Embelem of Federal Democratic Republic of Ethiopia Official Portal of Ministry of Education  
Homepage Home Page Students Page for Students Educators Page for Educators Businesses Page for Businesess Doners and Partners Page for Doners and Partners Decrease font Increase font

 ተጠሪ መስሪያ ቤቶች

 የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ

የከፍተኛ ትምህርት አገባብነትና ጥራት ኤጀንሲ (ከትአጥኤ) ራሱን የቻለ ህጋዊ ሰውነት ያለው አካል ሆኖ በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 351/1995 የተቋቋመ ሲሆን ተጠሪነቱም ለትምህርት ሚኒሰቴር ነው፡፡

የኤጀንሲው ራዕይ

አገር አቀፍና አለም አቀፍ እውቅና ያለው በከፍተኛ ተቋማት የሚሰጠውን ትምህርት ጥራት የሚቆጣጠር የሚገመግምና እውቅና የሚሰጥ፤ተቋማት የሚሰጡትን ትምህርት ጥራትና ደረጃ እንዲያበለፅጉ ድጋፍ የሚያደርግ ማዕከል መሁን ነው፡፡

ተልዕኮ

በኢትዮጵያ አግባብነትና ጥራት ያለው የከፍተኛ ትምህርት ስርዓት ማረጋገጥ ነው፡፡ ለዚህም

  • ዕውቅና የተሰጣቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተገቢውን ደረጃ የጠበቁ ስለመሆናቸው ለሁሉም ባለድርሻ አካላት የረጋግጣል፡፡
  • በነዚህ እውቅና በሰጣቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የትምህርት መርሀግብሮች ተገቢውን ጥራት የጠበቁና የስራ ዓለምና የሀገሪቱን የልማት ፍላጎት የሚያሟሉ መሆናችውን ያረጋግጣል፤
  • የኢትዮጵያን የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ አግባብነትና ጥራት ለማጎልበት የሚደረገውን ጥረት ያግዛል፡፡

ዓላማዎቹ

በከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር 351/1995 መሰረት ኤጀንሲው በማንኛውም የትምህርት የከፍተኛ ተቋም የሚሰጠውን የትምህርት አገልግሎት አግባብንትና ጥራት የመቆጣጠር ዓላማ ይኖረዋል፡፡

የኤጀንሲው ስልጣንና ተግባር

በአዋጅ ቁጥር 351/1995 ከተገለፀው የኤጀንሲው ስልጣንና ተግባራት መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

  • በማንኛውም ተቋም የሚሰጡ የከፍተኛ ትምህርት ስልጠናዎች ደረጃቸውን የጠበቁ አግባብነትና ጥራት ያላቸው መሆናችውን ያረጋግጣል፡፡
  • በማንኛውም ተቋም የሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት ስልጠናዎች ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ፤ ማህበራዊና ሌሎች አግባብነት ያላቸው ፖሊሲዎች ጋር መገናዘባቸውን ያረጋግጣል፡፡
  • በዚህ አዋጅና አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ለሚኒስትሩ ወይም ለኤጀንሲው የቀረበን የቅድመ እውቅና ፈቃድ፤ የእውቅና ፈቃድ ወይም የእውቅና እድሳት ፈቃድ ጥያቄን መርምሮ ለሚኒሰትሩ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል፡፡
  • ተቋማቱ ያሉበትን ሁኔታና ደረጃ በየጊዜው ለህዝብ በተለያዩ መንገዶች ያሳውቃል፡፡