News News

4ኛው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጉባኤ በድሬደዋ ከተማ ተካሄደ

4ኛው ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ-እንዱስትሪ ትስስር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጉባኤ የተካሄደው በትምህርት ሚኒስቴርና GIZ  ትብብር እንዲሁም በሀረማያ ዩኒቨርሲቲና በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ነበር።

 

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት / ግርማ ጎሮ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸው ውስጥ የሚከተሉትን መልዕክት አስተላልፈዋል። የከፍተኛ ትምህርት ቋማትና ኢንዱስትሪዎች መካከል ያለው ትብብር በትምህርትና  ስልጠና ውስጥ ለክህሎት ማዳበር፣ ለእውቀት ናቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም የስራ ፈጠራን  ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር በሚገባ ከተተገበረ  የሰልጣኞች የአቅም ክፍተት ከማጥበብ ባለፈ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ውጤታማ ምርምር ለማካሄድና አግባብነት ያለው የማህበረሰብ አገልግሎት ለመስጠት አመቺ ሁኔታን የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። / ግርማ አክለው በአሁኑ ወቅት ያለውን  የዩኒቨርሲቲ- እንዱስትሪ ትስስር የበለጠ መደበኛና ጠንካራ በማድረግ  ለሀገር ማበርከት በሚገባው አስተዋጽ ልክ ትኩረት ሰጥቶ በሁለንተናዊ መልኩ ሊሠራበት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በጉባኤው በኢ... ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የትምህርትና የምርምር ጉዳዮች ጀኔራል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት / ዘርሁን ከበደ የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑትን ክቡር / ሳሙኤል ክፍሌን በመወከል የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በመክፈቻ ንግግራቸው የሚከተሉትን መልዕክቶች አስተላልፈዋል። የጀመርነውን የኢኮኖሚያዊ መዋቅር ሽግግር ለማካሄድም ሆነ የሀገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ በዓለም ከተፈጠሩ ቴክኖሎጂዎች መካከል የሚጠቅሙንን ለይተን ለመቅዳት፣ለማሻሻልና በሂደትም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እየፈጠርን ለመሄድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣እንዱስትሪዎች፣የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት፣የምርምር ማዕከላት በተቀነጀና በተደራጀ መልኩ በተግበር ላይ የሚያውሉት እቅም ሊኖራቸው እንደሚገባ ጠቅሰው ከዚህ አንጻር የዩኒቨርሲቲ- እንዱስትሪ ትስስርን ያማከለ የቴክኖሎጂ  ሽግግር ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው  ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

 

የዩኒቨርሲቲ-እንዱስትሪ ትስስር በጋራ መጠቃቀም ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንደሆነና የሚከተሉት ጥቅሞች እንዳሉት ለአብነት ጠቅሰዋል። ዩኒቨርሲቲዎች በእንዱስትሪዎች ያሉትን የሰው ኃይል እጥረትንም ሆነ ክፍተት በቅርበት ተከታትለው እንዲሞሉ እድል የሚሰጥ መሆኑን፣ዩኒቨርሲቲዎች በእንዱስትሪ ምርታማነትና ጥራት ላይ የጋራ የሆነ ምርምር በመሥራት የእንዱስትሪዎች ምርታማነትና የምርቶች ጥራት እንዲያድግ እድል የሚሰጥ መሆኑን፣ዩኒቨርሲቲዎች በእንዱስትሪዎች የምርት አመራረትና አገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ላይ የሚታዩትን ችግሮች በጥናትና ምርምሮች እንዲፈቱ እድል የሚሰጥ መሆኑን፣እንዱስትሪዎች በነባራዊ እውቀት ላይ ብቻ ከመሞርኮዝ ይልቅ ዘመን ያፈራቸውን አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንም በሥራ ላይ እንዲያውሉት እድል የሚሰጥ መሆኑን፣እንዱስትሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትም ሆነ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ተማሪዎች በንድፈ-ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት በተግባራዊ ልምምድ እንዲጨብጡ በማድረግ የትምህርትና ሥልጠና ጥራት እንዲሻሻል የማይተካ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን አሁን ያለው የዩኒቨርሲቲ-እንዱስትሪ ትስስር ሀገሪቷ እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ጥቅሞች በሚገባ አሟጣ ለማግኘት በሚያስችልኩ የተጠናከረ እንዳልሆነ ገልጸዋል። ስለሆነም ሁለቱም ወገን እስከአሁን የነበረባቸውን የግልና ያጋራ ችግሮቻቸውን በመቅረፍ ትስስሩን በሚፈለገው መልኩ በማጠናከር ለሀገሪቷ የሰው ኃይል ልማትና የእንዱስትሪ ልማት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

 

በመድረኩ 3ኛው ጉባኤ ማጠቀለያ የቀረበ መሆኑ፣ ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ የሠራቸውን ሥራዎች በሚመለከት ልምዱን ያከፈለ መሆኑ፣ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ የሠራቸውን ሥራዎች በሚመለከት ልምዱን ያከፈለ መሆኑ፣በምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና እንዱስትሪዎች መካከል ያለው ትስስርና ትብብርን በሚመለከት በጅማ ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ልምድ የቀረበ መሆኑ፣በኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ኢንቲትዩት የተዘጋጀ የዩኒቨርሲቲ-እንዱስትሪ ትስስር ፍኖታ ካርታ የቀረበ መሆኑ፣አዳዲስ የንግድና የፈጠራ ሥራ ላይ የተሞረኮዙ ድርጅቶችን ማቋቋምን በተመለከተ በሥራ ፈጣሪ ግለሰብ ገለጻ የቀረበ መሆኑ፣ዩኒቨርሲቲዎች የሚያገኙትን የምርምር ውጤቶች በእንኩቤሽን ማዕከል አማካኝነት ወደ ንግድና ሀብት ፈጠራ ለመለወጥ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን በሚመለከት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንኩቤሽን ማዕከልን በማሳያነት የወሰደ ገለጻ የቀረበ መሆኑ፣ ከቴክኖሎጂ ሽግግር አንጻር በአከባቢው በብዛት ከሚገኝ የዕጸዋት ተረፈ-ምርት በቃላሉ ከሰል የሚሠራበትንና ከሸክላ አፈር የእንጀራ መጋገሪያ ምጣድ የሚሠራበትን ባህላዊ አሠራር በማሻሻል መገዶ ቆጣቢና ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሚሰጥ ምጣድ የሚሠራበትን ቴክኖሎጂ ለማሸጋገር እየተሠራ ያለውን ሥራ በሚመለከት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ልምዱን ያከፈለ መሆኑ፣በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከዲዛይን አስከ ትግበራ ድረስ ከባለድርሻ አካለት ጋር በትብብር የተሠሩ ጥቃቅን የውሃ ኃይል ማመንጫዎችን በሚመለከት በጅማ ዩኒቨርሲቲ ገለፃ የቀረበ መሆኑ እና በተግባራዊ ልምምድ (Internship) ጊዜያቸው በተመደቡባቸው ሦስት የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ ሥራ የሠሩ 2008 በጀት አመት ምሩቃን ተማሪዎች ልምዳቸውን እንዲያቀርቡ ተደርገዋል።ከላይ በተዘረዘሩና በሌሎችም ተያያዥ ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ የተለያዩ አስተያየቶችና ጥየቄዎች ተነስተው በአቅራቢዎች መልስና ማብራሪያ ተሰቶባቸዋል።

 

በመጨረሻም 5ኛው የዩኒቨርሲቲ-እንዱስትሪ ትስስር ጉባኤ የትኩረት ነጥቦች ምን መሆን እንዳለባቸው ሀሳብ እንዲሰጡ ለተሳታፊዎች በተሰጠው እድል መሠረት ለቀጣይ ጉባኤ በሚሆን መልኩ ነባር የትኩረት ነጥቦችን ለመከለስ የሚያስችሉ ሀሳቦች ከተሳታፊዎች ተሰጥተው፣ 5ኛው ጉባኤ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት በጎንደር ከተማ እንደሚካሄድ ተወስኖና የመዝጊያ ንግግር በሀረማያ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳን በፕሮፌሰር ጨመዳ ፍኒንሳ ተደርጎ መድረኩ ፍጻሜውን አግኝቷል።No comments yet. Be the first.
News

የ2009 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ (የ10ኛ ክፍል) ብሔራዊ ፈተና ከግንቦት 23- 25 እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና (የ12ኛ ክፍል) ከግንቦት 28 እስከ ሰኔ 1 2009 ዓ.ም. ይሰጣሉ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2009 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ (የ10ኛ ክፍል) ብሔራዊ ፈተና ከግንቦት 23- 25 እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተናዎች (የ12ኛ ክፍል) ከግንቦት 28 እስከ ሰኔ 1 2009 ዓ.ም. እንደሚሰጡ ገለጸ፡፡ የፈተናው አጠቃላይ ዝግጅት የተጠናቀቀ ሲሆን በሀገሪቱ ለሚገኙ ተፈታኞች 3,467 የፈተና ጣቢያዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ በዚህ ዓመትም ከ1.2 ሚሊየን በላይ የ10ኛ ክፍል እንዲሁም ከ288ሺህ በላይ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር በተፈጥሮ ሳይንስና ምህድስና ትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ሴት ተማሪዎችን ሸለመ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሥርዓተ ጾታ ዳይሬክቶሬት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሥርዓተ ጾታና ባለ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር በተፈጥሮ ሳይንስና ምህድስና ትምህርት መስክ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ከአንደኛ እስከ አምስተኛ አመት ያሉ ሴት ተማሪዎች፣ ድጋፍ ላደረጉላቸው መምህራንን እና አመራሮች የማበረታቻ ሽልማት ሰጠ፡፡ በዩኒቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አደራሽ ...

በሙያ ፍቃድ የምዘና ውጤት ትንተናና በመምህራን ትምህርት ኮሌጆች እውቅና አሰጣጥ ስታንዳርዶች ዙሪያ ምክክር መድረክ ተካሄደ

ሀገራችን የሙያ ፍቃድ አሰጣጥና እድሳት ስርዓት በመዘርጋት የመምራን፣ የርዕሰ መምህራንና የሱፐርቫይሮች ሙያዊ ብቃት ምዘና ሂደትን በወጥነት ለመተግበርና በሙያ ፍቃድ አሰጣጥ የአደረጃጀቶችን ሚናና የፈጻሚ ባለድርሻ አካለላትን ተግባርና ኃላፊነት ለይቶ ለማሳወቅና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚየስችል የአሰራር ስርዓት ዘርግታ እየሰራች ትገኛለች፡፡ በሙያ ፍቃድ አሰጣጥ ስርዓት ውስጥ ሶስት የሙያ ፍቃድ አይነቶች አሉ፡፡ እነዚህም፦ አንደኛው የመጀመሪያ ሙያ ፍቃድ ለጀማሪ መምህራንና በትምህርት ተቋማት አመራርነት ሰልጥነው ወደሙያው ለሚገቡ እንዲሁም ለደረጃው የብቃት መመዘኛ ላሟሉ የሚሰጥ ፣ ሁለተኛው ሙሉ የሙያ ፍቃድ፥ ለአምስት አመት የሚያገለግል ሆኖ የመጀመሪያ ሙያ ፍቃድ በማግኘት ሲሠሩ ቆይተው ላጠናቀቁ የሚሰጥ ሲሆን የሦሥተኛው ደግሞ ቋሚ የሙያ ፍቃድ ነው፡፡ ይህ ፍቃድ ሙሉ የሙያ ፍቃድ ከያዙ በኋላ ለደረጃው የሚመጥን አገልግሎት አጠናቀው የሙያ ፍቃድ ብቃት መመዘኛ ላሟሉ መምህራን፣ ለርዕሰ መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች የሚሰጥና በየአምስት አመት የሚታደስ ቋሚ የሙያ ፍቃድ ነው፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የትራፊክ አደጋን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከመንገድ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር “ከትራፊክ አደጋ የጸዳ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሀገራዊ ህዳሴ“ በሚል ሀገራዊ መሪ ቃል በሀገር ደረጃ የትራፊክ አደጋን ትርጉም ባለው መልኩ ለመቀነስ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ያካሄደው በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አደራሽ ሚያዝያ 20/2009 ዓ∙ም ነበር። የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚስትር ዴኤታ የሆኑት የተከበሩ ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ መድረኩን በእንኳን ዳህና መጣችሁ ንግግር በከፈቱበት ወቅት እንደተናገሩት የትራፊክ አደጋን ከምንጩ በመቀነስ የህዝባችንን ህይወት፣አካልና ንብረት፤እንዲሁም የሀገሪቱን ሀብት ከጥፋት ለመታደግ መላው ህብረተሰብ በትራፊክ ደህንነት ዙሪያ በባለቤትነት ስሜት እንድንቀሳቀስ ማድረግና ከዚህ አንጻር ዜጎችን በመልካም ሥነ-ምግባር መቅረፅ በአሁኑ ወቅት እጅግ በጣም አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁን ወቅት በትምህርት ዘርፉ ውስጥ በተለያዩ የትምህርት እርከኖች ላይ 30 ሚሊዮን የሚጠጉ ተማሪዎች፣ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ መምህራን፣ከተማሪዎች በስተጀርባ ያሉ በርካታ ወላጆችና መደበኛ ባልሆነ የተቀናጀ የጎልማሶች ትምህርት ላይ እየተሳተፉ ያሉ በርካታ ሠልጣኞች እንዳሉ ጠቅሰው ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በሚገባ በመቀናጀት ከዚህ በፊት ሲሠራ ከነበረው ይበልጥ ሥራውን በማስፋትና በማጠናከር ከተሠራ በሀገር ደረጃ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል አስገንዝበዋል።

የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት የትምህርት አቀራረብ ሥነ-ዘዴ እንደ አንድ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ማስፋፊያ አመራጭ ተወስዶ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንድተገበር የምመክር አውደ ጥናት ተካሄደ

የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል ከ2007 ዓ.ም ክረምት ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተተገበረ ያለውን የተፋጠነ የትምህርት ቤት ዝግጁነት የቅድመ መደበኛ ትምህርት አቀራረብ ውጤታማነትን ለማስተዋወቅና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማስፋት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውጪ ከሁሉም ክልሎች፤ ከድሬደዋ ከተማ አስተዳደር፣ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ እና ከህጻናት አድን ድርጅት እንዲሁም ከትምህርት ሚኒስቴር የተውጣጡ የሥራ ኃላፊዎችና የትምህርት ባለሙያዎች የተሳተፉበት አውደ ጥናት ሚያዚያ 2 እና 3/2009 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አደራሽ ተካሄደ። ይህ ፕሮግራም ከአራቱ የቅድመ መደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ሥነ-ዘዴ መካከል አንዱ ሲሆን በሦስቱም (መዋዕለ ህጻናት፤ ኦ ክፍልና ህጻን ለህጻን) የቅድመ መደበኛ ትምህርት አሰጣጥ ዘዴ ተጠቅመው ለመደበኛ ትምህርት ቅድመ ዝግጅት ያላደረጉትን እድሜያቸው ስድስት ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ህጻናትን በስምንት ሳምንታት ውስጥ ለመደበኛ ትምህርት ዝግጁ ማድረግ ያሚያስችል ፕሮግራም ነው።

Communication and Media Communication and Media

Communication Address:

Tel: +251-11-156-14-94

Fax: