4ኛው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጉባኤ በድሬደዋ ከተማ ተካሄደ

4ኛው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጉባኤ በድሬደዋ ከተማ ተካሄደ

4ኛው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ-እንዱስትሪ ትስስር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጉባኤ የተካሄደው በትምህርት ሚኒስቴርና GIZ  ትብብር እንዲሁም በሀረማያ ዩኒቨርሲቲና በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ነበር።

 

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት / ግርማ ጎሮ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው ውስጥ የሚከተሉትን መልዕክት አስተላልፈዋል። የከፍተኛ ትምህርት ቋማትና ኢንዱስትሪዎች መካከል ያለው ትብብር በትምህርትና  ስልጠና ውስጥ ለክህሎት ማዳበር፣ ለእውቀት ናቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም የስራ ፈጠራን  ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በሚገባ ከተተገበረ  የሰልጣኞች የአቅም ክፍተት ከማጥበብ ባለፈ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ውጤታማ ምርምር ለማካሄድና አግባብነት ያለው የማህበረሰብ አገልግሎት ለመስጠት አመቺ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። / ግርማ አክለው በአሁኑ ወቅት ያለውን  የዩኒቨርሲቲ- እንዱስትሪ ትስስር የበለጠ መደበኛና ጠንካራ በማድረግ  ለሀገር ማበርከት በሚገባው አስተዋጽ ልክ ትኩረት ሰጥቶ በሁለንተናዊ መልኩ ሊሠራበት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በጉባኤው በኢ... ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የትምህርትና የምርምር ጉዳዮች ጀኔራል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት / ዘርሁን ከበደ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑትን ክቡር / ሳሙኤል ክፍሌን በመወከል የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በመክፈቻ ንግግራቸው የሚከተሉትን መልዕክቶች አስተላልፈዋል። የጀመርነውን የኢኮኖሚያዊ መዋቅር ሽግግር ለማካሄድም ሆነ የሀገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ በዓለም ከተፈጠሩ ቴክኖሎጂዎች መካከል የሚጠቅሙንን ለይተን ለመቅዳት፣ለማሻሻልና በሂደትም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እየፈጠርን ለመሄድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣እንዱስትሪዎች፣የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት፣የምርምር ማዕከላት በተቀነጀና በተደራጀ መልኩ በተግበር ላይ የሚያውሉት እቅም ሊኖራቸው እንደሚገባ ጠቅሰው ከዚህ አንጻር የዩኒቨርሲቲ- እንዱስትሪ ትስስርን ያማከለ የቴክኖሎጂ  ሽግግር ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው  ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

 

የዩኒቨርሲቲ-እንዱስትሪ ትስስር በጋራ መጠቃቀም ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንደሆነና የሚከተሉት ጥቅሞች እንዳሉት ለአብነት ጠቅሰዋል። ዩኒቨርሲቲዎች በእንዱስትሪዎች ያሉትን የሰው ኃይል እጥረትንም ሆነ ክፍተት በቅርበት ተከታትለው እንዲሞሉ እድል የሚሰጥ መሆኑን፣ዩኒቨርሲቲዎች በእንዱስትሪ ምርታማነትና ጥራት ላይ የጋራ የሆነ ምርምር በመሥራት የእንዱስትሪዎች ምርታማነትና የምርቶች ጥራት እንዲያድግ እድል የሚሰጥ መሆኑን፣ዩኒቨርሲቲዎች በእንዱስትሪዎች የምርት አመራረትና አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ የሚታዩትን ችግሮች በጥናትና ምርምሮች እንዲፈቱ እድል የሚሰጥ መሆኑን፣እንዱስትሪዎች በነባራዊ እውቀት ላይ ብቻ ከመሞርኮዝ ይልቅ ዘመን ያፈራቸውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንም በሥራ ላይ እንዲያውሉት እድል የሚሰጥ መሆኑን፣እንዱስትሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ሆነ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ተማሪዎች በንድፈ-ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት በተግባራዊ ልምምድ እንዲጨብጡ በማድረግ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት እንዲሻሻል የማይተካ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን አሁን ያለው የዩኒቨርሲቲ-እንዱስትሪ ትስስር ሀገሪቷ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ጥቅሞች በሚገባ አሟጣ ለማግኘት በሚያስችልኩ የተጠናከረ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ስለሆነም ሁለቱም ወገን እስከአሁን የነበረባቸውን የግልና ያጋራ ችግሮቻቸውን በመቅረፍ ትስስሩን በሚፈለገው መልኩ በማጠናከር ለሀገሪቷ የሰው ኃይል ልማትና የእንዱስትሪ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

 

በመድረኩ 3ኛው ጉባኤ ማጠቀለያ የቀረበ መሆኑ፣ ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ የሠራቸውን ሥራዎች በሚመለከት ልምዱን ያከፈለ መሆኑ፣ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ የሠራቸውን ሥራዎች በሚመለከት ልምዱን ያከፈለ መሆኑ፣በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና እንዱስትሪዎች መካከል ያለው ትስስርና ትብብርን በሚመለከት በጅማ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ልምድ የቀረበ መሆኑ፣በኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ኢንቲትዩት የተዘጋጀ የዩኒቨርሲቲ-እንዱስትሪ ትስስር ፍኖታ ካርታ የቀረበ መሆኑ፣አዳዲስ የንግድና የፈጠራ ሥራ ላይ የተሞረኮዙ ድርጅቶችን ማቋቋምን በተመለከተ በሥራ ፈጣሪ ግለሰብ ገለጻ የቀረበ መሆኑ፣ዩኒቨርሲቲዎች የሚያገኙትን የምርምር ውጤቶች በእንኩቤሽን ማዕከል አማካኝነት ወደ ንግድና ሀብት ፈጠራ ለመለወጥ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን በሚመለከት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንኩቤሽን ማዕከልን በማሳያነት የወሰደ ገለጻ የቀረበ መሆኑ፣ ከቴክኖሎጂ ሽግግር አንጻር በአከባቢው በብዛት ከሚገኝ የዕጸዋት ተረፈ-ምርት በቃላሉ ከሰል የሚሠራበትንና ከሸክላ አፈር የእንጀራ መጋገሪያ ምጣድ የሚሠራበትን ባህላዊ አሠራር በማሻሻል መገዶ ቆጣቢና ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሚሰጥ ምጣድ የሚሠራበትን ቴክኖሎጂ ለማሸጋገር እየተሠራ ያለውን ሥራ በሚመለከት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ልምዱን ያከፈለ መሆኑ፣በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከዲዛይን አስከ ትግበራ ድረስ ከባለድርሻ አካለት ጋር በትብብር የተሠሩ ጥቃቅን የውሃ ኃይል ማመንጫዎችን በሚመለከት በጅማ ዩኒቨርሲቲ ገለፃ የቀረበ መሆኑ እና በተግባራዊ ልምምድ (Internship) ጊዜያቸው በተመደቡባቸው ሦስት የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ ሥራ የሠሩ 2008 በጀት አመት ምሩቃን ተማሪዎች ልምዳቸውን እንዲያቀርቡ ተደርገዋል።ከላይ በተዘረዘሩና በሌሎችም ተያያዥ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥየቄዎች ተነስተው በአቅራቢዎች መልስና ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።

 

በመጨረሻም 5ኛው የዩኒቨርሲቲ-እንዱስትሪ ትስስር ጉባኤ የትኩረት ነጥቦች ምን መሆን እንዳለባቸው ሀሳብ እንዲሰጡ ለተሳታፊዎች በተሰጠው እድል መሠረት ለቀጣይ ጉባኤ በሚሆን መልኩ ነባር የትኩረት ነጥቦችን ለመከለስ የሚያስችሉ ሀሳቦች ከተሳታፊዎች ተሰጥተው፣ 5ኛው ጉባኤ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት በጎንደር ከተማ እንደሚካሄድ ተወስኖና የመዝጊያ ንግግር በሀረማያ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳን በፕሮፌሰር ጨመዳ ፍኒንሳ ተደርጎ መድረኩ ፍጻሜውን አግኝቷል።


News

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለኤች አይቪ/ኤድስ ተጋላጭነት፤

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኤችአይቪ/ኤድስና ተያያዥ ጉዳዮች ዕቅድ አተገባበርና ውጤት በሚል ርዕሥ በአዳማ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ተሸማ ለማ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው እንደ ገለጹት በዚህን ሰዓት በሀገራችን 28 ሚሊዮን ማለትም ከ1/3ኛ በላይ ዜጎች በትምህርት ገበታ ላይ የሚገኙና ከእነዚህም በአፍላ ዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉት አምራች ሃይል የሆኑት ወጣቶች ለኤችአይቪ/ኤድስ በሽታ ተጋላጭ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎች በሲስተር-ሲስተር፣ አቻ ለአቻ፣ የህይወት ክህሎት ፕሮግራሞች እንዲመካከሩ፣ የማስተባበሪያ አደረጃጀቶች እና ክበባትን ማቋቋም፣መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና በዕቅድ አካተው የተሰራ ቢሆንም ተጋላጭነቱን ለመግታት የባህሪይ ለውጥ አሁንም አለመምጣቱን ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በ2010 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ተወያዩ፤

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር በ2010 በጀት ዓመት በቁልፍና አበይት ተግባራት ያከናወናቸውን ተግባራት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና መላው ሰራተኞች በተገኙበት ገምግሟል ፡፡ በግምገማው በርካታ ስኬታማ ስራዎች ቢሰሩም ከትምህርት ጥራት፣ ከትምህርት ግብዓት ማሟላት እንዲሁም ከባለሙያዎች ክህሎት ማነስ ጋር የተያያዙ መጠነ ሰፊ ችግሮች የነበሩበት በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሪፎርም ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቅሷል፡፡

የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ያደረጉት ውይይት፡

ተሳታፊ መምህራን ከ45ቱ የመንግስትና ከ4ቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቌማት የተውጣጡ 3ሺ175 ያህል ናቸው። በውይይቱም በርካታ ጥያቄዎች የተነሱ ቢሆንም ለተነሱት ጥያቄዎች የመምህርነት ሙያ የተከበረ እንደሆነና በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚያጋጥሙና ለሚስተዋሉ ችግሮች መምህራን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቌማት አመራር በጋራ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ጠ/ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምርቃት፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ-ግብር 8,152 ተማሪዎችን በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ሐምሌ 7/2010 ዓ.ም አስመርቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ክብርት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ፕሬዝዳንት በክብር እንግድነት የተገኙ ሲሆን ለተመራቂዎችም የስራ መመሪያ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡