት አውዶች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ከመሠረታቸው ጀምሮ ሊሠራ እንደሚገባ፤ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት አፈጻጸም በአራቱም ታዳጊ ክልሎች የሚጠበቀውን ያህል ባይሆንም በተለይ በጋምቤላ ብሔራዊ ክልል እጅግ በጣም ዝቅተኛ ሰለሆነ ይህን ውጤት በአፋጣኝ በመለወጥ የጎልማሶችን ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ፤ከጥቂት ጊዜ በኃላ በተጠናከረ መልኩ ሴቶችን ወደ አመራር ለማምጣት የሚያስችል የሴት አመራሮች ፑል ለመፍጠር ከየክልሉ የአመራርነት ተስጦ ያላቸውን ሴት መምህራን በመመልመል ለአመራርነት ሥልጠና ወደ ተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች አስገብቶ የማሰልጠን ሥራ የተጀመረ መሆኑ፤ የሥርዓተ ፆታ መዋቅር ሥራውን መሸከም በሚችልና ወጥነት ባለው መልኩ ትኩረት ተሰጥቶት መደራጀት እንደሚገባው፣ሥራው በበቂ በጀትና የሰው ኃይል መደገፍ እንደሚገባው፣የነባር ብሔረሰቦች የትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት ላይ ትኩረት በመስጠት መሥራት እንደሚገባ፣ከሚመለከታቸው የመንግሥትና የህዝብ ክንፍ እንዲሁም ከአጋር ድርጅቶች ጋር በሚገባ ተቀናጅቶ ከማቀድ ጀምሮ አስከ አፈጻጸም ግምገማ በትብብር ስለመሥራት፣የሴቶች ተሳትፎን፣ውጤታማነትንና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላት ቁርጠኝነት ወሳኝ ስለመሆኑ እና ሌሎችም ጉዳዮች ተነስተዋል።


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡