ዜናዎች ዜናዎች

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የለውጥ ምክር ቤት ጉባኤ በደሴ ከተማ ተካሄደ

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቋማዊ ለውጥ ምክር ቤት ጉባኤ ጥር 23 እና 24 2009 በደሴ ከተማ አማራ ክልል ተካሄደ፡፡ ጉባኤውን ያዘጋጀው የወሎ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ ወርቅነህ መኮንን የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው ውስጥ የሚከተሉትን መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዩኒቨርሲቲውን ከተቋቋመ ጀምሮ እስከ አሁን 2 ጀነሬሽን ዩኒቨርሲቲ አንደመሆኑ መጠን በቆይታው አቻዎቹን ካገጠሙት አይነት በርካታ ችግሮች በተጨማሪ በተለየ መልኩ ጋና ከጅምሩ የአመራር አለመረጋጋት ችግሮች ያገጠሙት መሆኑንና ከቅርብ አመታት ወዲህ እነዚህን ችግሮች በሙሉ ፈቶ ዘሬ ድህነትን ለማስወገድ በሚደረገው  ትግል ውስጥ በአስተሳሰቡና በእውቀቱ የበቃ የሰው ኃይል ከማሰልጠን ጎን ለጎን ከደሴ ከተማ፣ ከደቡብ ወሎና ከኦሮሞ ብሔረሰብ ዞኖች ጋር በመቀናጀት በጋራ እቅድ የሚመራ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንና እስከ አሁን የተገኙ ውጤቶችም በህብረተሰቡ ዘንድ  ከፍተኛ ይሁንታን ማስገኘታቸውን ጠቅሰው ነገር ግን መጠንን በማሳደግና ፍጥነትን ከመጨመር አንጻር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ክቡር አቶ ወርቅነህ አክለው የሀገራችን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በየጊዜው የመጨመርና የሚጠይቀውን የመምራት አቅም ለማሟላት የዚህ የለውጥ ምክር ቤት መድረክ ፋይዳ ትልቅ በመሆኑ ተቋማት በሀገራችን በሁለንተናዊ መልክ የሚገለጸውን ድህነት ማስወገድ ብቻ ሳይሆን ዘመኑ የፈጠራቸውን ፍላጎቶች ለማሟላት ይችሉ ዘንድ የተቋማቱ ማህበረሰብ የፈርጀ ብዙ እውቀትና ክህሎት ስብስብ እንደመሆናቸው መጠን ባላቸው አቅም ከመተግበር ጎን ለጎን የጎደላቸውን እርስ በርስ እየተማማሩ እየሞሉ እንዲሄዱ በማድረግ ረገድ ይህ መድረክ ትልቅ መሳሪያ እንደሆነ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የኢ... ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ (ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ) የሆኑት  ክቡር / ሳሙኤል ክፍሌ በመክፈቻ ንግግራቸው የሚከተሉትን መልዕክቶች አስተላልፈዋል። ባለፉት የተቋማዊ ለውጥ ምክር ቤት ጉባኤዎች የትምህርት ጥራትን፣አግባብነት፣ተደራሽነት፣ፍትሃዊነትና ተቋማዊ መልካም አስተዳደርን ለማሻሻል የተካሄዱ ምክክሮች፣ የልምድ ልውውጦች፣ በጋራ ተወስነው የተቀመጡ አቅጣጫዎችና በአቅጣቻዎቹ መሠረት በተሠሩ ሥራዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደጉ የመጡ ውጤቶች የተመዘገቡ መሆናቸውን ጠቅሰው በያዝነው የበጀት ዘመን በልዩ ትኩረት መፈጸም የሚባቸው በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ 26ኛው የትምህርትና ሥልጠና ጉባኤ ወቅት በተናጥልና በጋራ መድረክ የተቀመጡ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።  ክቡር / ሳሙሙል 34ኛው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማዊ ለውጥ ምክር ቤት ጉባኤ ዋነኛ ዓለማም የነዚህ አቅጣጫዎችን አፈጻጸምና የትምህርትና ሥልጠናን በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ከመደገፍ አንጻር ባሉት ቀሪ ጉዳዮች ላይ እንደሚሆን ጠቅሰው የመምህራን ልማት ሥራችን ያለበትድ ደረጃ በመለየት የወደፊት አቅጣጫ ማስቀመጥ እና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች፣ምክትል ፕሬዝዳንቶችና የአስተዳደር ቦርድ አመራር አባላት ምልመላና ስምሪት መመሪያን የማዳበር ሥራ የሚከናወን መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ የከፍተኛ ትምህርትና ምርምር ኔትዎርክ ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች መካከል በጥቅም ላይ የዋለውና ያልዋለውን በማነጻጸር ገለጻ የቀረበ መሆኑ፣በICT አጠቃቀም ዙሪያ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተሞክሮ፣የከፍተኛ ትምህርት 6 ወራት አበይተ ተግባራት፣የለውጥ ሥራዎችና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች አፈጻጸም፣የከፍተኛ ትምህርት የግምገማ ስታንዳርድና የምርጥ ተሞክሮ ቅመራን በተመለከተ የተዘጋጀ ረቂቅ ሀሳብ፣በከፍተኛ ትምህርት የመምህራን ልማት 07030 ምጣኔ ማሳኪያ ስልቶችን በተመለከተ እና የከፍተኛ ትምህርት የአመራር ምልመላና ስምሪት መመሪያ ረቂቅ ገለጻና ሪፖርት ቀርበው ውይይት ተካሂዶበቸዋል።

በመጨረሻም ክቡር ሚኒስትር / ሽፈራው /ማሪያም ባሉበት በጋራ ስምምነት ላይ የተመሠረቱ የትኩረት አቅጣጫዎች ተቀምጠው መድረኩ ፍጻሜውን አግኝቷል። ከተቀመጡት የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል የሚከተሉትን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል። እያንዳንዱ ዩኒቨርሲቲ በያዘነው 2 የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን አንድ 2 ደረጃ ትምህርት ቤትን ከሁለንተናዊ የትምህርት ጥራት ወወጤቶች አንጻር ማበልጸግ ያለበት መሆኑ፣ በቀጣይ በሁለንተናዊ መልኩ ICT የተደገፈ የመማር ማስተማር፣ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ሥራዎች መከናወን እንዳለባቸው፣ኪራይ ሰብሳቢነትን ለማክሰም የሚደረገውን ትግል ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑ፣ ያለፉትን የኦዲት ግኝቶች ከማረም በተጨማሪ ለወደፊቱ የኦዲት ግኝቶችን በሚገባ ለመቀነስ ህግና መመሪያን ብቻ ተከትሎ የመሥራት ጉዳይ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑ፣ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን የማረጋገጥ በእቅድ ተይዞ ቅድሚያ ተሰጥቶት መሠራት ያለበት ጉዳይ መሆኑን፣ለየመምህራን ልማትን እንደ አጠቃላይም ሆነ ከጾታ ስብጥር አንጻር በሚገባ ለማሳደግ ግለሰብን ጭምር የሚያመላክት ዝርዝር እቅድ ታቅዶ ሊሠራበት እንደሚገባና የመሳሰሉት አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።No comments yet. Be the first.
ዜናዎች

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚካሄዱ የትምህርትና ሥልጠና ሥራዎች ውጤታማነት ተማሪዎች፣ መምህራን ፣ወላጆችና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸውን በላቀ ደረጃ ሊወጡ እንደሚገባ የትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ አስታወቁ፡፡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ህብረ-ብሔራዊነትና ኢትዮጵያዊነት የሚገነባባቸው ተቋማት እንጂ ተግባራቸው በጥቂት ችግር ፈጣሪዎች የሚስተጓጎል አለመሆኑንም ገለጹ 141ሺህ አዲስ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ700 ሺህ በላይ ተማሪዎች በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በመማር ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምረቃ ትምህርት መስኮች የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና (የመውጫ ፈተና) ልተገበር ነው

ከ2011 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም የቅድመ ምርቃ ትምህርት መስኮች ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት የብቃት መለኪያ አጠቃላይ ምዘና (የመውጫ ፈተና) ወስደው አጥጋቢና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን በተለይም የምሩቃንን ብቃትና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ አጠቃላይ ምዘና ወይም የመውጫ ፈተና መስጠት የምሩቃንን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለመመዘን የላቀ ሚና ከመጫወቱም በተጨማሪ የተመራቂ ተማሪዎች በራስ መተማመን ያጎለብታል፡፡

የምርምርና የፈጠራ ስራ ውድድር ኤግዚቪሽን ተካሄደ

የሂሳብና ሣይንስ ትምህርቶች ማሻሻያ ማዕከል ከስቴምስ ሲነርጂ ፣ከዩኔስኮ እና ከኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ጋር በመተባበር "በሣይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ የበለፀገ ህብረተሰብ ለዘላቂ ሠላምና ልማት "በሚል መሪ ቃል አገር አቀፍ የምርምርና ፈጠራ ስራ ውድድር ኤግዚቪሽን በኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ተካሄደ፡፡ የምርምርና የፈጠራ ስራ አውደ- ርዕይ መከፈቱን አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሣይንስ አካዳሚ የኢትዮጵያን ሣይንስ ለማበልፀግ የተቋቋመ መሆኑን አስታውሰው ይህ ማዕከል የህብረተሰቡን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ እንዲሁም ቴክኖሎጂን የመጠቀም አቅሙን ለማጎልበት ለማስተማርና የሣይንስ ፖርሽን ለመፍጠር የተሰራ ሲሆን ቋሚ የሳይንስ ማዕከል ለመፍጠር ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡ በመሆኑም በቅርቡም የሳይንስ ማዕከሉ ወደ ስራ ይገባል በዚህም ወጣቱ ወደ ሣይንስ በሄደ ቁጥር የሀገራችን ተስፋ እየለመለመ ይሄዳል ብለዋል፡፡

የሥርዓተ-ፆታ ማካተትና ተቋማዊ ማድረግ መከታተያ፣ መመዘኛና በደረጃ የመለያ ማዕቀፍ ላይ ስልጠና ተሰጠ

የትምህርት ሚኒስቴር ሥርዓተ ፆታ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሁሉም የሥራ ክፍሎች እና ከተጠሪ ተቋማት ለተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ባለው ስልጠና የሁለተኛ ቀን ውሎ በሥርዓተ-ፆታ ማካተትና ተቋማዊ ማድረግ መከታተያ፣ መመዘኛና በደረጃ የመለያ ማዕቀፍ ላይ ስልጠና ሰጠ ፡፡ ስልጠናውን የሰጡት በዳይሬክቶሬቱ የስርዓተ ፆታ ክትትልና ድጋፍ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ብርሃኑ አረጋ ሲሆኑ የዚህ ስልጠና ዋና አላማ በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ያሉ የስራ ክፍሎች የሥርዓተ ፆታ እኩልነትና ሴቶችን ማብቃት ተቋማዊ ለማድረግ የሚያከናውኑትን ተግባራት በመመዘንና ተከታታይ ድጋፍ በመስጠት የሥርዓተ ፆታ እኩልነት በሁሉም ዘርፍ ለማረጋገጥ ብሎም የሀገራችንን የልማት ራዕይ ለማሳካት ነው ብለዋል፡፡

የመንግስታዊና ግብረሰናይ ድርጅቶች የጋራ ፎረም ውይይት ተካሄደ፡፡

ዛሬ ጥቅምት 20/2010 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አዳራሽ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በትምህርት ስልጠና ዘርፍ የ2010 ዓ.ም ዋና ዋና ዕቅዶች ላይ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ተገኝተው የመድረኩን አላማ የገለጹት በትምህርት ሚኒስቴር የእቅድ ዝግጅትና ሃብት ማፈላለግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ግርማ የመድረኩ ዋና አላማ የትምህርት ሴክተሩ እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት ማድረግ ነው ብለዋል፡፡