Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Ministry of Education  
Homepage Home Page Students Page for Students Educators Page for Educators Businesses Page for Businesess Doners and Partners Page for Doners and Partners Decrease font Increase font

 ተጠሪ መስሪያ ቤቶች

 በድጋሚ የምስክር ወረቀት እንዲዘጋጅላቸው መጠየቅ

   አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጉ መስፈረቶች 

·        ስድስት ወር ያልሞላው 1 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ሁለቱም ጆሮዎች የሚታዩበት

·        የቀበሌ ነዋሪነት መታወቂያ

·        ተወካይ ከሆነ የውክልና ማረጋገጫ ደብዳቤና የማንነት ማረጋገጫ መታወቂያ
 

አገልግሎቱን ለማግኘት የሚከናወኑ ሂደቶች 

1.     ምዝገባ ክፍል በመሄድ የሚሞላ ፎርም ይወሠዳል

2.     የተሞላውን ፎርም በዛው ቢሮ ማስገባት

3.     የሚመለከተው አካል ማመልከቻውን ይመለከታል

4.     ማመልከቻውን ከተመለከተ በኋላ የአገልግሎት ክፍያ እንዲፈፀም ማመልከቻው ላይ ፈርመው ወደ ገንዘብ ቤት ይመራል

5.     የተመራውን ደብዳቤ በመውሠድ ገንዘብ ቤት እንደ አገልግሎቱ ክፍያ ይከናወናል

6.     የተከፈለበትን ደረሰኝ በመዝገብ ቤት ይዞ ይሄዳል

7.     በዛው ቢሮ ቀጠሮ ይሠጠዋል

8.     በተሠጠበት ቀጠሮ መታወቂያ ይዞ በመምጣት የትምህርት ማስረጃውን የሚመለከተው አካል ይወስዳል