የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማስፈንም ሆነ የህዳሴ ጉዟችንን ለማሳካት አዎንታዊ ሚና አላቸው

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማስፈንም ሆነ የህዳሴ ጉዟችንን ለማሳካት አዎንታዊ ሚና አላቸው

Higher Education Preparation

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 2009 የትምህርት ዘመን በምርምር ፣በመማር ማስተማርና በማህበረሰብ አገልግሎት ከመቼውም ጊዜ የበለጠ የላቀ አፈፃፀም ለማስመዝገብ በቂ ዝግጅት ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን 2009 . የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የዝግጅት ምዕራፍ ላይ ለመወያየት በተዘጋጀ መድረክ ላይ እንደተናገሩት 2008 . የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማስፈንም ሆነ የህዳሴ ጉዟችንን ለማሳካት የሚደረገውን ጥረት በማገዝ ረገድ የተጫወቱት ሚና አዎንታዊ መሆኑን አቶ ደመቀ አስታውቀዋል፡፡

ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ከሌለ ስለ ምርምርና ዕድገት ማሰብ ፈፅሞ የማይቻል ነገር ነው ያሉት አቶ ደመቀ በአገልግሎት አሰጣጥ ፣በመልካም አስተዳደር እንዲሁም በሃብት አጠቃቀም ዙሪያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትየተጠናከረ ስራ መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

ሀገራችን እያስመዘገበች ያለችው ኢኮኖሚያ ዕድገት ከሚፈልገው የሰለጠነ የሰው ሃይል አኳያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከዚህም በላይ መጠናከር አለባቸው ያሉት // ደመቀ ይህንን በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ በተለየ ዝግጅት ተጠናክረው መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን ሃላፊነት ለመወጣት የሚያስችላቸው እንቅስቃሴ ውስ ሊገቡ ይገባል ብለዋል፡፡

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስትር ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩላቸው 2009 . የሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የዝግጅት ምዕራፍ በስልጠና እንደሚጀመር ጠቁመው ከዩኒቨርሲቲው አመራር አካላት ጀምሮ እስከ ተማሪዎች ድረስ በስልጠናው እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት ተመሳሳይ ስልጠናዎች መሰጠታቸውን ያስታወቁት አቶ ሽፈራው በዚህም ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሁኔታን በማረጋገጥ፣የመልካም አስተዳደር በማስፈን፣የተማሪዎች ውጤት በማሻሻልና ኪራይ ሰብሳቢነትን በመቀነስ ረገድ በቀጣይነት እያደገ የመጣ ለውጥ መኖሩን ተናግረዋል፡፡

2008 . ከሞላ ጎደል በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ምንም ዓይነት ችግር ሳይከሰት የመማር ማስተማር ሂደቱ መቀጠሉን የተናገሩት አቶ ሽፈራው ችግር ባጋጠመባቸው አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎችም ቢሆን ቦርዱ፣ተማሪውና አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተጋግዘውና ተደጋግፈው ችግሮችን በመፍታት የትምህርት ዘመኑ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ በማድረጋቸው ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርትና ቴክኖሎጂ ሰራዊት ገንብተው የመማር ማስተማር እና የማህበረሰብ ልማት አገልግሎትን በተሟላ ሁኔታ ከመስጠት አንፃር እያደገ የመጣ ጥንካሬ ቢኖራቸውም ወደሚፈለገው ደረጃ ያለመድረሱ በክፍተት የሚጠቀስ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ካባ ኡርጌሳ እንደተናገሩት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን ከማረጋገጥ ባለፈ አንድ የጋራ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ለአንድ ቀን በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢዎች፣የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና ምክትል ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ተገኝተዋል፡፡

Higher Education Preparation


ዜናዎች

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡