የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ

የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አከበሩ

የትምህርት ሚኒስቴር ሠራተኞች ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንንየሴቶች የቁጠባ ባህል ማደግ ለህዳሴያችን መሠረት ነው!!” በሚል መሪ ቃል በዓለምና በሀገር ደረጃ ከሚከበርበት ዕለት ቀደም ብለው የካቲት 24/20089 . በአዲስ አበባ ከተማ በብሔራዊ ትያትር አደራሽ አክብረዋል።

 

በትምህርት ሚኒስቴር የሥርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር / ኤልሳቤጥ ገሠሠ በዓሉን አስመልክተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የሚከተሉትን መልዕክቶች አስተላልፈዋል። የሴቶች ቀን አከባበር ታሪካዊ አመጣጥን አስመልክቶ / ኤልሳቤጥ በሰሜን አሜሪካ በኒውዮርክ ከተማ .. 1908 . የፋብሪካ ሴት ሠራተኞች የተሻለ ክፍያ፣የተሻለ የሥራ ሰዓትና የምርጫ መብት እንዲከበርላቸው ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ምክንያት የመጀመሪያው አለም አቀፍ የሴቶች ስብሰባ በኮፐንሀገን .. 1910 . መጀመሩን ጠቅሰው ከዚያም የሴቶች ቀን በሁለተኛው ኢንተርናሽናል ስብሰባ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በጀርመናዊቷ ክላሪዜትኪን ሀሳብ አቅራብነት  .. 1911 .  በሁሉም ሀገራት በተመሳሳይ ቀን መከበር መጀመሩን ገልጸዋል።

 

በዚህም መሠረት እያከበርን ያለነው ይህ የሴቶች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ 106 ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ 41 ጊዜ መሆኑን ጠቅሰው ይህንንም መነሻ በማድረግ ሀገራችን በተለይ በኢ... መንግሥት መሪነት የሠርዓተ ጾታ እኩልነትን ለማስፈንና ሴቶችን በሁለንተናዊ መልኩ ለማብቃት ቀልፍ የሆኑትን አብዛኛዎቹን ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን ፈርማ ከመተግበር በተጨማሪ የህግ፣የፖሊሲና የስትራቴጂ ማዕቀፎችን በመዘርጋት ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚትገኝ ተናግረዋል። ህገ-መንግሥቱን መሠረት አድርገው በሚወጡ ህጎች፣ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች የሴቶችን እኩል ተሳትፎነና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ታሳቢ የተደረጉና ሀገራችን ባስመዘገበቻቸው ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ እድገቶች ውስጥ ሴቶች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥረት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ እና ይህንንም ጥረት በከፊል ለማሳየት ሴክተራችንን ወስደን ብናይ ከየሴቶች የትምህርትና ሥልጠና ተሳትፎና ውጤታማነት አንጻር የሥርዓተ ፆታ ምጥጥን  1 እስከ 4 ክፍል 0.90 5 እስከ 8 ክፍል 0.96 9 እስከ 10 ክፍል 0.93፤ከ11 እስከ 12 ክፍል 0.87 የደረሰ ሲሆን በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና የሴቶች ተሳትፎ 52.3% ደርሷል። በከፍተኛ ትምህርትም 2009 በጀት አመት ዓመታዊ ቅበላችን ብቻ ወስደን ካየነው 41% ደርሷል።

 

/ ኤልሳቤጥ በዓሉ የህዳሴ ግድባችንን የምስረታ በዓል 6 ዓመት ምክንያት በማድረግ ከየካቲት 22-29/2009. በልዩ ሁኔታ ቦንድ በመግዛት የሚከበር መሆኑን አስገንዘበዋል። / ኤልሳቤት በማከል ለበዓሉ ተዳሚዎች በተለይ በቅርብ ጊዜ ባካሄድነው የጥልቅ ተሃድሶ መድረክ የተገኙ ጭብጦችን መሠረት በማድረግ ሀገራዊ የልማትና ዲሞክራሲ ግንባታን ለማሳካት በሚደረገው ርብርብ የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከት የሚጠበቅብን መሆኑን፣ ለዚህም አቅማችንን ገንብተን ለመለወጥና ለመሻሻል ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ እና በተለይ እኛ ሴቶች በተገኙ ምቹ ሁኔታዎች ሁሉ ተጠቅመን ራሳችንን ለማውጣት ጊዜው አሁን ስለሆነ ልንጠቀምበት ይገባል በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።  በዓሉን ምክንያት በማድረግም በዕለቱ በዘርፉ 2009 በጀት ዓመት ባለፉት 6 ወራት ከየሥራ ክፍሎች በሥራ አፈጻጸማቸው ግንባር ቀደም ሆነው የተመረጡ 43 ሴት ሠራተኞች እያንዳንዳቸው  1,300 ብር ቦንድ ተሸልመዋል።


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡