የትምህርት ሚኒስቴር ራዕይ
እድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ ህፃናት በሙሉ በ2008 ጥራት ያለው የ1ኛ ደረጃ ትምህርት እንዲያገኙ፣ እንዲሁም በየደረጃው
/በመጀመሪያ ደረጃ፣ በ2ኛ ደረጃ፣ በቴክኒክና ሙያ፣ በከፍተኛ ትምህርት/ በልማትና በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አወንታዊ ሚና
የሚጫወቱ መልካም ዜጐችን ለማፍራት የሚያስችል ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ የትምህርት ሥርዓት ተዘርግቶ ማየት፣
የትምህርት ሚኒስቴር ተልዕኮ
ህገ መንግሥቱ ለዜጎች የሰጠውን መብትና ግዴታ የሚያከብሩና የሚያስከብሩ፣ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችላቸውን አቅምና ፍላጎት
ለማዳበር የሚተጉ፣ በተለያየ ሙያ ሠልጥነው በኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ በንቃት የሚሳተፉ፣ ለልማት፣ ለዲሞክራሲ ግንባታ እንዲሁም
ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገትና ሥርፀት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ዜጎችን ማፍራት፣
የትምህርት ሚኒስቴር ዕሴት
-
ትምህርትን በጥራትና በፍትሐዊነት እንዲስፋፋ በቆራጥነት እንጥራለን፣
-
ተልዕኮአችንን ለመወጣት ሁል ጊዜ እራሳችንን እናበቃለን፣
-
የትምህርትን የልማት መሣሪያነት በተግባር እናረጋግጣለን፣
-
ህዝብን በታማኝነትና በቅንነት እናገለግላለን