በ2003 ዓ.ም በመጀመሪያ ድግሪ በተሻለ ውጤት ተመርቃችሁ ለረዳት ምሩቅነት ላመለከታችሁ በሙሉ
የዩኒቨርሲቲዎችን የረዳት ምሩቅ የቅጥር ፍላጐት መሠረት በማድረግ ለተመረጣችሁ ዕጩ ረዳት ምሩቃን በዋና ዋና የሀገሪቱ የልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ላይ ከነሐሴ 1/2003 ጀምሮ ለ11 ተከታታይ ቀናት ሥልጠና ይሰጣል፡፡ ስለሆነም ለሥልጠና የተመረጣችሁ በሙሉ ሐምሌ 30/2003 ዓ.ም አዳማ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት እንድታደርጉ እያሳሰብን፣ በዕለቱ ሪፖርት በማያደርግ ምሩቅ ፋንታ ከተጠባባቂ ለመተካት የምንገደድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ
- ሠልጣኞች የተመረጡት ከዩኒቨርሲቲያቸው በደረሰን የእንግሊዝኛ ቋንቋ መመዘኛ እና በቆይታቸው በነበራቸው የሥነ ምግባር ውጤት “C” እና ከዚያ በላይ ያላቸው ሆኖ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው አጠቃላይ ውጤት (CGPA) መሠረት ነው፡፡
- በሥልጠና ጊዜ የሠልጣኞችን የምግብ የመኝታና ለድንገተኛ ህመም የህክምና ወጪን ትምህርት ሚኒስቴር የሚሸፍን ሲሆን፣የትራንስፖርትና ሌሎች የግል ወጪዎች በራሳቸው በሠልጣኞች የሚሸፈኑ ይሆናሉ፡፡
- ሥልጠናውን በተሟላ ሁኔታ ያልተሳተፈ በረዳት ምሩቅነት አይመደብም፡፡
Please click here to view the Selected Graduate Assistants list.
If you have a reasonable appeal, please send email to: moe.heducation@yahoo.com.