የትምህርት ችግሮች መንስኤዎች ከሌሉች ሁኔታዎች ጋር ተዳምረው በአገራችን ትክክለኛ የትምህርት ፖሊሲ አለመኖር ትምህርት በዓላማው
በይዘቱ በማስተማር መማር ሥነ-ዘዴው በሥርጭቱ በአደረጃጀቱ በአስተዳደሩ በፋይናንስ በምርምሩ በድጋፍ ሰጪዎች ወዘተ ብቃት ማጣት
ናቸው፡፡
ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ ተስማሚ የትምህርት ፖሊሲ ማስፈለጉ አያጠያይቅም በመሆኑም አጠቃላይ የትምህርትና
ሥልጠና ፖሊሲ ተዘጋጅቷል:: ፖሊሲው ከሕፃናት አስተዳደግ ጀምሮ እስክ ከፍተኛ ትምህርት ድረስ ልዩ ትምህርትን ጨምሮ ያለውን
መደበኛና መደበኛ ያልሆነ ትምህርት አጠቃላይና ዝርዝር ዓላማዎችን እንዲሁም ሥልቶችንና ተግባሮችን አጠቃልሉ በሚያሳይ መልኩ
ተቀርጿል፡፡
ትምህርት የችግር ፈቺነትን አቅምና ባህል ለማጎልበት እንዲያስችል የትምህርት ይዘት የሥርዓተ ትምህርት
አወቃቀር የትምህርት አቀራረብ የትምህርት ቅስሞሽ ሳይንሳዊና ተግባራዊ እንዲሆን ያስገነዝባል፡፡ ከዚህ ጋር በማያያዝ ትምህርት
ምርምርና ልዩ ልዩ ሥልጠናዎች የልማት መሥሪያ ቤቶችና ድርጅቶች አስተዋጽኦ ተገቢው ተስተጋብሮት እንዲኖራቸው ፈር ያስይዛል፡፡
የትምህርት እርከንን ከተማሪው የባሕርይ ገጽታዎች ጋር አገናዝቦ ይገልጻል፡፡ ትምህርትና ሥልጠና የሚያስገኙዋቸው የባሕርይ
ለውጦችና ውጤቶችን ለመገምገም የትምህርት ምዘና ምን መሆን እንዲኖርበት ያመለክታል፡፡ በትምህርትና በማስተማሪያ ቋንቋ ረገድም
ሲሆን የሚገባውንና የሚቻለውን ያስቀምጣል፡፡ እንዲሁም የመምህርነት ሙያ በመማር ማስተማር ሂደት ትውልድን በእውቀት በአስተሳሰብ
በችሎታና በክህሎት የመቅረጽ ኃላፊነት ያለበት እንደመሆኑ ለማሠልጠኛ ተቋሞች አደረጃጀት ለሠልጣኞች ምልመላ ለሥልጠና መርሐ
ግብሮችና ሥነ-ዘዴዎች ለመምህራን መራሔ ሙያ ለሥራ ለእድገትና ለኑሮ ሁኔታ የሚሰጠውን ትኩረት ይገልጻል፡፡
ለመማር
ማስተማር ሂደት መጠናከርና መስፋፋት የትምህርት መሣሪያዎች የትምህርት ቴክኖሎጂና የትምህርት ፋሲሊቲ በተገቢው ሁኔታ መቅረባቸውና
ለተፈላጊው ተግባር በትክክል መዋላቸው የሚረጋገጥበትን ሥርዓት ይጠቁማል አመቺ የትምህርት አካባቢ መፈጠር እንደሚኖርበት
የትምህርት አደረጃጀትና አመራርም ዲሞክራሲያዊና ሙያዊ ሆኖ ቀልጣፋና ቀና በሁሉም አቅጣጫ ቅንጅት ባለውና ባልተማከለ አሠራር
ተገቢውን ውጤት የሚያስገኝ እንዲሆን ያስገነዝባል፡፡
የትምህርት ፋይናንስና ምንጭ አደላደሉና አጠቃቀሙ ትምህርትን
በጥራትና በስፋት ለማዳረስ የሚያስችል እንዲሆንና ፍትሃዊ ቀልጣፋ ቀናና ለመማር ማስተማሩ ሂደት አመቺ አሠራር የሚፈጠርበትን
ሥርዓት ይጠቁማል፡፡ስለሆነም የሀገርና የሕዝብ ችግሮችን ለመፍታት የተዘጋጀና ሰብአዊና አገራዊ ኃላፊነት የሚሰማው ዲሞክራሲያዊና
ሰብአዊ አመለካከቱ የተስተካከለ ከተፈጥሮ ተጽእኖ በተግባር ለመላቀቅ የተዘጋጀ የማምረትና የመመራመር አቅሙ የዳበር ዜጋ
ለማዘጋጀት የሚያስችል አጠቃላይ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ ቀርቧል፡፡